Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ኒፋቅ

ኒፋቅ
ንፍቅና ማለት ከላይ እስልምና እና መልካም ነገርን ለሰዎች እያሳዩ በድብቅ በክህደት ማመንና ተንኮልን መያዝ ነው።
ንፍቅና ሁለት አይነት ሲሆን ትልቁ ከኢስላም የሚያስወጣ አላህ ግለሰቡን በታችኛው የጀሀነም አዝቅት የሚቀጣበት አጥፊ ወንጀል ሲሆን ትንሹ ግን ከኢስላም ባያስወጣም ወደ ትልቁ ንፍቅና የሚያዳርስ አደገኛ ወንጀል ነው።
የትልቁ ኒፋቅ(እምነታዊ ንፍቅና) አይነቶች
1. ነቢዩን(ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም) ማስተባበል
2. ነቢዩ(ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም) ይዘው ያመጡትን በከፊሉ ማስተባበል
3. ነቢዩን(ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም) መጥላት
4. ነቢዩ(ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም) ይዘው ከመጡት ከፊሉን መጥላት
5. በኢስላም ዝቅ ማለት መደሰት
6. የኢስላም የበላይነትን መጥላት ናቸው።
ትንሹ ኒፋቅ ደግሞ በሚከተሉት ተግባራዊ የንፍቅና ስራዎች የሚከሰት ነው
1. የታመኑ ግዜ መካድ
2. ሲናገሩ መዋሸት
3. ቃል ገብቶ ማፍረስ
4. ቀጠሮን ማዛባት
5. ሲከራከር ማመፅ(ማወናበድ)
እነዚህ የትንሹ ኒፋቅ አይነቶች የተገኙበት ሰው ኢማንም ኒፋቅም የሚሰባሰቡበት ሲሆን ሁሉም የትንሹ ኒፋቅ አይነቶች በአንድነት ከተገኙበት ግን ጥርት ያለ ሙናፊቅ ይሆናል።
======================
*ወንድሞች ማንም ይሁን ማን ሙስሊም ወንድማችንን ሙናፊቅ ብለን ከምስደብ እንቆጠብ፤ እርሱ ያ የሰደብነው ሰው ሙናፊቅ ካልሆነ ነገርየው የሚመለሰው ወደራሳችን ነውና!
አላህ ከሁሉም የኒፋቅ አይነት ነጃ ይበለን!

Post a Comment

0 Comments