Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

አስገራሚ ነው የህፃናት ቁርዓን ምርቃት ተብሎ ድራማ እና ነሺዳ.... መጨረሻው ምን ይሆን?


አስገራሚ ነው
የህፃናት ቁርዓን ምርቃት ተብሎ ድራማ እና ነሺዳ.... መጨረሻው ምን ይሆን?
- ነሺዳ፤
- ድራማ
- ከዛ በመጨረሻ ለኡስታዙ የዳዕዋ ፕሮግራም
በዲን ስም ዲንን ከማበላሸት አላህ ይጠብቀን፡፡

ትላንት እሁድ ኡስታዝ ሰዒድ ሙሳ (አቡል ቡኻሪ) የዳእዋ ፕሮግራም እንደተጠራ እና አብሬው እንድሄድ ጠየቀኝ፡፡ አብረን ሄድን በጊዜ ስለደረስን መድረሳዋ ላይ ተማሪዎቹን በክረምት ቁርዓን ያስተማራቸው ኡስታዝ ስለ ፕሮግራሙ ለኡስታዝ ሰዒድ ይነግረው ጀመር፡፡
- አንድ ተማሪ ከተማረው ቁርዓን ውስጥ ያሰማል፤
ልጆቹን ቁርዓን ያስተማረውን ኡስታዝ ጫን ያለ ግሰፃ ለገስንለት፡፡ እንዴት አላህን አትፈራም፤ እድሜያቸው ለጉርምስና የደረሱ ወንድ እና ሴቶች መድረክ ላይ ወጥተው ድራማ ይስሩ ይባላል ትላለህ አልነው፡፡ እሱም ተማሪዎቹ እንዳስቸገሩ ሊነግረን ሞከረ፡፡ አንተ ነህ አስተማሪ፤ ተማሪዎችህን በስነስርዐዓት ማነፅ ይጠበቅብሃል አልነው፡፡ ሴቶቹን አስጠርተን አኢሻ (ረድየላሁ አንሃ) የምዕመናን እናት ከመሆኗም ጋር ሰሃባዎችን ከመጋረጃ ጀርባ ታስተምር እንደነበር እና ሌሎችንም ነገሮች መከርናቸው፡፡
ብቻ ቤተሰብ ልጆቹን ወዴት አይነት መድረሳ እና እንዴት አይነት ኡስታዝ ጋር እንደሚልክ ጠንቅቆ ሊያውቅ ይገባዋል፡፡ በዲን ስም ቢድዓን እና ጥመትን ሸምተው ከመጡ አደጋው የከፋ ነው፡፡ አተርፍ ባይ አጉዳይ እንዳንሆን እንጠንቀቅ፡፡
በየመድረሳው የምትሰሩ አላህን ልትፈሩ ይገባችኋል፡፡ ቤተሰብ ልጆቹን ድራማ ማስተማር ቢፈልግ ትምህርት ቤት ሆነ ሌላ ቦታ ልጆቹን ይልካል፡፡ በዲን ስም ለምን የሙስሊም ልጆችን መንገድ ማሳት ያውም ቁርዓንን ብሎ የመጣን ድራማ እና ነሺዳ ማስባል ኢናሊላሂ ወኢና ኢለይሂ ራጂዑን፡፡ አረ አላህን ፍሩ ቁርዓን፤ ሀዲስ እና የሰሃባዎች ታሪክ እና ተግባር ያለወጠውን ተውልድ ‹‹ድራማ፤ ነሺዳ እና ሌላም›› አይለውጠውም፡፡