Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

አባት ሞተሩን ሸጠው


አላሁ ሱብሃነሁ ወተዓላ ከእርሱ መብት ቀጥሎ የወላጆች ሃቅ እንዲጠበቅ አዟል፡፡ ነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ስለ ከባባድ ወንጀሎች ሲጠቅሱ በአላህ ላይ ከማጋራት ቀጥሎ ወላጆችን መበደል ነው ያሉት፡፡
ከዚህ በታች መጥቀስ የምፈልገው አንድ የማውቀው ወንድማችንን ትላንት አገኘሁት እና በወሪያችን መሃል ጭንቅላቴን የሚነካ ነገር ነገረኝ እናም ብዙ ወደ ኋላ እንድጓዝ ብሎም ይህቺን ፅሁፍ እንድፅፍ ሰበብ ሆነኝ፡፡
ወንድማችንን ስለ ነበረችው አንድ መንቀሳቀሻ ሞተር ሳይክል እንዴት ናት ብዬ ስጠይቀው ሸጫታለሁ አለኝ፡፡ ከዛም ምክንያቱንም ስጠይቀው ‹‹ልጁ ዩኒቨርስቲ ነጥብ አምጥቶ ገባ እና ላፕቶፕ ኮምፒውተር ግዛልኝ ሲለኝ፤ ሞተሬን ሸጬ ለሱ ኮምጲውተር ገዛሁለት›› አለ፡፡ ሱብሃነላህ ወላጅ ሁሌም ይህ ነው ተግባሩ፡፡
የአላህ ባርያዎች ሆይ! ከቤተሰብ የተለገሰንን ማንኛውንም ስጦታ በክብር ልንቀበል እና ልናመሰግናቸው እና ልናዝንላቸው ነው የሚገባን፡፡ ምክንያቱም ቤተሰብ ለልጁ የሆነን ነገር ሲገዛ ከራሳቸው በፊት ልጆቻቸውን አስቀድመው ‹‹እናንተ ትብሱ›› ብለው ነው የሚያደርጉት፡፡
ሰው እንደቤቱ እንጂ እንደጎረቤቱ አይኖርም፡፡ ስንቶች ናቸው ከቤተሰባቸው በሚደረግላቸው መስዋትነት ብዙም ደስተኛ ያልሆኑ? ምክንያቱም የሃብታም ልጅ የሚባሉትን እያዩ፡፡ የአላህ ባርያዎች ሆይ! ልብ እንበል ልክ በድህነታቸው ከአቅማቸው በላይ ለልጆቻቸው እንደሚያደርጉት ሁሉ አላህ አቅሙን ቢሰጣቸውም ላንተው/ላንቺው ነው ከራሳቸው በላይ የሚያደርጉት፡፡ በቤተሰቦቻችን ጉዳይ አላህን እንፍራ፡፡ መቼም የወላጅን ውለታ መመለስ የማይታሰብ ነገር ቢሆንም በነሱ ጉዳይ አላህ እና መልክተኛው ያዘዙንን አቅማችን በፈቀደው መጠን በመተግበር ከከለከሉን በቁርጥ በመራቅ አላህን እናምልክ፡፡
ኢንሻ አላህ በሰፊው በሌላ ትምህርት ስለ ወላጆች ሃቅ እንመለሳለን፡፡