Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

የተክፊር ክፋት

የተክፊር ክፋት

አሠላሙ አለይኩም ወራህመቱላሒ ወበረካቱ

☞ ተክፊር ክፋቱ እጅግ የበዛ የሆነ እና በራስ ላይ በሚስከፈረውም በኡማውም ላይ ከባድ የሆነ ጥፋትን የሚጭር አጥፊ የሆነ ተግባር ነው ይህ ከመሆኑምጋር ግን በአንዳንድ ሙስሊም ሀገራት የተለመደ እና የሙስሊሙን ደም ለማፍሠስ ምክንያት እየሆነ የመጣ ጉዳይ ነው ። ባለንባትም ሀገር ላይ ይህንኑ ተግባር ስራቸው አድርገው የተያያዙት እንዳሉ የማይካድ ነገር ነው ።
☞ ዛሬ ላይ አንድን ሙስሊም ከኢስላም ለማባረር አንዳንድ ተራ ግለሠቦች ያሠመሩትን ቀይ መስመር መርገጥ የሚበቃበት ግዜ ላይ ደርሠናል ።
☞ ለአንድ የዲን ቅርንጫው ካለው ሀማስ ወይም ከልክ በላይ ማጥበቅ እየተነሣ እሡ ቦታ የሠጠው ነገር ቸል ያሉትን ሠዎች በአጠቃላይ (ሸሪአው የኩፍር ድንጋጌ ባይፈርድባቸውም) ከኢስላም በቀይ ካርድ ያባርራቸዋል ።
☞ አልያም ለአንድ አንጃ ከልክ ያለፈ ወገንተኝነት ያጠቃው ግለሠብ እሡ የሚከተለውን አንጃ የማይከተሉትን በጅምላ ወይም በተናጠል የሚያከፍር የበዛበት ወቅት ላይ ደርሠናል ።
☞ አንድን ነገር የሀላልነቱን እና የሀራምነቱን ብይን የመስጠት መብት የአላህ እንደሆነው ሁሉ የአንድን ግለሠብ ከኢስላም የመውጣት ፍርድም የአላህ መብት ነው ።ይህም ማለት ሸሪአው የግለሠቦች አይደለም! ማንም እንደፈለገ የፈለገውን ብይን የመስጠት መብት የለውም! የአንድን ሠው ከኢስላም መውጣት የሚመሠረተው አላህ ሡብሀነሁ ወተአላ በደነገገው ሸሪአ ላይ ነው
☞ ይህንን ባላሞላ መልኩ (ሸሪአውን ባላማከለ መልኩ) የሚሠጥ የተክፊር ብይን በአስከፋሪውም የኩፍር ብይን የተሠጠበትም በአጠቃላይ በኡማውም ላይ ከበድ ያለ ክስረትን ያስከስታል

☞ ይህንን⇡ አይነት ፍርድ ለሚሠጡ የተሣሣቱ ግለሠቦች ከነብዩ ሠለላሁ አለይሒ ወሠለም የተነገሩ በርካታ ዛቻ አዘል ሠነዶች መጥተዋል ከነዛ ውስጥ ለአብነት ያክል …

★ "አንደኛቹ ለወንድሙ "አንተ ከሀዲ " ቢለው ክህደቷ ወደ አንደኛቸው ትሆናለች እንደተባለው ካፊር ከሆነ እሺ ካልሆነ ግን ወደ ተናጋሪው ትመለሣለች
★ "አንድን ሠው ከሀዲ ወይ የአላህ ጠላት ያለ የተባለው ከሀዲ ወይም የአላህ ጠላት ካልሆነ ወደ ተናጋሪው ይመለሣል
★" አንድ ሠው አንድ ሠውን በፋሲቅነት ወይም በክህደት አይሠድበውም እንደተባለው አይሆንምም ወደ ተናጋሪው የተመለሠች ብትሆን እንጂ "
★ "አንድ ሙእሚንን በኩፍር መስደብ እንደ መግደል ነው "

☞ የአላህ ባርያ ሆይ! የአንድን ግለሠብ ሙስሊም መሆን ሸሪአ ባስቀመጠልን መነፅር አይተን መርምረን ካረጋገጥን ቡሀላ ይህ ሠው ኢስላም ነው እንደምነለው ሁሉ ካፊር ነው ለማለትም ሸሪአው ያስቀመጠውን መነፅር መጠቀም መመርመር እና እርግጠኛ መሆንም የግድ ነው! በጥርጣሬ ላይ ሆነን መፍረድ ግን የሚያስከትለውን ችግር ባለፉት ሀዲሦች ላይ አይተናል ።
☞ አንድ ተግባርን መፈፀም ከኢስላም እንደሚያስወጣ ሸሪአው ቢደነግግም በተገበረው ግለሠብ ላይ የክህደት ብይን ለመስጠት መሟላት ወይ መጣራት ያለባቸው ቅድመ ሁናቴዎች እንደሚከተለው ይቀርባሉ

① እውቀት፦ ግለሠቡ የሚሠራው ስራ ከኢስላም እንደሚያስወጣው ሊያውቅ ይገባል በሠራው ነገር ላይ እውቀት ከሌለውና የተገበረው ተግባር ምንም እንኳን ከኢስላም ቢያስወጣው ባለማወቁ ብቻ የኩፍር ብይን አይሠጥበትም ። አላህ እንዲህ ይላል « ከጥተኛው መንገድ #ከተገለፀለት_ቡሀላ መልእክተኛውን የሚጨቃጨቅ ከሙእሚኖች መንገድ ውጪ ሌላን መንገድ የሚከትል በዞረበት (ጥመት) እናዞረዋለን መመለሻነቷም የከፋች የሆነችዋን ጀሀነምም እናስገባዋለን » አኒሣእ
⇡ በዚህ መሠረት ነገሩ ግልፅ ያልሆነለት ሠው ምንም ቢሠራ የክህደት ብይን አይሠጥበትም

② ስህተት ፦ የሠራው ወይም የተናገረው ንግግር የሚያስከፍር ከመሆኑም ጋር ሆን ብሎ ነው ተሣስቶ የተናገረው የሚለው ነገር የኩፍር ብይን ከመሠጠቱ በፊት ሊፈተሽ ይገባል አላህ እንዲህ ይላል « ጌታችን ሆይ በረሣነው እና በተሣሣትነው አትያዘን» አልበቀራ በሀዲሠል ቁድስ እሺ እንዳለ ተዘግቧል

③ ግዳጅ ፦ አንድ ሠው ተገዶ በሠራው ወይም በተናገረው ቃል የኩፍር ብይን አይሠጥበትም አላህ እንዲህ ይላል « በአላህ ላይ ከእምነቱ ቡሀላ የካደ የተገደደ ሠው ሢቀር ልቡ በእምነት ላይ የተረጋጋች ስትሆን»

④እርግጠኛ ባልተሆነበት ነገር ፦ ሸሪአው በመከልከሉ ወይም መተግበሩ የኩፍር ደረጃ በማድረሡ ላይ እርግጠኛ እስካልተሆነ ድረስ (የኢስላም ሊቃውንቶች በተለያዩበት ጉዳይ) የካሀዲነትን ፍርድ መስጠት አግባቡ አይደለም

☞ እነዚህ አራቱ ቅድመ ሁኔታዎች ሊሟሉ የግድ ነው እነዚህን ግምት ውስጥ ያልከተተ የክህደት ብይን ግን
"አንደኛቹ ለወንድሙ "አንተ ከሀዲ " ቢለው ክህደቷ ወደ አንደኛቸው ትሆናለች እንደተባለው ካፊር ከሆነ እሺ ካልሆነ ግን ወደ ተናጋሪው ትመለሣለች " ይህንን ያስከትላል !!!

አላህ ተጠቃሚ ያድርገን!!!

Post a Comment

0 Comments