Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

የአቡበክር እና የኡመር (ረድየላሁ አንሁም) አይነት መሬ እንፈልጋለን???

የአቡበክር እና የኡመር (ረድየላሁ አንሁም) አይነት መሬ እንፈልጋለን???
========================================
ሸይኽ ኡሰይሚን (ረሂመሁላህ) ሪያዱ ሷሊሂን ኪታብን ሲያብራሩ የሚከተለውን ታሪክ አስቀምጠው ነበር፡፡
የበኒ ኡመያ መሪ ከሆኑት ውስጥ አብድመሊክ ኢብን መርዋን (ረሂመሁላህ) የተባሉት ማህበረሰቡ ስለ ስልጣናቸው አስመልክቶ እያወራ እንደሆነ ሰሙ፡፡ ከዛም የማህበረሰቡን ታላላቅ ሰዎች ጠሩና የሚከተለውን ጠየቁ
‹‹እኛ አቡበክር እና ኡመርን እንድንሆንላችሁ ትፈልጋላችሁ?››
እነሱም እንዲህ አሉ ‹‹አዎን አንተም ኸሊፋ ነህ እነሱም ኸሊፋ ናቸው፡፡››
አብድልመሊክ ኢብን መርዋን እንዲህ አሉ ‹‹እናንተ በአቡበክር እና በኡመር ዘመን እንደነበሩ ሰዎች
ሁኑልን እኛም አቡበክር እና ኡመርን እንሆንላችኋለን››፡፡
የአብዱልመሊክ እና ህዝቦቻቸው ያደረጉት ንግግር እዚህ ላይ አበቃ፡፡ የአቡበክር እና የኡመር (ረድየላሁ አንሁም) አይነት መሬ የፈለገ መጀመሪያ በአቡበክር እና ኡመር ስር ይተዳደሩ የነበሩትን ሰሃባዎች፤ ታቢዕየች፤ እና አትበዓታቢንን ባህሪ፤ ተግባር ይላበስ፤ እነሱን ይምሰል፡፡ አላህ እንደነሱ ያድርገን፡፡

Post a Comment

0 Comments