Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ሰለፎች እነማን ናቸወ? ሰለፊያህ?


By  Elias Awol
ሰለፎች እነማን ናቸወ?ሰለፎች ስንል እኛን የተቀደሙ እና በመልካም ስራቸው አርአያሆነው ያለፉ አበው የሰሀባ እና እነርሱን በመልካም የተከተሉ ታቢዒዮችለማለት ነው። የሰለፎችን ግንዛቤ መከተል ሁሉንም ሙስሊሞች ወደአንድና ቀጥተኛ እና ስኬታማ መንገድ የሚያመጣ ንትርኮችን እናአለመግባባቶችን ሁሉ የሚፈታ ልዩ መርህ ነው። የሰለፎችን ግንዛቤ ማስቀደምና መቀበል ግዴታ መሆኑን የሚገልጹበርካታ መረጃዎች አሉ። ጥቂቶቹን እንዳስሳለን፦1- አላህ (ሱ.ወ) ቁርአንን ከማንም ይበልጥ መልዕክቱን እንደተገነዘቡት፣ የአላህን ትዕዛዛት እንደፈጸሙ፣ ክልከላዎችንም እንደራቁ፣የሚፈለገው ቦታ ላይ እንደደረሱ የመሰከረላቸው የነብዩ ባልደረቦች
ናቸው፡፡ እነዚህ የመጀመሪያዎቹ ቀዳሚዎች ከሙሓጂሮችና ከአንሳር፣
እነርሱንም በመልካም የተከተሉአቸውን አላህ (ሱ.ወ) ጀነትን
አዘጋጅቶላቸዋል፡፡ አላህ (ሱ.ወ) በዱንያ ላይ እያሉ ጀነት እንደሚገቡ
መስክሮላቸዋል ፣ለሁሉም ሥራቸውን እንደወደደላቸው ጠቁሞናል፡-
-
• • • ) صورة توبة: ١٠٠)
ከስደተኞቹና ከረዳቶቹም የመጀመሪያዎቹ ቀዳሚዎች፤
እነዚያም በበጎ ሥራ የተከተሉአቸው፤ አላህ ከነርሱ ወዷል
(ሥራቸውን ተቀብሏል)፤ ከእርሱም ወደዋል (በተሰጣቸው ምንዳ
ተደስተዋል)፤ በሥሮቻቸውም ወንዞች የሚፈሱባቸውን ገነቶች
በውስጣቸው ዘላለም ነዋሪ ሲሆኑ ለነርሱ አዘጋጅቶላቸዋል፤ ይህ
ታላቅ ዕድል ነው፡፡ (ሱረህ አት-ተውባህ፡100)
በዚህ መልኩ አላህ (ሱ.ወ) ቃል ኪዳኑን ሲገልጽላቸው ሙሓጂሮችና
አንሳሮች ብቻ ሳይሆኑ የተጠቀሱት ከሙሓጂሮችና ከአንሳሮች ውጭ
በመልካም የተከተሉአቸውም ተጠቅሰዋል፡፡ በበጎ ሥራ የተከተሉአቸው
የሚለው ግን መስፈርት ነው።
ይህንን ደረጃ ለማግኘት ከነርሱ በኋላ መምጣት ብቻ ሳይሆን
እነርሱን “ቢኢሕሳን” በመልካም ሥራ፣ በበጎ ተግባር መከተል የግድ
ነው፡፡ ስለዚህ አል-ሙሓጂሩን ወል አንሳርን መከተል የግድ ይሆናል
ማለት ነው፡፡ ማንኛዉም ሙስሊም ትልቁ የሚፈልገው ነገር ጀነት
መግባት፣ የአላህን ውዴታ ማግኘት ነው፡፡ አላህ (ሱ.ወ) የሰሀቦች ጉዞ
ለጀነት እንዳበቃቸው ከነገረን ይህ የተሞከረ መንገድ ትክክለኛ መንገድ
ስለመሆኑ በፍጹም ሳንጠራጠር ግንዛቤያቸዉን ማስቀደም
ይጠበቅብናል።አላህ(ሱ.ወ)እንዲህይላል፡-
• (صورة بقرة :١٣٨ ١٣٨)
በርሱ ባመናችሁበት ብጤ ቢያምኑ በርግጥ ተመሩ፤ ቢዞሩም
እነርሱ በጭቅጭቅ ውስጥ ብቻ ናቸው፡፡ (ሱረህ አል-በቀራህ፡137)
ይህ አንቀጽ ግልጽ በሆነ መልኩ እንደሚያመለክተው የሰለፎች
እምነትና ግንዛቤ ከእነርሱ በኋላ የሚመጡ ሰዎችን ሁሉ የሚዳኝ
መመዘኛ ነው። እናንተ (ሶሓቦች) ባመናችሁበት ካመኑ ቀጥተኛዉን
መንገድ ተመርተዋል እናንተ (ሶሓቦች) ባመናችሁበት ብጤ ካላመኑ ግን
መንገድ ስተዋል፣ ጠመዋል ማለት ነው፡፡ ሰሀቦች በእውነተኛ
ተከታይነታቸው እና በመልካም ግንዛቤያቸው ለሰው ልጆች ሁሉ
ተምሳሌት ናቸው፡፡
የአላህ መልዕክተኛ በትክክለኛ ሐዲሥ ላይ ሰሒሕ ነው
ገይሪማ እንደሚናገሩት ቢሪዋየት ዒምራን እብን ሐሰን ይላሉ፡-
قال رسول الله صلي الله عليه وسلم :"خير الناس قرني ثم الذين يلو٥هم ثم الذين يلو٥هم "
رواه البخاري ومسلم
«ከሰዎች ሁሉ የተሻለው ትውልድ የኔ ትውልድ ነው፡ ቀጥሎም
ተከታዮቻቸው፡ ቀጥሎም ተከታዮቸቸው» ይላሉ፡፡  Sultan Kheder ሰለፊ ስንል ምን ማለታችን ነው?1ኛ- ቁርዓን +ሐዲስ +የሰለፎች ግንዛቤ = ሰለፊያህ ስለሆነ ነው።2ኛ- ሰሓባ + ታብዕይ +የታብዕይ ተከታዮች ……….ሌሎችም እነሱን በመልካም አርዓያ የተከተሏቸው=ቀደምት ሙስሊሞች ማለት ስለሆነ1ኛው እና 2ኛው ሲደመር =ሰለፊያህ =እስልምናን በትክክኛው ግንዛቤ መረዳት ስለሆነ ነው።