Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

‹‹ለሰውየው ከውሸት ይበቃዋል የሰማውን ሁሉ ማውራቱ›› ሰሂህ አል ጃሚ 4482


‹‹ለሰውየው ከውሸት ይበቃዋል የሰማውን ሁሉ ማውራቱ›› ሰሂህ አል ጃሚ 4482
ዌብ ሳይቶች ላይ የተፃፈ ሁሉ እውነት ነው ማለት አይደለም፡፡ ለምሳሌ በጣም የሚገርም ያየሁት ቅጥፈት ያውም አስገራሚ እንዲህ ይላል
‹‹ሳውዲ የሙሃመድን መቃብር ካለበት ቦታ ለማንቀሳቀስ ባቀረበችው ሃሳብ አስቸጋሪ ክፍፍል ውስጥ ልትገባ ትችላለች›› ይላል፡፡ ይህን የፃፈው አንድ የምዕራቡ አለም ዌብሳይት ነው፡፡
እስቲ ኡለማዎቿ ተጠይቀው ያሉትን እንስማ
አቡ አብድረህማን ጅብሪል አልኢስሃቅ ሸይኽ ፈውዛን አል መድኸሊን በ 12፡06AM ቀን 2 ማክሰኞ ሴፕቲንበር 2014 በ whatsapp እንዲህ ሲል ጠየቃቸው
‹‹አሰላሙ አለይኩም ወረህመቱላሂ ወበረካቱሁ
ኸይኽ ሳውዲ የነብዩን (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ቀብር ከቦታው ልታነሳው ነው የሚል ወሬ ሰምቼ ነበር፡፡ ይህ ወሬ እውነት ነውን? ባረከላሁ ፊክ፡፡ ››
ሸይኹ እየሳቁ ‹‹ውሸት ነው›› ብለው መለሱ፡፡
ይኸው ጥያቄ ለሸይኽ ኻሊድ አዛፊሪ በዋትስ አፕ በተመሳሳይ ሰዓት ተጠይቀው ‹‹እውነት አይደለም፤ ውሸት ነው›› ብለው መልስ ሰጡ፡፡
የአላህ ባርያዎች ሆይ! ስለ ሳውዲም ይሁን ስለ ሌላ ሙስሊም አገር የሚወሩ ውሸቶችን አታሰራጩ፡፡ ነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም)
‹‹ለሰውየው ከውሸት ይበቃዋል የሰማውን ሁሉ ማውራቱ›› ሰሂህ አል ጃሚ 4482
በሌላ ዘገባ ‹‹የሰማውን ሁሉ መናገሩ ለአንድ ሰው ከወንጀል ይበቃዋል›› አሰሂህ 2025
የአላህ ባርያዎች ሆይ! ይሄ ሃዲስ ወሬን ሳያጣራ ለሚበትን ሰው ከባድ ይሆንበታል፡፡ የሰማነውን ወሬ ከማስተላለፋችን በፊት እናጣራ፡፡