Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ድምፃችን ይሰማ

ምስጋና ለዓለማቱ ጌታ ይሁን፤ ውዳሴ ሰላምታ በነቢያችን ላይ ይሁን
አሰላሙ ዓለይኩም
ይድረስ ለማንነቱ ለማይታወቀው “” እና ላልነቃው ሙስሊም ወገኔ
ከዛ በፊት ግን ማሳሰብያ። ያልተፃፈን ነገር አታንብቡ፣ የተፃፈውን አገናዝቡ፣ ከምትሳደቡ መረጃዊ ሁኑ። አለበለዚያ ኮሜንታችሁ ለመሰረዝነት ይዳረጋል።
__________________________________________________________
አላህ ሱብሓነሁ ወተዓላ በየጊዜው እና በየቦታው ሰዎችን ለመፈተን ፈተና ይልክባቸዋል። እንደዛውም ለዚህ ፈተና መገርሰሻ የሚሆኑ መፍትሄዎችን ይልካል (ያሳያል)። ረሱልም ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም “አላህ አንድንም በሽታ አያወርድም ለሷ መድሃኒት ቢያወርድላት እንጂ” ብለዋል። በፈተና ጊዜ ደሞ ሰዎች እንደመፍትሄ ብለው የሚያመጥዋቸው ነገራቶች አሉ። ነገር ግን እነዚህ አካሄዶች ከሃቅ ጋር ሊገጥሙም ላይገጥሙም ይችላሉ። ስሜት ምንም ዓይነት ቦታ የለውም በዚህ ሰዓት። አንዳንድ ሰዎች ነገሩ “የትም ፍጭው ዱቄቱን አምጭው” ይመስላቸዋል። ነገር ግን “የአለማወቅ መድሃኒቱ መጠየቅ ነው?!” ብለዋል ረሱል ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም። መጠየቅ ሲባል ግን እናንተው የፈለጋችሁትን የሚመልስላችሁን ሼኽ ማፈላለግ አይደለም። ይህችማ ስሜት ናት።
እውነት እንናገር ከተባለ “ተቃውሞ ይቻላል” የሚሉ ዓሊሞችን ነው ሰዉ እያፈላለገ ያለው። ነገር ግን በጣም የሚያሳዝነው “አይቻልም”ን አቋሜ ብሎ የያዘን ሰው እንደ ጠላት አርጎ መያዙ ነው። እሺ ይያዝ፤ ግን ሌሎችንም አይጠሉም??? ለምሳሌ እኔ “አካሄዱ ልክ አይደለም” ብል “አሕባሽ” እና “የመንግስት ካድሬ” ብሎም “ካፊር” የሚል ታፔላ ይለጠፍብኛል። እነ ሓሰን ታጁ፣ ዶ/ር ኢድሪስ፣ ሓሚድ ሙሳ፣ “ሙፍቲ” ዑመር ገነቴ እና የመሳሰሉትም እኮ ለዚህች ታፔላ ሰለባ መሆን ነበረባቸው። ነገሩ ግን እንደዛ አይደለምም አልሆነምም። አልሓምዱሊላህ የአሕባሽ እምነት ከኔጋ አራምባና ቆቦ ነው። አላህ ከዓርሽ በላይ እንደሆነ፣ በሙታን እንደማልታገዝ፣ መልካም ቢድዓ እንደሌለ ... ወዘተ እምነቴ ነው፣ አላህ በዚሁ ያፅናኝ። እነዛን ግን መዝኗቸው እስቲ። ማን ምን መባል እንደነበረበት ልባችሁ ያውቀዋል።
ወደ “ድምፃቸው...” ልምጣማ።
የ “ድምፃችን ይሰማ” አካሄድ “ሰዉን አስቀጥቅጪው ድሉን አምጪው” ሁኗል። ይገርማል። ማንነታቸው ያልታወቀ የዚህ ፔጅ መሪዎች ለማጋለጥና ሰዉን ለማንቃት ሲጣር “ካድሬ” ትባላለህ። “መሪው ሙስሊም ይሁን ካፊር የማይታወቅ ነገር እንዴት አሜን ብላችሁ ትነዳላችሁ” ስትል “ለደህንነት ሲባል ነው” ትባላለህ። እሺ እስቲ በአላህ ይሁንባችሁ ተመልከቱ፤ የሙስሊሙ ደህንነት አያሳስብም??? ዒድ በመጣ ቁጥር ሰዉ ከመደሰት ይልቅ ተጨንቆ ተረብሾ እያለቀሰ ያሳልፍ??? ሲጀመር የአካሄድ መዘንጋት በጣም ይስተዋላል። በጥቂቱ እንኳ ስለ ሴቶች እንመልከት።
ሴት ልጅ ቤቷ ውስጥ እንድትረጋ የታዘዘች ፍጡር ናት። ግዴታ ሰላት እንኳ ቤቷ ይበልጥላታል። ሰላት ውስጥ ስሕተት ቢከሰት እንኳ ታጨብጭብ ተብላለች። አሁን ግን “ጂሃድ” እና “ለዲን እኮ ነው” በሚል መፈክር ከቤት አስወጥተው ለአደጋ ሰለባ አረጓት።
عائشةَ رضيَ اللهُ عنها سألت رسولَ اللهِ صلَّى اللهُ عليه وسلَّمَ : هل على النساءِ جهادٌ ؟ قال : نعم جهادٌ لا قتالَ فيه : الحجُّوالعمرةُ
ዓኢሻ ረድየላሁ ዓንሃ በዘገበችው፤ ነብዩ ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለምን ጠየቀቻቸው፦ “ለሴቶች ጂሃድ አለባቸውን?” ነብዩም ሰለላሁ ዓላይሂ ወሰም፡ “አዎን ግድያ የለለብት፤ ሓጅና ዑምራ” አሏት።
ሌላው ደሞ ዓኢሻ “የውመል ጀመል” በተባለው ውግያ ተሳትፋ ነበረ። ከዛም ቤት ስትመለስ “وقرن في بيوتكن” “ቤታችሁ ውስጥ እርጉ” የሚለውን አንቀፅ ስታነብ ሂጃቧ እስኪበሰብስ አለቀሰች። አሁን ግን “ድምፃችን ይሰማ” ውጭ ሃገር የድሎት ኑሮ እየኖሩ፣ እዚህም ቢሆኑ የጁምዓ ተቃውሞ ውስጥ ይሳተፉ አይሳተፉ የማይታወቅ፣ “ካሜራችሁን እንዳትረሱ” እያለ የራሱን ካሜራ ቤት አስቀምጦ ሴቶችን አስቀጠቀጠ። 18 የፖሊስ ካምፕ ውስጥ የተከሰተውን ጉዳጉድ ነው የተሰማው። ኒቃብ ለባሾችን አራቁተው “እንዲዚህ አያምርባችሁም” እያሉ ይሳለቁባቸው ነበረ። ህዝቤ ግን አሁንም አልነቃም። እነሱ ተመችቷቸው ሰውን ያስቀጠቅጣሉ። ወላሂ የዓርብ ቅጥቀጣ ቀን ሰዉ ሲጨፈጨፍ አንዱ (ስሙ ይቆይልኝ) ቆንጅዬ መኪናዉን ይዞ ቦሌ አካባቢ መኪናዉን ነዳጅ ሲያስሞላ ነበረ። “ለዲን ብሎ መሞት ሸሂድነት ነው” ሲሉ እንዳልነበረ እነሱ ግን አጋፍጠው ላሽ አሉ። ምነው ሸሂድነት አይወድላቸውም ወይስ ሸሂድ መሆናቸውን ታምራት ገለታ ተነበየላቸው??? ዓጂብ!!!
ዲን የተባለ ነገር በሙሉ ኢኽላስ (ለአላህ ማጥራት) እና ሙታበዓ (ረሱልን ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም መከተል) ግድ ይላል። አንድን ነገር ለማሳካት ደሞ ሓላል መንገዶችን መጠቀም ግድ ይላል።
ለምሳሌ:
መስጂድ ማሰራት ዒባዳ ነው። ነገር ግን በሓራም ብር መስጂድ ማሰራት አይቻልም። ምክንያቱም የአንድን ነገር መዳረሻው መሆን ያለበት ሓላል ነገር ብቻ ነው መሆን ያለበት። “الوسائل لها أحكام المقاصد” ማለትም “መዳረሻዎች የግቡን ብይን ነው የሚይዙት”። ነገር ግን የጥመት መሪዎች “الغاية تبرر الوسيلة” ይላሉ ማለትም “ግቢቱ መዳረሻዎችን የተፈቀዱ ታደርጋለች”። ይህ ደሞ ውድቅ ነው። እንደዛ ቢሆን ኖሮማ ረሱል ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም ሰሓባዎች ከመስለማቸው በፊት ሽርክ እየሰሩ በጠሯቸው ነበር። ወይም አሁን እንደሚባለው ተውኔት እየተወኑ ባስተመሯቸው ነበር። ግን አይደለም። ወደ ሲራቸው (ሂወት ታሪካቸው) ተመለሱ። አሁንም ልክ እንደዛው ዲንን የበላይ ለማድረግ ከተፈለገ ሓላል የሆኑ መንገዶችን መጠቀም። ሴቶችን አስወጥቶ አደባባይ ላይ ማስጮህ ግን ሓላል አይደለም ብሎም ቢድዓ ነው። አይደለም ከተባለ መረጃችሁን።
ሌላው ደሞ ስለሙባየዓ (ቃል መገባባት) ማለት ምፈልገው ነገር አለኝ። ሙባየዓ መግባት ይቻላል ወይስ አይቻልም እሱ ሌላ አጀንዳ ነው። ግን ይቻላል ቢባል ራሱ ለማይታወቅ አካል እንዴት ሙባየዓ ይገባልን??? ወገኔ ሆይ እስቲ ባንተና በጌታህ መሃከል የሚቀር ጥያቄ ልጠይቅህ። በዚህ ግብግብ መሃል ለ“ዲንህ” በሚል አላግባብ አካሄድ ውስጥ ሞተህ አላህ ፊት ላለመወቀስህ ምን ያህል እርግጠኛ ነህ???
አንዳንዶንቹ ደሞ “ሃይማኖታችን ሊሰልበን እኮ ነው አሕባሽ የመጣው” ይለሃል። ከሱ በፊት ሱፊው እና ተብሊጉ በኡማው ሲያላግጥ የት ነበረ ይህ መፈክራችሁ??? አሕባሽ እና እነኛህ ምንድነው ልዩነታቸው??? እምነታቸው (ዓቂዳቸው) ያው ነው። ኧረ እነሱ ናቸው “ሰምተናል ታዘናል” ብለው የተቀበሏቸው።
የሆነው ሁኗል። የወደፊቱን ግን ማስተካከል ይቻላል። ወደ ቁርአን እና ሓዲስ በሰለፎቻችን አረዳድ እንመለስ። ካልሆነ ግን ለፍቶ መና ነው የሚሆነው ነገሩ።
በመጨረሻም ታች ባለው ውይይት ልጨርስ ፅሑፌን ልቋጭ። ከታች ያለውን ነገር እዩና ምን ያህል ለሙስሊሙ እንደማያስቡ ተመልከቱ። ያው መጨረሻ ላይ block ተደረግኩ። ትንሽ ረዘም ቢልም ታገሳችሁ ጨርሱት።
__________________________________________________________
ፊዳከ አቢ ወኡሚ ያረሱለላ with አልቁርአኑ መንሀጁ ሀያቲ and 4 others
10 hrs •
“ ደሰ አላቸው “ ፣ በጣም ደስ አለን
በአዲስ አበባ ከተማ ብቻ ለአራተኛ ጊዜ የመንግስት ሀይላት በንፁሀን ሙስሊሞች ላይ አስቃቂ እርምጃ ወስደዋል ፡፡
ይህን ተከትሎ የተለያዩ አካላት ስሜታቸውን ገልፀዋል ፡፡
አህባሾች፣የመንግስት ካድሬዎችና ያለጥሎሽ የተጋቧቸው መድኸሊዬች (የተውና ሂድ ባልደረቦች )የተጠቀሟቸው ቃላት ይለያይ እንጂ ስሜታቸውን የገለፁት በተመሳሳይ መንገድ ነው ፡፡
ሁሉም ደስ ብሏቸዋል ፡፡
ካድሬውና አህባሹ በህዝብ ሚዲያ መንግስት የወሰደው እርምጃ ተገቢ ነው ሲሉ መድኸሊዮች ደግሞ በሶሻል ሚዲያ እንደውም ሲያንሳችሁ ነው እያሉ ነው ፡፡
ምናልባትም ሲሲ ለወሰደው እርምጃ ፎቶውን ሰቅለው እንደዞሩት ሁሉ አሁንም የዶ/ር ሸፈራውን ፎቶ እያሠሩ ይሆናል ፡፡
መድኸልዮች ህዝበ ሙስሊሙ ጠግቦ ፣ሁከት ናፍቆትና ዱላ አምሮት የተደበደበ ይመስል የሰብዐዊነት እንጥፍጣፊ በሌለው ደረቅ ቃል ደስታቸውን እየገለፁ ነው ፡፡
ነብዩላህ ኢብራሂም (ዐ›ሠ.)ብቻቸውን ሁነው ጣኦታትን በመሰበራቸው እሳት ተከተዋል ፡፡ይሄንንም አርፈው ለምን አይቀመጡም ነበር ትሉት ይሆን ? ረሱሉል አሚን (ሰ›ዐ›ወ.)የጣዒፍ ህዝብን ወደ ኢስላም ሊጠሯቸው በወጡበት ጫማቸው በደም እስኪነከር ተደብድበዋል ፡፡
ይሄንንስ እዛ ድረስ ምን አስኬዳቸው ትሉ ይሆን ? ያህያ ታርደዋል ፡፡ ዘከርያ በመጋዝ ተሰንጥቀዋል ፡፡ ይህኛውንስ ምን ትሉት ይሆን ? አላሁል ሙስተዐን ፡፡
ጎዳናው እሾክ በእሾክ እንደሆነ እናውቀዋለን ፡፡ ሰለፎቻችንም አልፈውበታል ፡፡ለኛም አዲስ አይደለም ፡፡በመደብደባችን እናንተ ከተደሰታችሁት በላይ ወላሂ እኛም ደስተኛ ነን ፡፡
ለኢስላም ብሎ መደብደብ ጥቂት አላህ የመረጣቸው እንጂ አያገኙትም ፡፡የፈሰሰው ደማችን አላህ ዘንድ እጅግ ውዱ ደም ነው ፡፡
ዛሬ እንደፈሰሰው ሁሉ ነገም ከነገ ወዲያም ዘወትርም እንዲፈስ ምኞታችን ነው ፡፡ አዎ ዛሬ ደማችን በመፍሰሱ አህባሹም፣ካድሬውም፣ታጣቂ ውም ፣መድኸሊዩም ደስ አላቸው ፡፡
እኛም በመደብደባችን በጣም ደስ አለን ፡፡ ልዩነት ነገ አላህ ፊት ስንቀርብ የምንሰጠው ምላሽ ነው ፡፡
አህባሽ፡- ሙስሊሞችን አስደብድበናል ደስ ብሎናል
መንግስትና ግብረ አበረቹ ፡- ሙስሞችን ደብድበናል ደስ ብሎናል
መድኸሊዮች ፡- ሙስሊሞች ተደብድበዋልና ደስ ብሎናል
እኛ ፡-ለዲንህ ብለን ደማችን ፈሷልና ደስ ብሎናል ፡፡
LikeLike • • Share
አልቁርአኑ መንሀጁ ሀያቲ and 7 others like this.
3 shares
ኢክራሙ ላህ ኢክራሙላህ አልሀምዱሊላህ ያረብ እኔም ይሄ እድል እንዲደርሰኝ ምኞቴ ነው
10 hrs • Like • 2
Alif Laam Meem እኔ አንድ ነገር ልል የምፈልገው በሴቶች ላይ በደረሰው ጥቃት የተለያዩ ፅሁፎች ተለቀዋል ከተለቀቁት ሴቶችን ለተሳትፎ ብለው ባይወጡ ይመረጣል ይህን ያለው ግን ትክክለኛ ኢስላም አይመስለኝም እኔ በራሴ አልደግፈውም ምክኒያቱም ሴቶች መብታቸውን ለማስከበር የበታችነት ሊሰማቸው አይገባም ይህ የደረስባችሁ ኒቃብ ማስጣል እና ጅልባብ አውልቃችሁ ስለሄዳችሁ የእናንተን አይቶ ሌላውእንድዳከም ነው ስለ ኢስላ...See More
7 hrs • Like • 2
Ibnu Mohammed እኔ አንተ መድኸልይ ከምትላቸው ጀምዓ ውሥጥ ነኝ:
ነገር ግን ሙሥሊም ወንድምና እህቶቼ በመደብደባቸው :ክብርአቸው በመነካቱ በጣም አዝኛለው በጣም ተከፍቻለው
1 hr • Like
Ibnu Mohammed የፈሠሠው ደም አላህ ዘንድ ከደምዎች ሁሉ ውድ ደም ነው
1 hr • Like
Abu Meryem Sami AlJeberti "ነብዩላህ ኢብራሂም (ዐ›ሠ.)ብቻቸውን ሁነው ጣኦታትን በመሰበራቸው እሳት ተከተዋል ፡፡ይሄንንም አርፈው ለምን አይቀመጡም ነበር ትሉት ይሆን ? ረሱሉል አሚን (ሰ›ዐ›ወ.)የጣዒፍ ህዝብን ወደ ኢስላም ሊጠሯቸው በወጡበት ጫማቸው በደም እስኪነከር ተደብድበዋል ፡፡
ይሄንንስ እዛ ድረስ ምን አስኬዳቸው ትሉ ይሆን ? ያህያ ታርደዋል ፡፡ ዘከርያ በመጋዝ ተሰንጥቀዋል ፡፡ ይህኛውንስ ምን ትሉት ይሆን ? አላሁል ሙስተዐን ፡፡
ጎዳናው እሾክ በእሾክ እንደሆነ እናውቀዋለን ፡፡ ሰለፎቻችንም አልፈውበታል ፡፡"
lalshiw, Inesu iko Allah yazezachen akahed slehedu new. Indenesu bitihedu noroma mngna yamare neber. Inesu akahedachew hulu halal nebere, indenante haram negeratochn yamakele alneberem. Lemsale Set lej kebet aswetito masdebdeb mn ybalal??? Set lj iko aydelem badebabay weta chuha litidebedeb qerto selatwa ybeltlatal yetebalew betwa new. Muhammed Awel Salih inkwa "Imesgejash lay rgi" blwal, bemigebachuh qwanqwa. Allahm "Betachuh wst Rgu" blwal. Gn Misema yelem. Selat sisasat inkwan machebcheb inji " Subhanellah " tbel mech tebale???!!! Set lj weta mitilafa bihon noroma selefochachin beqedemun neber. Aisha redyellahu anha inkwan Yezane "يوم الجمل" lay tewagta ketemelesech behwala "وقرن في بيوتكن" milewn stqera hijabwa iskebesebis dres aleqesech.
50 mins • Like • 1
Abu Meryem Sami AlJeberti "ለኢስላም ብሎ መደብደብ ጥቂት አላህ የመረጣቸው እንጂ አያገኙትም ፡፡የፈሰሰው ደማችን አላህ ዘንድ እጅግ ውዱ ደም ነው ፡፡" anjet lemeblat atmokri be Allah. Le Islam blo megedel kbr indehone manim yaqewal. Gn izi lay and netb ayche nebere "የፈሰሰው ደማችን አላህ ዘንድ እጅግ ውዱ ደም ነው ፡፡" bleshal. Indet aweqsh be Allah??? Masrejashin isti.
46 mins • Like • 1
Num Ahlam Abu Meryem Sami AlJeberti jezakelah hayren eski nigerlgn
42 mins • Unlike • 1
Abu Meryem Sami AlJeberti Wellahi demo mnm des aylim muslim simeta ina siqeteqet, miyasaznew neger binor Ye muslimu alemenqat sayhon "Amir" tebyewoch yedil nuro lay teqemtew sewun maschefchefachew new. Inesu iwn Jum3a qen neberu??? Anchi rasishs nebersh??? Wellahi sewu siqeteqet andu Gleseb Suzuki Grand mekinawun yzo bole nedaj simola nebere. Agbab new be Allah??? Sewun agafto lash malet???
41 mins • Like • 1
Alif Laam Meem የኢትዮጽያ ሙስሊሞች አብሺሩ በርቱ ድል ያለ አዛብ አይመጣም እንኮን እኛ ሙስሊሞች ለኢስላም ብለን እንግልት የደረስብን መሀይሙ ወያኔ ጫካ ገብቶ ሰወችን በጥይት ፈጅቶ ስልጣን የያዘው እኛም በስላማዊ ትግላችን አንድ ቀን ድል እናደርጋለን በዱአ በርቱ ማንኛውም ሀይል ለሚያደርስብን ችግር ስበብ ይሆናል እንጅ ሙስሊም ነስር ማምጣቱ መቸም አይቀርም ኢንሻ አላህ
40 mins • Like
አልቁርአኑ መንሀጁ ሀያቲ Wandema lame daraqe mugete temogetalake egnako dinachen sela tadafaranawe menetagalawe rasule endatanagaru zagabiwen balasetawese allah wede yahonute tabetawoche andu ba allah manegade laye tagelake yamifaseke dame naw
34 mins • Like
Num Ahlam Alif Laam Meem
Num Ahlam's photo.
34 mins • Like
Abu Meryem Sami AlJeberti አልቁርአኑ መንሀጁ ሀያቲ
ye ፊዳከ አቢ ወኡሚ ያረሱለላ tewekay kehonk letsafkut hula mels sit. Meselegn ina alastawisim mels ayhonm. Demom and account satihonu atqerum. Honachihum alhonachihum aygermim, mifelegewm isu aydelem. Mels new mifelegew.
28 mins • Like
አልቁርአኑ መንሀጁ ሀያቲ 9:16 እነዚያን ከናንተ ውስጥ የታገሉትንና ከአላህም ከመልክተኛውም ከምእምናንም ሌላ ምስጢረኛ ወደጅ ያልያዙትን አላህ ሳይገልጽ፣ ልትተዉ ታስባላችሁን? አላህን በምትሠሩት ሁሉ ዉስጠ ዐዋቂ ነው። 9:20 እነዚያ ያመኑት ከአገራቸዉም የተሰደዱት በገንዘቦቻቸውና በነፍሶቻቸዉም በአላህ መንገድ ላይ የታገሉት አላህ ዘንድ በደረጃ በጣም የላቁ ናቸው፤ እነዚያም እነሱ ፍላጎታቸውን ያገኙ ናቸው።
27 mins • Like
አልቁርአኑ መንሀጁ ሀያቲ 9:24 ፦ አባቶቻችሁና ወንዶች ልጆቻችሁ፣ ወንድሞቻችሁም፣ ሚስቶቻችሁም፣ ዘመዶቻችሁም፣ የሰበሰባችኋቸዉ ሀብቶችም፣ መክሰሩዋን የምትፈሩዋት ንግድም፣ የምትወዷቸው መኖሪያዎችም እናንተ ዘንድ ከአላህና ከመልክተኛዉ በርሱ መንገድም ከመታገል፣ ይበልጥ የተወደዱ እንደሆኑ፣ አላህ ትእዛዙን እስከሚያመጣ ድረስ ተጠባበቁ፣ በላቸው፤ አላህም አመጠኞች ሕዝቦችን አይመራም።
27 mins • Like
Abu Meryem Sami AlJeberti "እነዚያ ያመኑት ከአገራቸዉም......" lemilew merejaye bleh lametahew mlash:
Mi'emenan sibal sehabawoch bamenut menged new. Qur'anum benesu gize new yeweredew. Inesun ina benesu menged leteramedu new mimeleketew.
فَإِنْ آمَنُوا بِمِثْلِ مَا آمَنتُم بِهِ فَقَدِ اهْتَدَوا ۖ وَّإِن تَوَلَّوْا فَإِنَّمَا هُمْ فِي شِقَاقٍ ۖ فَسَيَكْفِيكَهُمُ اللَّهُ ۚ وَهُوَ السَّمِيعُ الْعَلِيمُ (137)
"በርሱ ባመናችሁበት ብጤ ቢያምኑ በእርግጥ ተመሩ፡፡ ቢዞሩም እነርሱ በጭቅጭቅ ውስጥ ብቻ ናቸው፡፡ እነርሱንም አላህ ይበቃሃል፤ እርሱም ሰሚው ዐዋቂው ነው፡፡ "
Ibakhn kelay yetsafkwachewn 3 commentochen merejawi mels stegn. Ibakihin.
Unable to post comment. Try Again
________________________________________________
ጨርሻለሁ። አሰላሙ ዓለይኩም

Post a Comment

0 Comments