Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ከአህሉሱና ወልጀመዓህ መሰረታዊ የእምነት መርሆዎች መካከል

BY;- Aman Ibrahim

ከአህሉሱና ወልጀመዓህ መሰረታዊ የእምነት መርሆዎች መካከል፡-
1 . ኢማን (እምነት) ሶስት ነገሮችን (ንግግርን፣ ተግባርንና ልቦናዊ እምነትን) የሚያቅፍ መሆኑን ፤
2 . አሏህን በመታዘዝ እምነት የሚጨምር፤ ወንጀልን በመስራት ደግሞ እምነት የሚቀንስ መሆኑን፤
3 . እምነትን ከልቦና ውጭ በተግባርና በንግግር ብቻ ማስገኘቱ የሙናፊቆች እምነት እንደሆነና ፤ የልቦና እውቀት ያለ ንግግርና ተግባር የከሀዲዎችና የአመጸኞች እምነት መሆኑን ያረጋግጣሉ፡፡
وَجَحَدُوا بِهَا وَاسْتَيْقَنَتْهَا أَنْفُسُهُمْ ظُلْمًا وَعُلُوًّا فَانْظُرْ كَيْفَ كَانَ عَاقِبَةُ الْمُفْسِدِينَ
"ነፍሶቻቸውም ያረጋገጧት ሲኾኑ ለበደልና ለኩራት በርሷ ካዱ የአመጸኞችም ፍጻሜ እንዴት እንደ ነበር ተመልከት፡፡(ነምል፡14)
فَإِنَّهُمْ لَا يُكَذِّبُونَكَ وَلَكِنَّ الظَّالِمِينَ بِآيَاتِ اللَّهِ يَجْحَدُونَ
"እነርሱም (በልቦቻቸው) አያስተባብሉህም ፤ግን በዳዩቹ በአሏህ አንቀጾች ይክዳሉ፡፡"(አንዓም፡ 33)
እምነት በልብ ብቻ የሚቋጠር ወይም በንግግርና በተግባር አስገኝተውት ከልባችን የሚወገድ አይደለም፤ የሶሰቱ (የልቦና፣ የአንደበትና የተግባር) ጥምረት እንጅ፡፡
የሶስቱንም የእምነት ጥምረት አሏህ ሱብሃነሁ ወተዓላ እንደሚከተለው ገልጾታል፡-
إِنَّمَا الْمُؤْمِنُونَ الَّذِينَ إِذَا ذُكِرَ اللَّهُ وَجِلَتْ قُلُوبُهُمْ وَإِذَا تُلِيَتْ عَلَيْهِمْ آيَاتُهُ زَادَتْهُمْ إِيمَانًا وَعَلَى رَبِّهِمْ يَتَوَكَّلُونَ (2) الَّذِينَ يُقِيمُونَ الصَّلَاةَ وَمِمَّا رَزَقْنَاهُمْ يُنْفِقُونَ
"ፍጹም ምዕመናን እነዚያ አሏህ በተወሳ ጊዜ ልቦቻቸው የሚፈሩት በነሱም ላይ አንቀጾቻችን በተነበቡ ጊዜ እምነትን የሚጨምሩላቸው በጌታቸውም ላይ ብቻ የሚመኩት ናቸው፡፡ እነዚያ ሶላትን ደንቡን አሟልተው የሚሰግዱ ከሰጠናቸውም ሲሳይ የሚለግሱ ናቸው፡፡"( አንፋል፡ 2-3)
ተግባር ከኢማን አይደለም ለሚሉት ሙርጅዓዎች የሚከተለው የአሏህ ንግግር መልስ ይሆናቸዋል፤
وَمَا كَانَ اللَّهُ لِيُضِيعَ إِيمَانَكُمْ
አሏህ እምነታችሁን የሚያጠፋ አይደለም፤""
" ኢማነኩም " ያለው ቃል "ሶላተኩም" በሚል ተተርጉሟል፡፡ ይህ ማለት ሶላት ከእምነት አካል መሆኑንያረጋግጣል፡