Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

"ቀድሞ ነበር እንጂ መጥኖ መደቆስ፤ ኋላ ምን ያደርጋል ድስት ጥዶ ማለቀስ፡:" የሚከተለው አጭር ፅሁፍ በወንድማችን ሙሃመድ ኢብራሂም የግብፁ የቀድሞ ፕሬዝዳንት ሙሃመድ ሙርሲ ኢኽዋኒ ላይ ህዝባቸው ሲያምፅ ነበር የተፃፈው፡፡ እስቲ ለትዝብት ያህል ወደ ኋላ ዞር ብለን እንቃኘው፡፡

"ቀድሞ ነበር እንጂ መጥኖ መደቆስ፤ ኋላ ምን ያደርጋል ድስት ጥዶ ማለቀስ፡:"
የሚከተለው አጭር ፅሁፍ በወንድማችን ሙሃመድ ኢብራሂም የግብፁ የቀድሞ ፕሬዝዳንት ሙሃመድ ሙርሲ ኢኽዋኒ ላይ ህዝባቸው ሲያምፅ ነበር የተፃፈው፡፡ እስቲ ለትዝብት ያህል ወደ ኋላ ዞር ብለን እንቃኘው፡፡
By Mohammed Iberahim
ልብ ያለው ልብ ይበል!
وَمَن يُشَاقِقِ الرَّسُولَ مِن بَعْدِ مَا تَبَيَّنَ لَهُ الْهُدَىٰ وَيَتَّبِعْ غَيْرَ سَبِيلِ الْمُؤْمِنِينَ نُوَلِّهِ مَا تَوَلَّىٰ وَنُصْلِهِ جَهَنَّمَ ۖ وَسَاءَتْ مَصِيرًا [٤:١١٥]
"ቅኑም መንገድ ለእርሱ ከተገለጸ በኋላ መልክተኛውን የሚጨቃጨቅና ከምእምኖቹ መንገድ ሌላ የኾነን የሚከተል ሰው (በዚህ ዓለም) በተሾመበት (ጥመት) ላይ እንሾመዋለን፤ ገሀነምንም እናገባዋለን፡፡ መመለሻይቱም ከፋች!" 4፡115

በርግጥ ትክክለኛው የነቢዩ(ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) መንገድ ፍንትው ያለ ነው፡፡ትናንትም ዛሬም ግልጽ ነው፡፡ ነቢያችንም "ግልጽ በሆነ ሜዳ ላይ ትቻችኋለሁ፤ ሌሊቱ እንደቀኑ በሆነ" ብለው ነበር፡፡ አዎን ከዚህ ግልጽ መንገድ ግን ጨለማውን የመረጠ፣ ስሜቱ እንዳዘዘው የተነዳ፣ የነቢዩን ሱና ጥሎ በዘመን አመጣሽ ፍልስፍና የበረረ ምንግዜም እንደተምታታ ነው፡፡ ለዚህ ደግሞ ዛሬ ወንድሞቻችን በግብጽ የወደቁበትን መመልከት ጥሩ ነው፡፡
ለግብጽም ሆነ ለመሪዋ መልካም እንመኛለን፡፡ ግና ዛሬ ግብጾች እንደለመዱት ሙስሊም መሪያቸውን አሽቀንጥረው ሊጥሉ ባደባባይ ተሰልፈው ያንቋርራሉ፡፡ ገዢው ፓርቲ ደግሞ "አላህን ፍሩ በመሪ ላይ አታምጹ" ይላል፡፡ ዋ…ኔ! ማን ነው ለዚህ ምስኪን ህዝብ አመጽ ያስተማረው? እኮ ማንስ ነው በተቀሩት ሙስሊም ሀገራትና ሙስሊም መሪዎች ላይ ተቃውሞና አመጽ የሚቀሰቅሰው? ኢኽዋነል ሙስሊሚን አይደለም እነዴ?! ታዲያ ዛሬ ህዝቡን ተው ብትለው ምን ልሁን ብሎ እሺ ይልሀል? `ትናንት ተነስ ፈንቅል!` ስትለው የነበረውን ህዝብ ዛሬ በየትኛው አፍህ `ቁጭ በል` ትለዋለህ፡፡ ትናንት ሲነገርህ ይጎመዝዝህ የነበረው ሐዲስ እንዴት ዛሬ ላፍህ ጣፈጠህ?
"ቀድሞ ነበር እንጂ መጥኖ መደቆስ፤ ኋላ ምን ያደርጋል ድስት ጥዶ ማለቀስ፡:" ያለውን ማን ለኢኽዋኖች በነገራቸው፡ ለነገሩ ሐዲስ አልሰማ ያሉ ጀግኖች ለኔ ቢጤ ተረት መች ጆሮ ይኖራቸዋል፡፡
አሁንም ተመከር! ምንም ይሁን ማን የሙስሊም መሪ ልታምጽበትና ጣትህን ልትቀስርበት አይገባም፡፡ ስልጣን ለማስለም ከመሄድህ በፊት ህዝቡን ለማስለም ሂድ፡፡ ህዝቡ ሳይሰለም ወንበር ብትጨበጥ፤ በሰቀለህ እጁ አውረዶ ይፈጠፍጥሀል!
እወቅ! የነቢዩ ሱና ቅድሚያ ለተውሂድ እንጂ ቅድሚያ ለPOWER አይልም፡፡ ተመከር! ምንግዜም የነቢዩ ሱና ለስኬት አቋራጭ ነው፡፡ ሌላን አቋራጭ በፈለክ ቁጥር ትርፍህ በዱኒያም በአኸይራም ኪሳራ ነው፡፡ የዛሬ 80 አመት በተፈበረከ ፍልስፍና ከመነዳት ሰለፎች በነጎዱበት ፋና መመራት ልዋጭ የሌለው አማራጭ ነው፡፡ ስለ አኸይራ እጣፈንታ አላህ ያውቃል! የዱኒያውን ግን እያየነው ነው!!
ልብ ያለው ልብ ይበል! ለሀቅ ፈላጊ ይህ በቂው ነው፡፡ ስሜቱን ለሚከተል ግን አላህ ይሁነው፡፡
ነቢዩ(ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) እንዲህ ብለው ነበር "አሚሩን የሚታዘዝ በርግጥ ታዘዘኝ፤ አሚሩን የሚያምጽ ደግሞ በርግጥ አምፆብኛል" ቡኻሪ ዘግበውታል
አላህ ግብጽንም መሪዋንም ይጠብቃቸው፡፡
===============================
ትላንት የፖለቲካ ፓርቲ መሪያቸው የነበረውን ሙሃመድ ሙርሲን ስልጣን ላይ ለማቆየት የነብዩን (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ሀዲስ ‹‹መሪን ስሙ እና ታዘዙ›› የሚለውን ቢናገሩትም ህዝቡ አልሰማ አላቸው፡፡ መቼ ለሌሎች የሙስሊም መሪዎች ጥሩም ይሁኑ መጥፎ ይህን ሀዲስ ተግብረውት ያውቁ ነበር???
አል ጀዛኡ ሚን ጂንሲል አመል

Post a Comment

0 Comments