Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ዛሬ ዛሬ በፋሽን ሰበብ በየ መንገዱ ተገላልጠው እና የሰውነታቸውን ቅርጽ የሚያሳዩ .....

ዛሬ ዛሬ በፋሽን ሰበብ በየ መንገዱ ተገላልጠው እና የሰውነታቸውን ቅርጽ የሚያሳዩ እጅግ በጣም አጭር ሆነው በሱሪ እና በላይኛው ልብሳቸው መሃከል ያለውን የሰውነት አከላቸውን ገላልጠው የሚዞሩ ወንዶችን ማየት ከእንግደነትም አልፎ የተለመደ ነገር ሆነ እያየን ነው ነገር ግን ይህን አለባበስ በለመዱበት ጎደና ለይ ቢንጎራደዱበት ጥሩ ነበር ሆኖም ግን ይህ አለባበስ መስጊድ ሁላ ዘልቆ በመግባት ለሰላት ሲቆሙ ረቁታቸውን ሆነው ማየት በጣም የሚያሳዝን ከመሆኑም ጋር ህዝባችንም ምን ያክል መሰረታዊ ለሆኑ ኢስላማዊ መርሆች እውቀቱ አነስተኛ መሆኑን ያመላክታል። መቼም አንድ ሰው ግዜውን መስዋት አድርጎ ሰለቱን የሚሰግደው አላህ ዘንድ ተቀባይነት እንዲኖረው እና ዘላለማዊ የሆነውን የመቺውን አለም በማሰብ መሆኑ ምንም ጥርጥር ዬለውም ይህ ሰይሆን ቀርቶ ይሰግዳል ኣአንዲባል ከሆነ የበሳ ቅጣት የተብቀዋል ምክንያቱም ለዪዩልኝ ተበሎ የሚሰራ ስራ ሽርክ ነው ሽርክ ደግሞ ወደ ጀሓነም ለመዶል ወነኛ ምክንየት ነውና። ወደ ዋና ሐሳቤ ልመለስና አንድ ሰላት አላህ ዘንድ ተቀባይነት እንዲኖራት መሟለት የሚገባቸው መስፈርቶች የሚከተሉትን ይመስላሉ።
1 ሙስሊም መሆን
2 አቅሉ በትክክል የለ መሆን(እብድ የልሆነ)
3 ለ አቅመ አደም/ ሔዋን መድረስ
4 ለ ኡዱ ወይንም ለትጥበት የሚያስገድዱ ነገሮች መወገድ
5 ነጃሳን ከሰውነት ማስወግድ
6 አውረ የሆኑ የሰውነት ክፍሎችን መሰፈን
7 የሰላት ወቅት መግባት
8 ወደ ቂብላ መቀታቸት
9 ኒያ(በቀልብ)
ትኩረት ማድረግ የፈለኩት በቁትር 6 ላይ የተጠቀሰው ሸርጥ ነው ብዙ ግዜ መስጂድ ላይ ጀማኣ ሰላትም ይሁን በግል ሲሰግዱ ብትመለከቱ በዙ ወንድሞች የሚለብሱዋቻው ሹራቦች ከማጠራቸው እንዲሁም በፋሽን ሰበብ ቀበቶ ካለመልበሳቸው የተነሳ ለሩኩ ጎንበስ ሲሉ የማህል ሰውነታቸው እርቃናቸውን ሲሆን ይታያል እንደም ኣንዳንዴ ኢማም ሆነውም ታገኛቸዋለክ ይህ ሊስተካከል የሚገባው ነገር ነው ምክንያቱም የአንድ ሙስሊም ወንድ ሰውነት ከእምብርቱ እስከ ጉልበቱ መሽፈን የገባዋል አውራ ነው እና ይህ ካልሆነ ሰላቱ ሸርጡን አላሟለም ተቀበይነት ኣይኖረውም። አላህ ሰላታቸውን ሸርጧን አሟልተው እና በኹሹ ከሚሰግዷት ባሪያዎቹ ያደርገን አላሁማ አሚን