Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ተውሂድ የሁሉም ነብያት ተልዕኮ

By Salah Ahmed Abdurahman
ተውሂድ የሁሉም ነብያት ተልዕኮአላህ በተለየዩ ዘመናት በርካታ ነቢያትን ልኳል፡፡ እነዚህ ነብያት ለተላኩላቸው ሕዝቦች ያስተምሩ የነበረው የአላህን ብቸኛ አምላክነት የሚገልፀውን (ተውሂድ አል ኡሉሂያ) የተውሂድ ክፍል እንደነበረ ቁርአን ይነግረናል፡፡ وَلَقَدْ بَعَثْنَا فِي كُلِّ أُمَّةٍ رَسُولًا أَنِ اعْبُدُوا اللَّهَ وَاجْتَنِبُوا الطَّاغُوتَالنحل: ٣٦
‹‹በየሕዝቡም ሁሉ ውስጥ «አላህን ተገዙ፤ ጣዖትንም ራቁ» በማለት መልክተኛን በእርግጥ ልከናል፡፡›› (አል ነህል 36)
በሱረቱል አንቢያ ውስጥም አላህ ወደየህዝቦቻቸው ስለላካቸው መልዕክተኞች ለነቢያችን ሲገልፅላቸው እንዲህ ይላል፡-
وَمَا أَرْسَلْنَا مِنْ قَبْلِكَ مِنْ رَسُولٍ إِلَّا نُوحِي إِلَيْهِ أَنَّهُ لَا إِلَهَ إِلَّا أَنَا فَاعْبُدُونِ
الأنبياء: ٢٥
‹‹ከአንተ በፊትም እነሆ ከእኔ ሌላ አምላክ የለምና ተገዙኝ በማለት ወደርሱ የምናወርድለት ቢኾን እንጅ ከመልክተኛ አንድንም አልላክንም፡፡›› (አል አንቢያ 25)
በየዘመናቱ ወደ ሕዝቦቻቸው የተላኩ ነቢያት በአቂዳ ዙሪያ ጠንከር ያለ የፀና አቋምና እምነት እንዲኖራቸው ነበር፡፡ ሕዝባቸውን ያስተምሩና ይመክሩ፣ ያስጠነቅቁና ይዘክሩ የነበረው፡፡ ህዝቡ ግን ጌታቸው ለእርሱ የዋለውን ውለታና አመስግነው መቀበል ሲገባቸው አስተባበሉ፡፡ በአመፀኛነታቸውም ገፉበት፡፡
በአቂዳ ዙሪያ ባሉ የዲን ጉዳዮች ማወላወል ፈፅሞ የለም፡፡ የሐቀኛ ምዕመናን የአህሉ ሱና ወልጀመዓ የሕይወት መመሪያ የሆነውን ቁርአንንና የነብዩን ሱና ሙሉ በሙሉ መከተል ብቻ ነው፡፡ በየዘመናቱ የተላኩ ነቢያትም ያስተማሩት ይህንኑ ነው፡፡