Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ሼኽ ሙቅቢል ኢብኑ ሃዲ አል-ዋዲዒ ያሉትን አንብቡማ


ሼኽ ሙቅቢል ኢብኑ ሃዲ አል-ዋዲዒ ያሉትን አንብቡማ:
“እውቀት ፈላጊዎችን የምመክረው ነገር ቢኖር: ራሳችውን በመሪዎች ነገር አያጥምዱ (ቢዚ አያርጉ)፤ ጠቃሚ ወደ ሆነው እውቀትም እንዲጠጉ።
እነሱኮ (መሪዎቹኮ) በስራዎቻቸው ላይ የእውቀት ባለቤቶችን አያማክሩም (አያወያዩም)። ስለዚህ ለምን ራሳችንን በዚህ ነገር እናጠምዳለን???
እኛ ወደ አብዮት አንጣራም፣ እንደዛውም ወደ መፈንቅለ-መንግስት አንጣራም።
- ወላሂ ዒራቅ ላይ አብዮት እንዲኖር አንወድም። ምክንያቱም የሙስሊሞች ደም ይፈሳል።
- ሊብያ ላይም አብዮት እንዲኖር አንወድም። ምክንያቱም ጣጣው (ጦሱ) የሚሆነው ምስኪኖች ላይ ነው።
- ሱርያ ላይም አብዮት እንዲኖር አንወድም። ምክንያቱም ጣጣው (ጦሱ) የሚሆነው ሙስሊሞች ላይ ነው።”
“አል አስኢለቱል-የመኒያ” “الأسئلة اليمنية في مسائل الإيمان والتكفير المنهجية أجاب عنها العلامة مقبل بن هادي“ የሚለው ኪታባቸው ላይ የሰፈረ ፅሁፍ
______________________________________________________________
አለቀ የሳቸው ንግግር። እሳቸው ከሞቱ 13 ዓመት ገደማ ሆኗቸዋል። ግን አሁን አጠገባችን ያሉ ያስመስላል ቀደም ያለው ንግግራቸው። ዑለማዎች አንዲትን ችግር የሚያውቋት ከመምጣቷ በፊት ነው። አላዋቂዎች ግን ችግሯ ካለፈች በኋላ ነው የሚያውቋት።
________________________________
እንዲሁም የሼይኹል ኢስላም ኢብኑ ተይሚያህ ንግግርን ተመልከቱ
“የዓለምን ሁናቴ ያስተነተነ ሰው ምድር ላይ መስተካከልን ካየ ምክንያቱ አላህ በአምልኮ ተነጥሏል፣ መልዕክተኛውም ታዘዋል (ትእዛዛቸው ተከብሯል)። (በተገላቢጦሽ) ዓለም ላይ ክፋት (ሸር)፣ ፈተና፣ መከራ፣ ድርቅ፣ የጠላት የበላይ ሆኖ መጨቆን እናም የመሳሰሉት ካለ ምክንያቱ መልዕክተኛውን መቃረን እና ከአላህ ውጭ ወዳለ አካል መጣራት ነው።”
መጅሙዑል-ፈታዋ 15/25
___________________________________________________
አሁን በሂወት ያሉ አይመስሉም??? እውነታቸውን ነው አላህ ይዘንላቸውና። ተመልከቱ እስቲ ዓረብ ሃገራት ብትሉ አፍሪካ ሃገራት ብትሉ ምን ብትሉ ምን ዓለማችን ጉስቅልቁሏ ነው እየወጣ ያለው። አላህ ያስተካክለን፤ አላህ ይጠብቀን።
መፍትሄው ምንድነው ከተባለ ከላይ ያሉትን ፅሑፎችን አስተውሉ።

Post a Comment

0 Comments