Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ሰላማዊ ሰልፍ በኢስላም ዕይታ

ተቃውሞ ሰልፍ ሃራም ነው፤ ከእስልምና ዕምነት አይደለም፤ ከከሃዲያን(ካፊሮች) ዕምነት እንጂ፤ በጭራሽ ከእስልምና ዕምነት አይደለም፡፡ (ተቃውሞ ሰልፍ) ለቀውስ፣ ለብጥብጥ፣ ያለ ልክ ዕልቂት ምክኒያት ነው፡፡ ተቃውሞ ሰልፍ በካፊር በህጉ ወይንም በመንግስቱ የተፈቀደ ቢሆንም ነገር ግን በኢስላም በጭራሽ የተፈቀደ አይደለም፡፡
እኛ ሙስሊሞች ነን፤ ለአላህ ምስጋና ይገባው፤ በሃገሩ(ህግ) የተፈቀደ ቢሆንም (ተቃውሞ ሰልፍ) ዲናችን(ዕምነታችን) ግን ይከለክላል፡፡ እኛ ሙስሊሞች ነን ከአላህ ኪታብ ነው እንጂ(መመሪያችን) የምንወስደው ከፍራንክ ህግ ወይንም ከሌላ አይደለም፡፡
አላህን ፍሩ የአላህ በሮች..! በዚህ ጉዳይ ላይ አስቡበት..! ልጆቹን፣ ሚስቶቹን፣ ሴት ልጆቻችሁን ከዚህ እርኩስ ማሽን(ኢንተርኔት) ከሚያዩትና ከሚያነቡት ነገር(እንዳይታለሉ) ምከሯቸው፡፡ በአሁኑ ሰዐት በየሙስሊም ቤቱ ልክ እንደ ጣዖት ዕኩይን እያሰራጨ ፕሮፓጋንዳና አሉባልታን እየነዛ ሙስሊሞችን ቤታቸው ውስጥ እንኳን በፍርሃት እንዲጨነቁ፤ እናም እነዚህ ቤቶች ላይ አለመረጋጋት እንዲመጣ እየመጣ ነው፡፡ ስለዚህም አላህን ፍሩ የአላህ ባሪያዎች ሆይ፡፡
“ጠበኞችም በነበራችሁ ጊዜ በናንተ ላይ (የዋለውን) የአላህን ፀጋ አስታውሱ፤ በልቦቻችሁም መካከል አስማማ፤ በፀጋውም ወንድማማቾች ሆናችሁ፤ በእሳት ጉድጓድ አፋፍም ላይ ነበራችሁ፤ ከእርስዋም አዳናችሁ” አል-ዒምራን-103
ዕወቁ ከንግግሮች ሁሉ በላጩ የአላህ መፅሀፍ(ቁርዓን) ነው፤ ከመመሪያዎች ሁሉ በላጩ(ቅናቻ) መመሪያ የሙሀመድ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም መመሪያ(መንገድ) ነው፤ ከመጥፎ ድርጊቶች ሁሉ መጥፎው አዲስ(ዲን ላይ) የተፈጠሩ ፈጠራዎች ናቸው፤ ሁሉም ቢድዐ ጥመት ነው፤ ሁሉም ጥመት የእሳት ነው፡፡
ለበለጠ መረጃ ድመምፁን ያዳምጡ
https://www.youtube.com/watch?v=t2Zd4M9T3o8

Post a Comment

0 Comments