Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ወገንተኝነት



ወገንተኝነት
ወገንተኝነት ማለት ፦ አንድን ነገር ከልክ በላይ መውደድ ከሡ የተሻለ ነገር ቢመጣለትም አለመቀበል ማለት ነው ። በተጨማሪም ሀቅም ላይ ትሁን ባጢል ላይ ያለችን አንድ ጀመአ በጭፍንተኝነት መከተል ፣ ስለ ዛች ጀመአ መሟገት ሌላም ሌላም ነገር ማድረግ ማለት ነው
ሠዎች ለተለያየ ነገር ወገንተኝነታቸውን ያሣያሉ ከነዛ ውስጥ…
1 ለሒዝብይ የሆነ ወገንተኝነት ፦ እንደ መንገድ ወይም አቋም አድርጎ የያዛትን ጀመአ በሀቁም በባጢሉም መርዳት እና መከተል የዛች ጀመአ መሪዎች ያሉትን በአጠቃላይ ከሸሪአው ጋር ቢጋጭም አምኖ መቀበል እንዲሁም ተሣስተዋል ብሎ በመረጃ ተደግፎ የተናገረውን አካል መጥፎ (የኢስላም ጠላት አድርጎ መሣል)
2 ቀውሚይ የሆነ ወገንተኝነት ፦ በሌላ ቋንቋ ዘረኝነት ማለት ነው
3 የመዝሀብ ወገንተኝነት ፦ ይህ ዛሬ ኡማው ለመለያየቱ ዋነኛ መንስኤ የሆነ ነገር ነው የማሊኪይ ተከታይ ነኝ የሻፊኢይ… እየተባለ እነሡ የሠሩትን የተናገሩትን በአጠቃላይ ከኢስላም ድንጋጌዎች ጋር ይጋጩም አይጋጩም መቀበል እና መተግበር በሚስመለሡ ግዜም የመዝሀባቸውን መሪ ተግባር እና ንግግር እንደ መረጃ ማቅረብ
4 ፊክርይ የሆነ ወገንተኝነት ፦ የሡን ሀሣብ ለተቀበሉ ሠዎች መወገን የሡን ሀሣብ ያልተከበሉትን እንደ ጠላት መቁጠር
ወገንተኛ እንድንሆን የሚያደርጉን ምክንያቶች ውስጥ
★ ራስን ከፍ ከፍ ማድረግ
★ አላዋቂነት
★ ግለሠቦችን ከልክ በላይ መውደድ
★ ከራስ ውጪ ማንንም አለመስማት አለመቀበልም
★ ዲንን በተሣሣተ መልኩ መረዳት እና ሌሎችም ይገኙበታል

Post a Comment

0 Comments