Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ጀሀነም በራፍ ላይ ቆመው ከሚጣሩ ተጣሪዎች ክፍል 2

ጀሀነም በራፍ ላይ ቆመው ከሚጣሩ ተጣሪዎች
ክፍል 2

ወልይ ይሉታል ይህን ጠሞ አጥማሚ ነቅሸበንዲ፡፡ ከዚህ ዘመን ጠሞ አጥማሚዎች መካከል ነዚም ሀቃኒ ነቅሸበንዲ ሱፊ እንዲህ ሲል ይቀጥፋል
‹‹እኔ ምንም ነገር አይያዝብኝም (አልጠየቅም፤ ሚዛን ላይ አይቀርብብኝም)፤
80 (አመተት) ከመሞለላኘኝ በኃኋለላ፤
የአራህማን ኡተቃ (በአላህ ነፃ የተባልኩ የማልጠየቅ) ሆኛለሁ፤
ይኽኛው (በቀኝ በኩል ያለው መላኢካ) ይፅፋል፤
ይኽኛው (በግራ በኩል ያለው) አይፅፍም (ብሎ በእጀጁ ይጠቁማል)፤
(ልብ በሉ ወንጀሌ አይመዘገብም እንደማለት ነው፡፡ የግራው መላኢካ ወንጀሌን አይመዘግብም እንደማለት ነው፡፡)
በየቀኑ 40 ግዜ እንድምል ተፈቅዶልኛል፡፡››

አላህ ደግሞ እንዲህ ይላል
وَلَقَدْ خَلَقْنَا ٱلْإِنسَٰنَ وَنَعْلَمُ مَا تُوَسْوِسُ بِهِۦ نَفْسُهُۥ ۖ وَنَحْنُ أَقْرَبُ إِلَيْهِ مِنْ حَبْلِ ٱلْوَرِيدِ
ሰውንም ነፍሱ (በሐሳቡ) የምታጫውተውን የምናውቅ ስንኾን በእርግጥ ፈጠርነው፤ እኛም ከደም ጋኑ ጅማት ይበልጥ ወደርሱ ቅርብ ነን፡፡
إِذْ يَتَلَقَّى ٱلْمُتَلَقِّيَانِ عَنِ ٱلْيَمِينِ وَعَنِ ٱلشِّمَالِ قَعِيدٌ
ሁለቱ ቃል ተቀባዮች (መላእክት) ከቀኝና ከግራ ተቀማጮች ኾነው በሚቀበሉ ጊዜ (አስታውስ)፡፡
مَّا يَلْفِظُ مِن قَوْلٍ إِلَّا لَدَيْهِ رَقِيبٌ عَتِيدٌ
ከቃል ምንም አይናገርም በአጠገቡ ተጠባባቂና ዝግጁ የኾኑ (መላእክት) ያሉበት ቢኾን እንጅ፡፡

አላህ ከጠሞ አጥማሚዎች ይጠብቀን፡፡

Post a Comment

0 Comments