Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

"እኔን ነው የሚመለከተው"

"እኔን ነው የሚመለከተው"

አሠላሙ አለይኩም ወራህመቱላሒ ወበረካቱ

☞ ዛሬ ስለ አንድ ወሣኝ ጉዳይ ላወራቹ ነው እሡም በ facebook ግድግዳ ላይ የሚለቀቁ በርካታ ጠቃሚ ትምህርት አዘል የሆኑ ፅሁፎችን አንባቢያንን ይመለከታል

☞ የሚፃፉትን ጠቃሚ የሆኑ ትምህርቶች በምናነብበት ግዜ የተፃፈው ፅሁፍ እኔን ነው የሚመለከተው ብሎ በተሠጠው ትምህርት መሠረት እራስን ከማረም እና ከስህተቱ ከመመለስ ይልቅ የሚፃፉትን ፅሁፎች ሌላ ስያሜ ሰጥቶ መሸሽ ፣ ወይም እሡን ሣይሆን ሌላ ሠዎች እንደተፈለጉበት አድርጎ በማሠብ በሚፃፉት ነገሮች ምንም ተጠቃሚ ሣይሆን ማለፍ ።

☞ የአላህ ባርያ ሆይ! እነ ኡመርን አስታውስ ስለ ሙናፊቅ ሢወራ በልባቸው ስር ኒፋቅ ያለ ያክል ይጨናነቁ ነበር እኔና አንተ ግን! በልባችን ስር ስላለው ወንጀል እየተነገረን እንኳን ዝንብ ያረፈብን እስከማይመስለን ድረስ ድርቅ ብለን ሠምተን እንዳልሠማን አይተን እንዳላየን እናልፋለን ከዚህ በላይ የልብ መድረቅ አለን?

★ የአላህ ባርያ ሆይ! የሚነገረው የሚፃፈው እኔን ነው የሚመለከተው ብለን እናንብብ እናድምጥ በዚህ መሠረት ነው ያነበብነውም ያደመጥነውም ፍሬ ሊያፈራ የሚችለው አላህ ይወፍቀን

Post a Comment

0 Comments