Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ስለ አንድነት የማያወላዳ መስፈር


ስለ አንድነት የማያወላዳ መስፈርት

የኡማው አንድነት አንድ አላህን አንድ ብቻ አድርጎ በመገዛት ነው፡፡ የአላህን ብቸኛ እውነተኛ ተመላኪነት፤ ከእርሱ ውጭ የሚመለኩት ውድቅ መሆናቸውን በልብ አምኖ፤ በምላስ መስክሮ፤ በሰውነት ተግብሮ አንድ አላህን ብቻ የእውነት አንድ አድርጎ በማምለክ አንድ መሆን ይቻላል፡፡

ምክንያቱም ግልፅ ነው አላህ እሱ አንድ ነው፡፡ አንድነቱን ብቸኛ ጌትነቱን፤ ብቸኛ ተመላኪነቱን፤ ለእርሱ ምርጥ ስም እና ባህሪያት እንዳሉት ሁላችንም የመሰከርን፤ የተገበርን ጊዜ እሱም አንድ ያደርገናል፡፡ 

አለበለዚያ ከአላህ ውጭ ላለ (መላኢካም፤ ነብይም፤ ጂን፤ ፍጡራንን..) አካል ለአላህ ብቻ የሚሰጡትን የአምልኮ ክፍሎች ሁሉንም ይሁን አንዱን አሳልፎ እየሰጡ ‹‹አንድ ነን›› ብሎ ማውራቱም ነውር ነው፤ አላህም በፍፁም አንድ አያደርገንም፡፡

አላህ ሆይ! እውነተኛ አንድነትን ለግሰን ያንተን አንድነት ያረጋገጡ፤ ካንተ ውጭ ባሉት ተመላኪነት ሁሉ የካዱ ህዝቦች አድርገን፤ በዚሁ ላይ አኑረህ በዚሁ ግደለን፡፡