Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

የላኢላሀ ኢለላህ መስፈርቶች የሚከተሉት ናቸው

  የላኢላሀ ኢለላህ መስፈርቶች የሚከተሉት ናቸው
1. የመሀይምነት ተፃራሪ የሆነው እውቀት
ይህም ማለት የዚህ ቃል መልዕክት ቃሉ ዉድቅ የሚያደርጋቸዉን እና የሚያፀድቃቸውን ነገሮች ማወቅ ማለት ነው፡፡ ማለትም አላህ በእውነት ሊመለክ የሚገባ እና ብቻውን የሚመለክ አምላክ መሆኑን ከእርሱ ውጭ ያሉ ሁሉ አምልኮ የማይገባቸው ሀሰት አማልክት መሆናቸውን ማወቅ ሲሆን ካለ እዉቀት የሚሰጥ ምስክርነት ተቀባይነት የለዉም። ለዚህም ማስረጃው ቀጣዩ የአላህ ቃል ነው፡፡
 (እነዚያም ከአላህ ሌላ የሚያመልኳቸዉ እነሱ የሚያውቁ ሆነው በእውነት ከመሰከሩት በስተቀር ምልጃን አይችሉም) አል-ዙኸሩፍ 86

2. የጥርጥር ተፃራሪ የሆነው እርግጠኝነት
ይህ መስፈርት የሚያመለክተው (ላ ኢላሀ ኢለላህ) የሚለውን ምስክርነት ከልቡ በመቀበል አላህ ብቻውን የሚመለክ አምላክ መሆኑን እና ከእርሱ ውጭ ያሉ አማልክት በሙሉ ከንቱ መሆናቸውን በአንደበት እንደሚናገረው ሁሉ በልቡም ማረጋገጥ እንዳለበት ነው። እርግጥኝነት ከሌለ ጥርጥር ዉስጥ ነዉና እምነቱ ከመናፍቃን እምነት አይለይም። አላህ (ሱ.ወ)እንዲህ ይላል፡-
 ({እዉነተኞቹ} ምእመናን እነዚያ በአላህና በመልእክተኛዉ ያመኑት ከዚያም ያልተጠረጠሩት ናቸው) አል-ሑጁራት 15
የአላህ መልእክተኛምه ለአቡ ሑረይራ እንዲህ ብለውታል፡- ‹‹ከዚህ አጥር በስተጀርባ የአላህን ብቸኛ አምላክነት ከልቡ በእርግጠኝነት የሚመሰክር ሰው ብታገኝ በጀነት አበስረው፡፡›› ሙስሊም ዘግበዉታል

3. የማጋራት ተፃራሪ የሆነው ማጥራት (ኢኽላስ)
የላኢላሀ ኢለላህን የምስክርነት ቃል የሰጠ ሰው ስራውን ከሽርክ ማጥራት አለበት፣ የሚያከናውናቸውን ተግባራቶችም ሆነ የሚናገራቸውን ንግግሮች በሙሉ ለአላህ ብቻ ብሎ መፈጸም አለበት። በዚህ የምስክርነት ቃል የዱንያ ጥቅማጥቅሞችንና ዝናን ከመከጀል ለይዩልኝ እና ይስሙልኝ ከመስራት መጥራት አለበት፡፡ ለዝና ወይም ለዱንያዊ ጥቅም ተብሎ የሚፈፀም ተግባር ከአላህ ጋር ሌሎችን በአምልኮ ማጋራት በመሆኑ ምንዳን አያስገኝም።የሚያስከትለውም ቅጣት ብርቱ ነው። የአላህ መልዕክተኛه እንዲህ ብለዋል ‹‹የቂያማ ዕለት የኔን ምልጃ በማግኘት ዕድለኛ የሚሆነው ከልቡ ጥርት አድርጎ ላ ኢላሀ ኢለላህ ያለ ሰው ነው፡፡›› ቡኻሪ ዘግበዉታል፡፡

4. የውሸት ተፃራሪ የሆነው እውነተኛነት
ላ ኢላሀ ኢለላህ ብሎ የሚመሰክረው ግለሰብ በልቡ የሚያምንበት እምነትም ሆነ በአንደበቱ የሚናገረው ንግግር እውነትን የተላበሰ መሆን አለበት። ይህ ካልሆነ ውሸትን የሚያራምድ አታላይ እንጂ እዉነተኛ መስካሪ አይሆንም።የአላህ መልእክተኛ هእንዲህ ይላሉ ‹‹ማንኛውም ከልቡ በእውነተኛነት በአላህ ብቸኛ አምላክነትና በሙሐመድه መልዕክተኝነት የሚመሰክር ሰው አላህ ከእሳት እርም ይለዋል›› ቡኻሪ ዘግበዉታል
  ላ ኢላሀ ኢለላህ ብሎ የሚመሰክረው ግለሰብ ይህ ምስክርነቱ ግዴታ የሚያደርጋ ቸውን ነገሮች ሁሉ መውደድ ይገባዋል። ወዶ እና ፈቅዶ ካልመሰከረ ተገዶ ነዉና ምስክርነቱ ተቀባይነት የለዉም። ላኢላሀ ኢለላህ የሚለውን የምስክርነት ቃል ፣ አላህን እንዲሁም አላህን በብቸኝነት የሚያመልኩትን የተውሂድ ሰዎችን መውደድ ነው፡፡ አላህ እንዲህ ይላል ፡-
 (ከሰዎችም አላህን እንደሚወዱ የሚወዷቸው ሆነው ከአላህ ሌላ ባለንጣዎችን የሚይዙ አሉ፡፡ እነዚያ ያመኑትም አላህን በመውደድ (ከነርሱ) ይበልጥ የበረቱ ናቸው) አል በቀራህ 165

5. የመጥላት ተፃራሪ የሆነው መውደድ
ላ ኢላሀ ኢለላህ ብሎ የሚመሰክረው ግለሰብ ይህ ምስክርነቱ ግዴታ የሚያደርጋ ቸውን ነገሮች ሁሉ መውደድ ይገባዋል። ወዶ እና ፈቅዶ ካልመሰከረ ተገዶ ነዉና ምስክርነቱ ተቀባይነት የለዉም። ላኢላሀ ኢለላህ የሚለውን የምስክርነት ቃል ፣ አላህን እንዲሁም አላህን በብቸኝነት የሚያመልኩትን የተውሂድ ሰዎችን መውደድ ነው፡፡ አላህ እንዲህ ይላል ፡-
 (ከሰዎችም አላህን እንደሚወዱ የሚወዷቸው ሆነው ከአላህ ሌላ ባለንጣዎችን የሚይዙ አሉ፡፡ እነዚያ ያመኑትም አላህን በመውደድ (ከነርሱ) ይበልጥ የበረቱ ናቸው) አል በቀራህ 165

6. የመተው ተፃራሪ የሆነው መታዘዝ
  ይህ ማለት ‹‹ላ ኢላሀ ኢለላህ›› የሚለው የምስክርነት ቃል ለሚጠቁማቸው ትዕዛዛትና ክልከላዎች ሙሉ ታዛዥ ተከታይና ተናናሽ መሆን ነው፡፡ አላህ (ሱ.ወ) እንዲህ ይላል፡-
 (እርሱ መልካም ሰሪ ሆኖ ፊቱን (በመታዘዝና በመተናነስ) ወደ አላህ የሚሰጥ ሰው ጠንካራን ገመድ በእርግጥ ጨበጠ...) ሉቅማን 22
7. የተቃውሞ ተፃራሪ የሆነው መቀበል
ላ ኢላሀ ኢለላህ ብሎ የሚመሰክረው ሰው ቃሉ ግዴታ የሚያደርጋቸዉን ነገሮች በሙሉ (አላህን በብቸኝነት ማምለክን እና ለሌላ ለፍጡራን የሚከናወኑ አምልኮቶችን መተው) ከልቡ አምኖ በአንደበቱ መስክሮ መቀበል አለበት። ይህንን መስፈርት ያላሟላ እምቢተኛ ነዉና መሰከረ አይባልም።አላህ ኩራተኛነታቸውን እና አለመቀበላቸውን እንዲህ በማለት ከገለፃቸው ሙሽሪኮች ጎራ ይመደባል፡፡
 (እነርሱ፤ ‹ከአላህ ሌላ አምልኮ የሚገባው ሆኖ የሚመለክ አምላክ የለም› በተባሉ ጊዜ ይኮሩ ነበር፡፡ እኛ ለእብድ ባለቅኔ ብለን አማልክቶቻችንን የምንተው ነን ይሉም ነበር፡፡) አልሷፋት 35-36

8. ከአላህ ውጪ የሚመለኩ አማልክትን መካድ (ማስተባበል) ናቸው።
ከላይ እንደተመለከትነው ከአላህ ሌላ አምልኮ የሚገባው እንደሌለ የምናረጋግጥበት ቃለ ተውሂድ ይህንን መስፈርት በዉስጡ ያካትታል። ከባዕድ አምልኮ ያልተላቀቀ ሰው በአላህ አላመነም።