Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

አሁንም ቅድሚያ ለተውሂድ!!!

አሁንም ቅድሚያ ለተውሂድ!!!
ድንበር ካለፉ ሱፍያ የጥመት ቡድን አንዱ ስለ ነቅሸበንዲያ ሱፊ ጠሪቃ መሪ ‹‹መውላና ታላቁ ሸይኽ ነዚም ሀቃኒ›› ብለው ስለሚጠሩት የሚከተለውን ኩፍር አባባል ፅፈውለታል
‹‹ (የሱልጣነል አውልያ ደረጃ) የአውልያዎች መሪ (የቁጥብ) ደረጃ››
‹‹የምታየው ነገር ሁሉ በሱልጣነል አውልያ ቁጥጥር ስር ነው፡፡ እዚህ ዩኒቨርስ ላይ ላሉ ሰዎች ሁሉ ሃላፍትናውን የወሰደው እሱ ነው፡፡ የጂኑ አለምም ይሁን የመላኢካዎች አለምንም ጭምር ሃላፍትና ወስዷል፤ የሰው ልጆች መሪ (ሱልጣን) የጂንም የመላኢካም (መሪ) እንደሆነው ሁሉ፡፡
ይህ የሱልጣነል አውሊያ (መቃም) ደረጃ ከልብ ጋር የተገናኘ ደረጃ ነው፡፡ አእምሮ እንኳን የዚህን ደረጃ ትልቅነት አስቦ አይደርስበትም፡፡ ይህ ደረጃ ባለንበት ወቅት ከመውላና ሸይኽ ናዚም ጋር የተቆራኘ ነው፡፡›› ኢናሊላሂ ወኢና ኢለይሂ ራጂዑን
ምንጭ ‹‹ሀቂቀቱል ሀቃኒ›› የተሰኘ የነዚሁ ሱፍዬች አርቲክል
በአላህ ፍቃድ ጥቂት መልሶች
1) የዚህ ዩኒቨርስ አስተናባሪ አላህ ብቻ መሆኑን የድሮዎቹ የቁረይሽ አጋሪያን እንኳን አልከዱም ነበር፡፡ የሚከተለው የአላህ ቃል ለዚህ ማስረጃችን ነው
قُلْ مَن يَرْزُقُكُم مِّنَ ٱلسَّمَآءِ وَٱلْأَرْضِ أَمَّن يَمْلِكُ ٱلسَّمْعَ وَٱلْأَبْصَٰرَ وَمَن يُخْرِجُ ٱلْحَىَّ مِنَ ٱلْمَيِّتِ وَيُخْرِجُ ٱلْمَيِّتَ مِنَ ٱلْحَىِّ وَمَن يُدَبِّرُ ٱلْأَمْرَ ۚ فَسَيَقُولُونَ ٱللَّهُ ۚ فَقُلْ أَفَلَا تَتَّقُونَ
«ከሰማይና ከምድር ሲሳይን የሚሰጣችሁ ማን ነው? መስሚያዎችንና ማያዎችንስ የፈጠረ ማን ነው? ከሙትም ሕያውን የሚያወጣ ከሕያውም ሙትን የሚያወጣስ ማን ነው? ነገሩን ሁሉ የሚያስተናብርስ ማን ነው?» በላቸው፡፡ «በእርግጥም አላህ ነው» ይሉሃል፡፡ «ታዲያ (ለምን ታጋራላችሁ?) አትፈሩትምን?» በላቸው፡፡
ተፍሲር ጠበሪ ላይ የሚከተለውን እናገኛለን
( ومن يدبر الأمر) ، وقل لهم: من يُدبر أمر السماء والأرض وما فيهن ، وأمركم وأمرَ الخلق (50) ؟ ، ( فسيقولون الله)
ነገሩን ሁሉ የሚያስተናብርስ ማን ነው?
በላቸው በሰማያት፤ በምድርም፤ በመካከላቸው ያለውን ነገር ፤ የናንተንም ጉዳይ ይሁን የፍጡራንን ጉዳይ የሚያስተናብረው ማን ነው በላቸው?
እነሱም (አጋሪዎችም) በእርግጥ አላህ ነው ይሉሃል፡፡
2) አደለም ይህ ወደ ኩፍር የሚጣራ ሰው መላኢካዎች በእርሱ ቁጥጥር ስር ሊውሉ፤ ሊያዛቸው፤ የአደም ልጆች ሁሉ ምርጥ የነብያት ሁሉ መደምደሚያ ነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ጂብሪል (አለይሂ ሰላም) ወህይ ይዞ መምጣት ሲዘገይ እና ሲናፍቃቸው ‹‹ምን ነው እንደ በፊቱ ቶሎ ቶሎ አትመጣም›› ሲሉት የሚከተለውን መልስ ሰጣቸው
وَمَا نَتَنَزَّلُ إِلَّا بِأَمْرِ رَبِّكَ ۖ لَهُۥ مَا بَيْنَ أَيْدِينَا وَمَا خَلْفَنَا وَمَا بَيْنَ ذَٰلِكَ ۚ وَمَا كَانَ رَبُّكَ نَسِيًّا
(ጂብሪል አለ) «በጌታህም ትእዛዝ እንጅ አንወርድም፡፡ በፊታችን ያለው፣ በኋላችንም ያለው በዚህም መካከል ያለው ሁሉ የርሱ ነው፡፡ ጌታህም ረሺ አይደለም፡፡
ስለዚህ ድንበር ያለፉ ሱፍያ የጥመት ቡድን መንገድ የሳተ ሆኖ ሳለ፤ ሱፍያን ጥሩ አድርጎ ለማቅረብ መሞከር ብሎም ‹‹ሱፊያዎች ጭንቀታቸው ሙስሊሙ እንዴት አንድ ሆኖ ንጹህ ቀልብ ይዞ አላህ ፊት ይቀርባል›› ማለት አላህ ፊት የሚያስጠይቅ ነው፡፡
ሱፍዬች መንገድ የሳቱ የጥመት ቡድኖች ናቸው፡፡ ስለነሱ የሌላቸውን ባህሪ እየሰጡ እነሱን ጥሩ አድርጎ ማቅረብ አማናን መብላት ነው፡፡ አገራችን ላይ ዛሬ አህባሽ የምንላቸው ትላንት ሱፊ ነን ሲሉ የነበሩ ናቸው፡፡ አንዳንዶች እንዲያውም አንድ ነን ብለው ሁሉ ከተፈራረሙዋቸው መሃል ትላንት ሰፈ ነን ሲሉ ቆይተው ዛሬ አህባሽ የሆኑ አሉ ሸይኽ ጠሃን ይመስል፡፡ ጠሃ ስም ቢቀያይርም ትላንት የነበረውን የሱፊ ኩፍር እምነት ሙታንን መለመን እና የመሳሰሉትን ይዞ ነው አሁንም ያለው፡፡ ሱፍያን አትንኩ፤ አታጋልጡ የሚሉ ሰዎች አላህን ሊፈሩ ይገባቸዋል፡፡
ይህንን ሰው ነዚም ሀቃኒን አገራችን ያሉ አህባሾች ሁሉ ፌስቡክ ላይ ወል ፎቶዋቸው አድርገውት ይንቀሳቀሳሉ፤ የዚህን ሰው ኩፍርያት አሳምረው በማቅረብ ሰው ሊያታሉ ይሞክራሉ፡፡
ባለፈው ካስታወሳችሁ ነዚም ሃቃኒ ‹‹በግራ በኩል ያለው መላኢካ አይፅፍም›› ያለበትን የኩፍር ንግግሩን መልስ የተሰጠበት መሆኑ ይታወሳል፡፡
አላህ ከጠሞ አጥማሚዎች ይጠብቀን፡፡

Post a Comment

0 Comments