Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ሽርክ


By  Elias Awel & Salah Ahmed Abdurrahman
ሽርክ 
ሽርክ ማለት በአምልኮ ከአላህ ጋር ሌላን እኩል ማድረግ ማለት ነዉ፡፡ አምልኮን

ከአላህ ዉጪ ለማንም ማዋል የሽርክ ተግባር ነዉ፡፡ ተዉሂድ ፍትህ ነዉ፡፡ ሽርክ ግን

የበደሎች ሁሉ በደል ነዉ፡፡ በመሆኑም አላህ የማይምረዉ ከባድ ወንጀል ነዉ፡፡

አላህ እንዲህ ይላል፡-
“"አላህ በእርሱ ላይ ማጋራትን (ሽርክን) በፍፁም አይምርም! ከሽርክ በታች ያለን(ኃጢአት) ለሚሻው ሠው ይምራል" (ሱረቱ አል ኒሳእ) 
 “ባጋሩም ኖሮ ይሰሩት የነበሩት ከነሱ በታበሰ ነበር፡፡”(ሱረቱ አል አንአም) “እንሆ በአላህ የሚያጋራ ሰው አላህ በርሱ ጀነትን በእርግጥ እርም አደረገ፡፡መኖሪያቸውም እሳት ናት፡፡ለበዳዮች ምንም ረዳቶች የላቸውም ”(ሰረቱ አል ማኢዳህ) አንዳንድ ሰዎች ስለ ተውሂድ መስማት አይፈልጉም፡፡ የተለያዩ የኢባዳ

አይነቶችን ለነብያት፣ ለመላዕክት እና ለሷሊሆች ያዉላሉ፡፡ ለምሳሌ፡- ጭንቅ

በሚገጥማቸዉ ጊዜ በቀብር ዙሪያ ጠዋፍ ያደርጋሉ፣ ከአላህ ዉጪ ማንም መፈፀም

የማይችላቸዉን ጉዳዮች ለማስፈፀም ከምዕተ አመታት በፊት ለኖሩ ሰዎች የድረሱልን

ጥሪ ያሰማሉ! ይማፀናሉ!! ልጅ ቢያጡ ለሚያመልኩት ሰዉ ስለት ይገባሉ፣ በስሙም

ይምላሉ፡፡ በሀገራችን በተለያዩ ቦታዎች ይህ አይነቱ ቀብር አምልኮ ሰዎችን እየሸነገለ
ይገኛል፡፡
ጁንዱብ ኢብኑ አብዲላህ ባስተላለፉት ሀዲስ ነብዩ እንዲህ ብለዋል፡፡(አደራችሁን! ቀብሮችን የአምልኮ ስፍራ አንዳታረጉ፡፡ እኔ ከዚህ አይነቱ
ተግባር እከለክላችለሁ፡፡) ሙስሊም ዘግበዉታል
አዎ! ታላቁ ነብይ ይህንን የተናገሩት ህይወታችዉ ከማለፉ አምስት ቀናት ብቻ
ቀደም ብለዉ ነበር፡፡ ደግመዉ ደጋግመዉ ተመሳሳይ መልዕክት አስተምረዋል፡፡ በዱንያ
ቆይታቸዉ በመጨረሻዎቹ ሰዓታት ሳይቀር ከቀብር አምልኮ አስጠንቅቀዋል፡፡ አጅግ
በጣም የሚያሳዝነዉ፤ ሸይጣን ይህ አይነቱን ባዕድ አምልኮ የሚያስፋፋበትን ስልት
መቀየሩ ነዉ፡፡አንዳንድ ሰዎች ‹ቅርስን መንከባከብ› ፣ ‹ታሪክን ማቆየት› እና መሰል
ምክኒያቶችን በማቅረብ የቀብር አምልኮ ቦታዎች በብዙ ወጪ እያሻሻሉና እየገነቡ
ይገኛል፡፡ ይህ አይነቱ ተግባር ባዕድ አምልኮን ያበረታታል፡፡ በቁርአንና በሱና የተጠቀሱ
መረጃዎች አጅግ በጣም ግልፅና በርካታ ከመሆናቸዉ ጋር የተለያዩ ጦሪቃዎን
የሚከተሉ ሙሪዶች አንዲያዉቋቸዉ አልተደረገም፡፡ አንድ ዒባዳ(አምልኮ) ተቀባይነት
እንዲያገኝ ሁለት መስፈርቶች መሟላት አለባቸዉ፡፡ በኢኽላስ ለአላህ ብቻ ሊፈፀም እና
በነብዩ የአምልኮ ፈለግ መሰረት ሊተገበር ይገባዋል፡፡
አላህ ቀጥተኛዉን መንገድ ይመራቸዉ ዘንድ እንማፀነዋለን!! —
  
ስለት ...ለፍጡራን መሳል ይፈቀዳልን?በማህበረሰባችን ውስጥ ከሚንፀባረቁት የሽርክ አይነቶች አንዱ ዑለማዎች ከትልቁ ሽርክ አይነት የሚመድቡት ስለትን ከአላህ ሌላ ላለ አካል ማድረስ ነው፡፡ ስለት ማለት አንድ ሰው በእርሱ ላይ ግዴታ ያልሆነበትን ነገር በራስ ተነሳሽነት እራሱ ላይ ግዴታ ማድረጉ ነው፡፡ ይህ ደግሞ ከአላህ በቀር ለማንም የማይፈፀም አምልኮ መሆኑን የሚጠቁሙ የቁርአንና የሀዲስ መረጃዎች ብዙ ናቸዉ፡፡ አላህ በሱረቱል ሀጅ እንዲህ ይላል፡-
(وَلْيُوفُوا نُذُورَهُمْ (الحج:٢٩‹‹ስለቶቻቸውን ይሙሉ…›› አል ሀጅ 29በሌላውም የቁርአን አንቀፅ አላህ ደጋግ የሆኑ ባሮቹን ባህሪ ሲገልፅ እንዲህ ይላል፡-(يُوفُونَ بِالنَّذْرِ وَيَخَافُونَ يَوْمًا كَانَ شَرُّهُ مُسْتَطِيرًا(الإنسان: ٧‹‹ስለቶቻቸውን ይሞላሉ፡፡ መከራው ተሰራጭ የኾነንም ቀን ይፈራሉ፡፡›› ኢንሳን 7عن عائشة رضي الله عنها قالت: قال رسول الله صلى الله عليه وسلم : "من نذر أن يطيع الله فليطعه. ومن نذر أن يعص الله فلا يعصه". رواه البخاريእናታችን ዓኢሻ በአስተላለፉት ሐዲስ ላይ የአላህም መልዕክተኛ እንዲህ ይላሉ፡-
“አላህን ለመታዘዝ (የአላህ ህግ ለመተግበር) የተሳለ ሰው ስለቱን ያሟላ፣ በአላህ ላይ ለማመፅ (የአላህ ህግ ለመጣስ) የተሳለ ሰው ግን እንዳይስጥ” ቡኻሪ ዘግበውታል
እነዚህ የቁርአን የሐዲስ መረጃዎች እንደሚጠቁሙት ስለት ከአምልኮት አይነቶች መካከል አንዱ ነው፡፡ በተለይ በመጀመሪያው አንቀፅ ላይ ስለትን መሙላት ግዴታ መሆኑን በሚያጎላ መልኩ አላህ ካዘዘ ዒባዳ መሆኑን ያመለክታል፡፡ አንድን የአምልኮ ክፍል ከአላህ ሌላ አካል መስጠት ሽርክ ነው፡፡ ስለዚህም ስለትን ከአላህ ሌላ ለፍጡራን ማድረግ ከኢስላም የሚያስወጣ የሽርክ ተግባር ነው፡፡ ለደጋግ የአላህ ባሮች ፣ ለጅብሪልም ይሁን ለሌሎች መላእክት፣ ለሙታኖች፣ ለጂኖችና ለመሳሰሉት መሳል ግልፅ የሆነ የሽርክ ተግባር ነው፡፡ አላህ ከሽርክ ይጠብቀን!!


ሂርዝ
ሂርዝን ማንጠልጠል ሀራም ከመሆኑም በላይ ከሽርክ አይነቶች አንዱ ነው፡፡ ምክንያቱ ከአላህ ውጭ በሆነ ነገር መንጠልጠል ነው፡፡ ክፉን መካች አላህ ብቻ በመሆኑ ማንኛውም ሰው ጎጂን ነገር መከላከል ያለበት በአላህ በስሞቹና በባህሪያቱ ብቻ ነው፡፡
ኢብኑ መስዑድ እንዳሉት የአላህ መልዕክተኛ እንዲህ ሲሉ ሰምቻለው
 ‹‹ሩቃ፣ እርዝና መስተፋቅር መስራት ሽርክ ነው” 
አብደላህ ኢብኑ ዑከይም እንዳስተላለፉት የአላህ መልዕክተኛ እንዲህ ብለዋል
 “በአንድ ነገር ላይ የተንጠለጠለ ወደ ለርሱ ይተዋል”ዑቅበት ኢብን ዓሚር እንዳስተላለፉት የአላህ መልዕክተኛ እንዲህ ብለዋል “እርዝን ያንጠለጠለ ሽርክን ፈፅሟል” 
ፍጡራንን መማፀንና ዱዓን ለእነርሱ ማቅረብ 
አላህ እንጂ ሌላ ማንም በማይችለው ጉዳይ ላይ ከአላህ ሌላ የሆነን አካል መለመን፣ እርዳታን እና ጥበቃን መጠየቅ እንዲሁም ድረሱልን ማለት … እነዚህ የተለያዩ የዱዓእ ወይም የፀሎት ክፍሎች ናቸዉ፡ ኑዕማን ኢብኑ በሺር በአስተላለፉት ሀዲስ የአላህ መልዕክተኛ ዱዓእ ለአላህ ብቻ የሚገባ አምልኮ መሆኑን እንዲህ በማለት ይገልፁልናል፡- “ዱዓእ እርሱ እራሱ አምልኮ ነው፡፡” (ኢማሙ አህመድ፣ ቲርሚዚይ እና ሌሎችም ዘግበውታል)

ሽርክ ማለት ለአላህ ብቻ የሚገባን ዒባዳ (አምልኮ) ለሌላ አሳልፎ መስጠት ነው፡፡ ስለሆነም ከላይ የጠቀስናቸዉን የተለያዩ የዱዓእ ክፍሎች ለነብያት፣ ለመላኢኮች (መላእክት) ፣ ለጂኖች (ለአጋንንት)፣ ለሞቱም ሆነ በህይወት ሳሉ ደጋግ የአላህ ባሮች፣ ለአላህ ወዳጆች (ወልዮች) … ወዘተ ማዋል ከትልቁ ሽርክ ውስጥ የሚመደብ ተግባር ነው፡፡ ፍጡራንን “ያ ረሱለላህ፣ ያ ዐሊይ፣ ያ ሰይዳ ፋጡማ፣ ያ ሁሰይን፣ ያ አብዱልቃድር ጀይላኒ፣ ያ ሰይዳ ዘይነብ፣ ያ ነጃሺ፣ ያ ኑርሁሰይን፣ ያ አብሬት፣ ያ ቃጥባሪ፣ ያ አልከሰዬ፣ ያ ሐጂ አሊዬ … ወዘተ እያሉ አላህ እንጂ ሌላ ማንም ሊፈፅመው በደይችለው ጉዳይ ላይ ለምሳሌ፡- ልጅ የለኝምና ልጅ ስጡኝ ፣ ታምሜያለሁና ፈውሱኝ፣ ተርቤያለሁና ሲሳይን ለግሱኝ፣ ፣ ተጨንቂያሁና ከጭንቅ አውጡኝ፣ ፈርቼያለሁ እና ከአደጋ ጠብቁኝ፣ ከጀሀነም እሳት ጠብቁኝ፣ ለጀነት አብቁኝ፣ አማላጅ ጠበቃ ሁኑኝ… በማለት እነሱን መጠራትና መማፀን እና ድረሱልኝ ማለት በጥብቅ የተከለከለ ግልፅ የሽርክ ተግባር ነው፡፡

ይህ አይነቱ ጥሪ ሽርክ መሆኑን ከሚያመላክቱ እጅግ በጣም በርካታ የቁርአን እና የሐዲስ መረጃዎች መካከል ጥቂቶቹን ብቻ ለመጠቆም እምክራለሁ፡፡ አላህ እርሱ እንጅ ሌላ ማንም በማይችለው ጉዳይ ላይ ሌላን እርዳታ እንዳንጠይቅ ቃል ሲያስገባን እንዲህ ይላል፡-
}إِيَّاكَ نَعْبُدُ وإِيَّاكَ نَسْتَعِينُ { الفاتحة: ٥
‹‹አንተን ብቻ እናመልካለን አንተንም ብቻ እርዳታ እንለምናለን፡፡›› አል ፋቲሀ 5
እንዲሁም አላህ የሰው ልጆች ከደጋሚ፣ ከመተተኛ እና ከጠንቋይ፣ ከአጋንንት እና ከሌሎች እርኩሳን አካላት ክፋት እና ሴራ በእርሱ ብቻ አንዲጠበቁ ያዛል፡፡ አላህ መልዕክተኛውን እንዲህ እንዲሉ አዟቸዋል፡፡
قُلْ أَعُوذُ بِرَبِّ الْفَلَقِ (1) مِنْ شَرِّ مَا خَلَقَ (2) وَمِنْ شَرِّ غَاسِقٍ إِذَا وَقَبَ (3) وَمِنْ شَرِّ النَّفَّاثَاتِ فِي الْعُقَدِ (4) وَمِنْ شَرِّ حَاسِدٍ إِذَا حَسَدَ (5)
በል «በተፈልቃቂው ጎህ ጌታ እጠበቃለሁ፡፡ ከፈጠረው ፍጡር ሁሉ ክፋት፡፡ ከሌሊትም ክፋት ባጨለመ ጊዜ፤ በተቋጠሩ (ክሮች) ላይ ተፊዎች ከኾኑት (መተተኛ) ሴቶችም ክፋት፡፡ በተቋጠሩ (ክሮች) ላይ ተፊዎች ከኾኑት (ደጋሚ) ሴቶችም ክፋት፡፡›› አል ፈለቅ 1-5
  •  አላህ ብቻ እንጂ ሌላ ማንም በማይችለው ጉዳይ ላይ አንድ ሰው ከችግር እንዲያወጣውም ይሁን ጥቅምን እንዲያስገኝለት ሌላን አካል ድረሱልኝ ብሎ መማፀኑ ችግሩን እንደማያስወግዱለት ወይም ጉዳቱን እንደማይመክትለት ከመግለፁም ባሻገር ይህ ተግባርና እምነት ክህደት እንደሆነ ተናገሯል፡፡
قال تعالى :(وَمَنْ أَضَلُّ مِمَّن يَدْعُو مِن دُونِ اللَّهِ مَن لا يَسْتَجِيبُ لَهُ إِلَى يَومِ الْقِيَامَةِ وَهُمْ عَن دُعَائِهِمْ غَافِلُونَ) الأحقاف: ٥ – ٦
‹‹እስከ ትንሣኤ ቀን ድረስም ለእርሱ የማይመልስለትን (ጣዖት) ከአላህ ሌላ ከሚጠራ ሰው ይበልጥ የተሳሳተ ማነው? እነርሱም ከጥሪያቸው ዘንጊዎች ናቸው፡፡ ሰዎችም በተሰበሰቡ ጊዜ (ጣዖቶቹ) ለእነርሱ ጠላቶች ይኾናሉ፡፡ (እነሱን) መገዛታቸውንም ከሓዲዎች ይኾናሉ፡፡›› አል አህቃፍ 5-6
عن ابن مسعود رضي الله عنه أن رسول الله صلى الله عليه وسلم قال: (من مات وهو يدعو مندون الله نداً دخل النار) رواه البخاري
  • ዓብድላህ ኢብኑ መስዑድ በአስተላለፉት ሐዲስ የአላህ መልዕክተኛ እንዲህ ይላሉ “ከአላህ ውጭ ሌላን አካል ለአላህ አጋር አድርጎ መለመንን ሳይተው (ተውበት ሳያደርግ) የሞተ ሰው እሳት ገባ፡፡” ቡኻሪ ዘግበውታል
 ففي الحديث الصحيح قال النبي صلى الله عليه وسلم لابن عباس رضي الله عنهما : (...إذا سألت فاسأل الله وإذا استعنت فاستعن بالله) رواه الترمذي وقال حديث حسن صحيح
  • በሌላ ሐዲስም የአላህ መልዕክተኛ እንዲህ ብለዋል “መለመንን ስትፈልግ አላህን ብቻ ለምን፣ እርዳታንም ብትፈልግ በአላህ ብቻ ተረዳ” ቲርሚዚይ ዘግበውታል