Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

የጀሃነም ተጣሪዎች ክፍል 5

የጀሃነም ተጣሪዎች ክፍል 5
አሜሪካ የምትገኙ የኢትዬጵያ ሙስሞች ጠንቀቁ ሌሎችን በከለር ጥቁር የሆኑ አፍሪካዊያንን አስጠንቅቁ፡፡
አሜሪካ ውስጥ ተቀማጭነቱን ያደረገው እራሱን “Nation of Islam” ብሎ የሚጠራው ጀመዓ ከኢስላም አካል እንዳልሆነ ሊታወቅ ይገባል፡፡ ኢስላም ለጥቁሮች ብቻ እንደሆነ አድርገው በማቅረብ ይታወቃሉ፡፡ ከኢስላም ውጭ የሆኑ ብዙ እምነቶች አሏቸው ምንም እንኳን እራሳቸውን “Nation of Islam” ብለው ቡጠሩም፡፡

ከኩፍራቸው ውስጥ የሚከተሉትን ብለዋል ምንም እራሳቸውን ወደ ኢስላም እያስጠጉ ቢጠሩም
1) ‹‹አላህ በ1935 በሰው ምስል በጥቁር ሰው ምስል መጥቷል ስሙም ማስተር ደብሊው ፈራድ ይባላል›› ጥራቻ ይገባው ፈጣሪ አላህ፡፡ ይህ ኩፍር ነው፡፡
2) ‹‹ማስተር ደብሊው ኢላጃ ሙሃመድ የተባለውን ሰው መልክተኛው እና ነብዩ አድርጎ መርጦታል›› ይህም ኩፍር ነው፡፡
እና በጣም ብዙ ኩፍሮች

የመድረኩ አስተዋዋቂ የሚከተለውን ሲል የተሰበሰቡት ጠቅላል በጭብጨባ ይቀበሉታል
‹‹Are you ready to receive the messenger of Allah the honorable minister loius farrakhan›› ትርጉሙም ‹‹የአላህ መላክተኛ የሆነውን፤ የተከበረውን ሉዊስ ፋራካን ለመቀበል ዝግጁ ናችሁን››
ኢናሊላሂ ወኢና ኢለይሂ ራጂዑን ከአላህ መላክተኛ ሙሀመድ ኢብን አብደላህ በኋላ ሌላ ነብይ የለም እሳቸው የነብያት መደምደሚያ ናቸው፡፡ ነብየላህ ኢሳ (አለይሂሰላም) እንኳን ድጋሚ ሲመጡ በነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ሸሪዓ ነው አስተዳድረው የሚሄዱት፡፡

እነዚህ ሰዎች ኢስላምን ለጥቁር ብቻ አድርገው ይሰብካሉ አላህ ግን እንዲህ ይላል
يَٰٓأَيُّهَا ٱلنَّاسُ إِنَّا خَلَقْنَٰكُم مِّن ذَكَرٍ وَأُنثَىٰ وَجَعَلْنَٰكُمْ شُعُوبًا وَقَبَآئِلَ لِتَعَارَفُوٓا۟ ۚ إِنَّ أَكْرَمَكُمْ عِندَ ٱللَّهِ أَتْقَىٰكُمْ ۚ إِنَّ ٱللَّهَ عَلِيمٌ خَبِيرٌ
እናንተ ሰዎች ሆይ! እኛ ከወንድና ከሴት ፈጠርናችሁ፡፡ እንድትተዋወቁም ጎሳዎችና ነገዶች አደረግናችሁ፡፡ አላህ ዘንድ በላጫችሁ በጣም አላህን ፈሪያችሁ ነው፡፡ አላህ ግልጽን ዐዋቂ ውስጥንም ዐዋቂ ነው፡፡

ይቺ በጣም ትንሽ ፅሁፍ ናት በአላህ እዝነት ሰፊ ማብራሪያ ይኖራል ስለዚህ የጥመት መንገድ እምነት፡፡
አላህ ሆይ! ቀጥተኛውን መንገድ ምራን፡፡

Post a Comment

0 Comments