Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ኢስላም ስለ ሙስሊም መሪዎች ጥሩም ይሁን መጥፎ ምን ይላል፡፡

ኢስላም ስለ ሙስሊም መሪዎች ጥሩም ይሁን መጥፎ ምን ይላል፡፡
ኢስላም በሙስሊም መሪዎች ላይ አምፆ መውጣትን በጥብቅ ይኮንናል፡፡ የፍትህ መጓደል፣ አድሎ፣ ብዝበዛና ግፍ ቢኖር እንኳ በማያሻማ ሁኔታ ከኢስላም እስካልወጡ ድረስ ፊትና በማይፈጥር መልኩ መምከር እንጂ ብጥብጥ መቀስቀስን አልፈቀደም፡፡ ይህን የሚያመላክቱ ከ 100 በላይ መረጃዎች ቢኖሩም የነብዩን ትእዛዝ ለሚያከብሩ ሀቅ ፈላጊዎች አንድ ማስረጃም ቢሆን ይበቃቸዋል፡፡ ለናሙና ያክል ጥቂት መረጃዎችን ልጥቀስ
1. “ሙስሊም የሆነው ሰው መሪውን ቢወድም ቢጠላም መታዘዝ አለበት፡፡ በወንጀል እስካልታዘዘ ድረስ፡፡” ቡኻሪና ሙሊም
2. “አዋጅ! በሱ ላይ መሪ የተሾመበት ሰው፣ መሪው በአላህ ላይ ሲያምፅ ካየው ያየውን ነገር ይጥላ፡፡ ለአሚሩ ያለውን ታዛዥነት ግን እንዳያነሳ” ሙስሊም የዘገቡት፡፡
3. “ከኔ በኋላ በመመሪያየ የማይመሩ፣ በሱናየም የማይጓዙ መሪዎች ይመጣሉ፡፡ በነሱም ላይ ልቦቻቸው የሸይጧን አካላቸው ደግሞ የሰው የሆኑ ሰዎች ይነሱባቸዋል” አሉ፡፡ ሁዘይፋ ረዲየላሁ ዐንሁ “እንዲህ አይነት ሁኔታ ላይ ከደረስኩኝ ምን ላድርግ” ሲላቸው “አሚሩን ትሰማለህ፣ ለሱም ትታዘዛለህ- ጀርባህን ቢመታህም ገንዘብህን ቢነጥቅህም እንኳን” አሉት፡፡ ሙስሊም የዘገቡት
4. “ከኔ በኋላ መልካምም ክፉም መሪዎች ይመጣሉ፡፡ መጥፏቸውን የተቃወመ በርግጥም ነፃ ሆነ፡፡ መጥፏቸውን የጠላ በርግጥም ዳነ፡፡ መጥፏቸውን የወደደና የተከተለ ግን ጠፋ!!!” አሉ፡፡ ሶሐቦችም እንዲህ አይነት መሪዎችን በሰይፍ እንፋለማቸው” ሲሉ ጠየቁ፡፡ ነብዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ግን “ሶላትን እንዲሰገድ እስካደረጉ ድረስ እንዳታደርጉት” አሉ፡፡ ሙስሊም የዘገቡት
5. ሶሐቦች “ሐቃቸውን የሚጠይቁን ሐቃችንን ግን የሚከለክሉን መሪዎች ካገኙን ምን እናርግ” ብለው ነብዩን ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ጠየቁ፡፡ እሳቸውም “ስሙ ታዘዙ!! በነሱ ላይ የተጣለባቸው ሀላፊነት አለ፡፡ በናንተም ላይ የተጣለባችሁ ሀላፊነት አለ” አሉ፡፡ ሙስሊም የዘገቡት

እነዚህ ማስረጃዎች ለሁሉም ሙስሊም መሪዎች የሚሰሩ ናቸው፡፡ እህቶችና ወንድሞች እባካችሁ ለመረጃ እጅ እንስጥ፡፡ እንደ ቡድናቸው ጥቅም የሐዲሶችን መልእክቶች የሚቀያይሩ ኢኽዋኖች ሰለባ አንሁን