Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ሠላት

Away Bedru
 ሠላት

ሠላት ከኢስላም መሠረቶች መካከል ሁለተኛው መሠረት ነው

የሶላት ጊዜ ፣ ቦታ፣ ልብስና ዓይነቶች የሶላት ጊዜያት እያንዳንዱ ሶላት ጊዜው እንደደረስ ወይም በጊዜ ክልሉ ውስጥ መከናወን አለበት፡ ዕለታዊና ግዴታ (ፈርድ) የሆኑ አምስት ሰላቶች አሉ፡፡

★ የፈጅር ሶላት ፈጅር ወይም የሱብሂ ሶላት ጊዜ ጎህ ከቀደደ ጀምሮ ፀሐይ ወይም የፀሐይ ጮራ እስኪወጣ ድረስ ነው፡፡

★ የዙሁር (የቀትር) ሰላት የዙሁር ወይም የቀትር ሰላት ጊዜ ፀሐይ ከእኩለ ቀን በኋላ ከሰማይ እንብርት (ምዕራብ) ጋደል ስትል ይጀምርና የማንኛወም ነገር ጥላ መጠን የነገሩ መጠን ሲያክል ያበቃል፡፡ በእኩለ ቀን ፀሐይን ስንመለከት ልክ በጭንቅላታችን አቅጣጫ ሆና እናገኛታለን፡፡ በዚህን ጊዜ ጥላችን ከእግራችን ሥር ይሆናል፡፡ ነገር ግን ፀሐይ ወደ ምዕራብ ትንሽ ጋደል ስትል ጥላችንም ከእግራችን ሥር ወደ ምሥራቅ አቅጣጫ ወጣ ማለት ይጀምራል፡፡ የዙሁር ሶላት ጊዜም ልክ ከዚህ ጊዜ ይጀምራል፡፡ ከፀሐይቱ ማጋደል ጋር ከእግራችን ሥር ወደ ምሥራቅ ወጣ ያለው ጥላችን እያደገ ከራሳችን ቁመት ጋር እኩል ሲሆን የዙሁር ሰላት ወቅት ያከትማል፡፡ ጃቢር ኢብን ዐብዱላህ እንደተናገሩት፡ "መልአኩ ጅብሪል ነቢዩ ሙሐመድ (ሶ.ዐ.ወ) ዘንድ ከቀትር በኋላ መጠና «ዙሁር ስግድ» አላቸው፡፡ የአላህ መልዕክተኛም (ሶ.ዐ.ወ) ተነሱና ዙሁር ሰገዱ፡፡ ከዚያም መልአኩ ጅብሪል እንደገና ከቀትር በኋላ ቆየት ብሎ መጣና (ተነስ ዐሱር (ድህረ ቀትር) ሰላት ስገድ አላቸው፡፡ ከዚያም ነቢዩ ሙሐመድ (ሶ.ዐ.ወ) የማንኛውም ነገር ጥላ መጠን ከራሱ ቁመት ጋር እኩል በነበረበት ወቅት የዐሱርን ሶላት ሰገዱ፡፡ አሁንም በሚቀጥለው ቀን ነቢዩ ሙሐመድ (ሶ.ዐ.ወ) ተነሱና የማንኛውም ነገር የጥላው መጠን ከራሱ ቁመት ጋር እኩል በነበረት ጊዜ የዙሁር ሶላት ሰገዱ፡፡
ከዚያም ጅበሪል እንደገና በዐሱር ሰዓት (ከቀትር በኋላ) መጣና ተነስና የዐሱር ሶላት ስገድ አላቸው፡፡ ከዚያም እሳቸው ተነሱና የማንኛውም ነገር የጥላ ርዝመት የራሱን ርዝመት ሁለት እጥፍ ሆኖ በነበረት ወቅት የዐስር ሶላት ሰገዱ፡፡... ከዚያም ጅብሪል ለሁለት ተከታታይ ቀናት እየመጣ ከነቢዩ ሙሐመድ (ሶ.ዐ.ወ) ጋር ከሰገደ በኋላ የሁለቱ ሶላቶች ጊዚያት በነዚህ ሁለት ወቅቶች መካከል መሆኑን ተናገረ፡፡ (አሕመድ፣ ነሳኢይ፣ ቲርሚዚና ቡኻሪ ዘግበውታል) ሰላት የሶላት ጊዜ ፣ ቦታ፣ ልብስና ዓይነቶች ብዙ የሶላት መጻህፍት የማንኛውም ነገር ጥላ ርዝመት የራሱን ቁመት ሁለት ጊዜ ሲያጥፍ የዙሁር ሶላት ጊዜ የሚያከትምና የዐሱር ሶላት ጊዜ የሚጀምር መሆኑን ያትታሉ፡፡ ነገር ግን ይህ አባባል በመጀመሪያው ቀን መልአኩ ጅብሪል የማንኛውም ነገር ጥላ ከራሱ ጋር እኩል በነበረት ወቅት መጥቶ ነቢዩ ሙሐመድ (ሶ.ዐ.ወ) የዐሱር ሶላት እንዲሰግዱ የጠየቀበትና የሰገዱበት ወቅት መሆኑን የሚገልፀውን ከላይ የሰፈረወን ሐዲስ ይፃረራል፡፡ ይህም የዙሁር ሶላት ጊዜ መብቂያ ማለት መሆኑ ነው፡፡ ጊዜው ሳይደርስ ሶላት መስገድ የማይቻል መሆኑን በዚሁ አጋጣሚ ሳናስታውስ አናልፍም፡፡

★ የዐሱር (ድህረ ቀትር) ሶላት የዐሱር ሶላት ጊዜ የሚጀምረው የአንድ ነገር የፀሐይ ጥላ ርዝመት ከራሱ ቁመት ጋር እኩል በሚሆንበት ወቅት ሲሆን የሚያበቃውም ፀሐይ ልትጠልቅ ስትል ነው፡፡ የዐሱር ሶላት ፀሐይቱ ለመጥለቅ ስትቃረብ መስገድ የሚቻል ቢሆንም ቅሉ ይህችን ሶላት እስከዚያ ጊዜ ድረስ ማጓተት የመናፍቃን ባህሪ መሆኑን ነቢዩ (ሶ.ዐ.ወ) ጠቁመዋል፡፡

★ የመግሪብ ሶላት የመግሪብ ሶላት ጊዜ ፀሐይቱ ልክ እንደጠለቀች ይጀምርና ቀዩ ወጋገን ሲጠፍ ያከትማል፡፡

★ የዒሻ ሶላት የዒሻ ወይም የምሽት ሶላት ጊዜ ቀዩ ውጋገን እንደጠፋ ይጀምርና ከእኩለ ሌሊት ትንሽ አስቀድሞ ያበቃል፡፡ ይህን ሶላት ጐህ እስከሚቀድ ድረስ መስገድ ቢቻልም ከእኩለ ሌሊት በፊት መስገዱ የተመረጠ ነው፡፡

✔ ሡና ሠላቶች

ከእያንዳንዱ ፈርድ ሠላት ቡሀላ እገዳ ከመጣባቸው ሠላቶች ውጪ ሡና ሠላት አለ እነሡም ጠበቅ ያለ ሡና በመባል የተነጠሉም አሉ እነሡም ከሡብሒ በፊት 2 በዙሁር በፊት 4 ከዙሁር ቡሀላ 2 ከመግሪብ ቡሀላ 2 ከኢሻ ቡሀላ 2 በጥቅሉ አስራ ሁለት ሡናዎች ይሆናሉ

✔ ሶላት የተከለከለባቸው ጊዜያት

ዑቅባህ ኢብን ዓምር እንዳመለከቱት፡- «ሶላት እንዳንሰግድ ወይም ሙታንን እንዳንቀብር በአላህ መልዕክተኛ (ሶ.ዐ.ወ) የተከለከልንባቸው ሶስት ጊዜያት አሉ፡፡ እነርሱም፡- - ፀሐይ መውጣት ከጀመረች ጀምሮ ሙሉ በሙሉ እስክትወጣ ድረስ፣ - ፀሐይ ጨረር አናት ላይ ስትሆን ጀምሮ ወደ ምዕራብ እስክታገድል ድረስ፣ - ፀሀይ መጥለቅ ስትቃረብ ጀምሮ እስክትጠልቅ ድረስ ናቸው» (ሙስሊም ዘግበውታል፡፡)