Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ሙስሊም መሪን መራገም እና ለእርሱ ዱዓ ማድረግ አስመልክቶ የኢማም አል በርበሃሪን ንግግር ከሸርሁ ሱና ኪታባቸው ላይ ጠቅሼ ባስቀመጥኩት ላይ የሚከተሉት ጥያቄዎች እና ማንገራገሮች በፌስቡክ እና ዋትስ አፕ ተሰንዝረዋል፡፡

ሙስሊም መሪን መራገም እና ለእርሱ ዱዓ ማድረግ አስመልክቶ የኢማም አል በርበሃሪን ንግግር ከሸርሁ ሱና ኪታባቸው ላይ ጠቅሼ ባስቀመጥኩት ላይ የሚከተሉት ጥያቄዎች እና ማንገራገሮች በፌስቡክ እና ዋትስ አፕ ተሰንዝረዋል፡፡
‹‹ባሁኑ ዘመን መች ሙስሊም መሪ አለ››፤
‹‹በአሁን ሰዓት ሙስሊም መሪ የሚባል የት አለ?››፤
‹‹ማን ነው ሙስሊም መሪ?››

ሱብሃነላህ አዎን ባለንበት ዘመን ጥሩም ይሁን መጥፎ ሙስሊም መሪዎች አሉ፡፡ ሙስሊም መሪዎችን የአላህ መላክተኛ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ቢደበድቡንም፤ ቢቀሙንም እንድንሰማ እንድንታዘዝ ነበር ያዘዙን፡፡ የሙስሊም መሪን አስመልክቶ ጥፋት ሲያጠፉ ለብቻቸው እንድንመክራቸው ነበር ያዘዙን
ኢያድ ኢብን ጉኑም እንደዘገቡት ረሱል ሰለላሁአለይሂወሰለም እንዲህ ብለዋል:- ‹‹ ማንም ሰው ሙስሊም መሪውን መምከርና መገሰፅ ከፈለገ በአደባባይ ማድረግ የለበትም እንግዲያውስ ቀረብ ብሎ መሪውን እጁን ይዞ (በፅሁፍም ሆኑ በሌላ ማግኛ ዘዴዎች) ምክሩን ይለግሰው። ምክሩን ተቀብሎት እንደሆን አላማውን አሳክትዋል ካልተቀበለውም በመምከሩ ግዴታውን ተወጥትዋል ›› [አሕመድ ዘግበውታል አልባኒ ሰሒሕ ብለውታል]
መቼም መሪ ከማህበረሰቡ ነው የሚሾመው፡፡ ጥሩን ለጥሩ፤ ቢጤን ለቢጤ እንደሚባለው፡፡ ይህን ጥያቄ የሚጠይቁ ሰዎች እራሳቸውንም ሆነ ማህበረሰቡን አክፍረው ነውን? ካልሆነ ሙስሊሞች በዚህ ባለንበት ማህበረሰብ ውስጥ እንዳሉት ሁሉ በዚህም ዘመን ሙስሊም መሪዎች አሉ፡፡ መቼም እነዚህ መሪዎች አቡበክር ሲዲቅ፤ ኡመር፤ ኡስማን፤ አልይ፤ ሙዐዊያ፤ ኡመር አብድል አዚዝ (ረድየላሁ አንሁም) እንዲሆኑ አይጠበቅም ምክንያቱም እኛ በአቡበክር እና ኡመር ዘመን የነበሩትን አይነት ሰዎች አይደለንም እና፡፡
የአላህ መላክተኛ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ከሳቸው በኋላ ስለሚመጡት ሙስሊም መሪዎች ነው ነግረውን የሄዱት ጥሩውንም መጥፎውንም እንድንታዘዝ በመጥፎ እስካላዘዙን ድረስ ግልፅ ኩፍር እስካልፈፀመ ድረስ፡፡ ታድያ የነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለምን) ሃዲስ ወደዚያ አሽቀንጥሮ ጥሎ ወዴት ሊደረስ ነው???
አላህ ስሜትን ከመከተል ይጠብቀን