Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

የጀሃነም ተጣሪዎች ክፍል 4

የጀሃነም ተጣሪዎች ክፍል 4
አሜሪካዊ አሽዐሪ ሱፊ ሀምዛ ዩሱፍ የሚከተሉትን ይላል
‹‹አቂዳ በጣም ቀላል ነው በትንሽ ቀን ውስጥ ልትማረው ትችላለህ››
‹‹በመጀመሪያ ትኩረት መስጠት የምፈልገው አቂዳ ኢማን አይደለም፡፡ አቂዳ አእማድ (የማይቀየር ሙሶሶ) ነው፤ ሙስሊሞች አቂዳ ላይ ትኩረት ሰጥተው አያውቁም፡፡ ትኩረት የሰጡት ለኢማን ነው››
‹‹አቂዳ በጣም ቀላል ነው በትንሽ ቀን ውስጥ ልትማረው ትችላለህ በጥሩ አስተማሪ፡፡ ቁጭ በል መትኖች አሉ ..... ትማራቸዋለህ እኔ የተማርኩበት መትን ሞሪታንያ በረሃ ላይ 20 መስመር ግጥም ነው፡፡ የአቂዳ (ሙሶሶ) ጠቅላላ እዛ (20 መስመር) ውስጥ ነው፡፡ ልትማረው ትችላለህ ለአቂዳ ትኩረት መስጠት ህመም ነው፤ የሙስሊሞች በሽታ ነው፡፡››

ለዚህ ጠሞ አጥማሚ ጥቂት መልሶች ከሸይኽ ፈውዛን (ሀፊዘሁላህ)
ነብያት በጠቅላላ በተለይ የነብያት ሁሉ መደምደሚያ ነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) የተጣሩት የኡማውን አቂዳ ማስተካከል ነበር፡፡
አላሁ ሱብሀነሁ ወተዓላ የ18 ነብያትን ገድል ከተናገረ በኋላ እንዲህ ይላል
1) وَلَوْ أَشْرَكُوا۟ لَحَبِطَ عَنْهُم مَّا كَانُوا۟ يَعْمَلُونَ
ባጋሩም ኖሮ ይሠሩት የነበሩት ከነሱ በታበሰ ነበር፡፡
2) إِنَّهُۥ مَن يُشْرِكْ بِٱللَّهِ فَقَدْ حَرَّمَ ٱللَّهُ عَلَيْهِ ٱلْجَنَّةَ وَمَأْوَىٰهُ ٱلنَّارُ ۖ وَمَا لِلظَّٰلِمِينَ مِنْ أَنصَارٍ
እነሆ! በአላህ የሚያጋራ ሰው አላህ በርሱ ላይ ገነትን በእርግጥ እርም አደረገ፡፡ መኖሪያውም እሳት ናት፡፡ ለበዳዮችም ምንም ረዳቶች የሏቸውም፡፡
3) ነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለምን) እንዲህ ይላቸዋል አላህ
وَلَقَدْ أُوحِىَ إِلَيْكَ وَإِلَى ٱلَّذِينَ مِن قَبْلِكَ لَئِنْ أَشْرَكْتَ لَيَحْبَطَنَّ عَمَلُكَ وَلَتَكُونَنَّ مِنَ ٱلْخَٰسِرِينَ
ብታጋራ ሥራህ በእርግጥ ይታበሳል፡፡ በእርግጥም ከከሓዲዎቹ ትኾናለህ ማለት ወደ አንተም ወደእነዚያም ካንተ በፊት ወደነበሩት በእርግጥ ተወርዷል፡፡

ከላይ የተጠቀሱ እና ሌሎችም አንቀፆች ለአቂዳ ትኩረት እና ቅድሚያ እንደሚሰጠው ያሳያሉ፡፡ አቂዳው ላልተስተካከለ ሰው ሰላትም፤ ሀጅም፤ ጀሃድም ማንኛውም አምልኮ አይጠቅመውም፡፡ ተግባራት ጠቅላላ ተቀባይነት የላቸውም ከአቂዳ መስተካከል በኋላ ቢሆን እንጂ፡፡
ይህም (መልስ) ይሁነው ለዛ ‹‹ለአቂዳ ትኩረት ሳንሰጥ ኢማን በቂ ነው›› ለሚለው (ሰው)
ይህ አባባሉ የተሳሳተ እና (ሃቅን) የተቃረነ ነው፡፡ ምክንያቱም አቂዳ ያልተስተከለ ኢማን ኢማን አይባልም፡፡ አቂዳ ካልተስተካከለ ኢማን እና ሃይማኖት የለም፡፡

ትርጉሙ ላይ አንዳንድ የራሴን ማብራሪያ ጨምያሁ፡፡
አላህ ከጠሞ አጥማሚዎች ይጠብቀን፡፡ የአላህ ሰላት እና ሰላም በነብያት መደምደሚያ፤ በቤተሰቦቻቸው፤ በባልደረቦቻቸው፤ ሀቅን በተከተለ ላይ ሁሉ ይሁን፡፡

Post a Comment

0 Comments