Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

አሕባሽ እና ኸዋሪጁ ISIS(ዳዒሽ)

አሕባሽ እና ኸዋሪጁ ዳዒሽ
እራሱን ISIS (በዐረብኛው ምህፃረ-ቃል ዳዒሽ) እያለ የሚጠራው ፅንፈኛው አንጃ ከቅርብ ጊዜ ጀምሮ የዒራቅና የሶሪያ ግዛቶች ውስጥ በሰፊው እየተንቀሳቀሰ ነው፡፡ አንጃው አቡበክር አልበግዳዲ በሚባል ዒራቃዊ የሚመራ ተስፈንጣሪ የኸዋሪጅ ቡድን ነው፡፡ አንጃው አካሄዱን ያልተቀበሉ ሙስሊሞችን ባደባባይ ሲረሽን፣ በጅምላ ሲጨፈጭፍ፣ አስከሬኖቻቸውን ከእይታ በራቁ ስውር ጉድጓዶች ሲወረውር የሚያሳዩ የቪድዮ መረጃዎች ወጥተዋል፣ እየወጡም ነው፡፡ አንጃው በቅርቡ በቁጥጥሩ ባሉ የዒራቅና የሶሪያ ተሸጋጋሪ ግዛቶች ውስጥ “ኢስላማዊ መንግስት መስርቻለሁ” እያለ ነው፡፡ የኸዋሪጅ አመለካከት የተፀናወታቸው አካላት በኢስላምና በሱና ስም አረመኔያዊ ጭፍጨፋ በፈፀሙ ቁጥር የኢስላም ጠላቶች ዘወትር ጣታቸውን የሚቀስሩት ወደ አንድ አቅጣጫ ነው፡፡ ምእራባውያን ሽብርና አክራሪነት የሸይኽ ሙሐመድ ኢብኑ ዐብዲልወሃብ አስተምሮ ውጤት እንደሆነ ደግመው ደጋግመው ያስተጋባሉ፡፡ ለምእራባውያን ተልካሻ ጥቅማጥቅም የሚንበረከኩ ተውሒድን የሚዋጉ አካላትም ጉዳዩ ላይ እጃቸውን ያስገባሉ፡፡
እውነታው ግን ወዲህ ነው፡፡ እነዚህ በየቦታው የሚያፈነዱ፣ ሰላማዊ ዜጎችን የሚጨፈጭፉ አካላት ከሸይኽ ሙሐመድ ኢብኑ ዐብዲልወሃብ አስተምሮ ያፈነገጡ ናቸው፡፡ እነኚህ ጠርዘኛ አካላት ቀዳሚ ኢላማ የሚያደርጉት ሙስሊሞችን ነው፡፡ ለዚህም መነሻቸው ሙስሊሞችን ማክፈራቸው ነው፡፡ ሙስሊሞችን ማክፈር ግን የሸይኽ ሙሐመድ ኢብኑ ዐብዲልወሃብ አቋም አይደለም፡፡ ሸይኹ ረሒመሁላህ “እኛ በጅምላ እንደምናከፍር፣ ባሉበት ዲናቸውን ማንፀባረቅ የሚችሉን ሰዎች ወደ እኛ መሰደድ አለባቸው እንደምንል፣ ያላከፈረን እንደምናከፍርና እንደምንዋጋና ሌላም እጥፍ ድርብ የሚወራው ይሄ ሰዎችን ከአላህና ከመልእክተኛው ዲን ለመዝጋት የሚጠቀሙበት ውሸትና ቅጥፈት ነው” [አዱረሩሰኒያ፡66]” የሚለው ንግግራቸው በሀሰት ለሚወነጅሏቸው ጠላቶቻቸው እና በኸዋሪጅ ቫይረስ ለተጠቁ እንጭጮች ህያው ምስክር ነው፡፡ በሌላም ቦታ “ከተከተሉኝ ውጭ ያሉን ሁሉንም ህዝብ እንደማከፍርና ኒካሐቸውም ትክክል አይደለም እያልኩ እንደምሞግት የጠቀሳችሁት ግን አቤት ሲደንቅ! ይህን የሚለው ሙስሊም ነው? ወይስ ካፊር ነው? ወይስ እብድ ነው?” [አርረሳኢሉ አሽሸኽሲያህ፡ 18] አንዳንዶች ደግሞ ልክ አሕባሾች እንደሚያደርጉት የኸዋሪጆቹን በሽታ ወደ ኢብኑ ተይሚያህ ይወስዱታል፡፡ ይሄ ግን አይን ያወጣ ቅጥፈት ነው፡፡ ሸይኽ ኢብኑ ተይሚያ ረሒመሁላህ ሙስሊሞችን ከማክፈር እጅግ የራቁ እንደነበር ይሄ ንግግራቸው አጉልቶ ያሳያል፡- “ማንም የትኛውንም ሙስሊም ቢሳሳትም ሊያከፍር አይገባውም፡፡ መረጃ ካልቆመበት፣ እውነታው ግልፅ ካልተደረገለት በስተቀር፡፡ እስልምናው በየቂን የተረጋገጠ በጥርጣሬ ከሱ አይወገድም፡፡ [መጅሙዑል ፈታዋ፡ 12/466] “እኔ ሁሌም - አብሮኝ የሚቀመጥ ሁሉ ከኔ የሚያውቀው- አንድን ሰው ለይቶ ካፊር ወይም አመፀኛ ወይም ወንጀለኛ ማለትን አጥብቀው ከሚከለክሉት ነኝ፣ ፡፡ …” [መጅሙዑል ፈታዋ፡ 3/229]
እነዚህን የተውሒድ አርበኞች በመልካም የተከተሉ ታላላቅ ዑለማዎችም ዛሬም ድረስ ይህን የኸዋሪጅ አመለካከት በፅኑ ያወግዛሉ፡፡ እነ ሸይኽ ኢብኑ ባዝ፣ አልባኒ፣ ኢብኑ ዑሠይሚን፣ ሙቅቢል፣ ፈውዛን፣ ወዘተ የነ ቢላደንን፣ አልቃዒዳን እና የመሰሎቻቸውን አካሄድ ከኢስላም ጋር ምንም አይነት ግንኙነት እንደሌለው በግልፅ አጋልጠዋል፡፡ የሚገርመው ግን እነኚህ ታላላቅ ዑለማዎች ባንድ በኩል በኢስላም ጠላቶች የአክራሪነት ምንጭ እየተደረጉ ሲሳሉ፣ እንደ አሕባሽ ባሉ ግልገሎች “ወሃብዮች” እየተባሉ ሲኮነኑ፣ በሌላ በኩል ደግሞ እንደ ኢኽዋን ባሉ ጠማማ አንጃዎች ለምእራባውያን ጥቅም እንደሚሰሩ መወረፋቸው ነው፡፡
የሰሞኑ የአሕባሾች ስራም ይሄው ነው፡፡ “ኢስላማዊ መንግስት መስርቻለሁ” የሚለው ISIS /ዳዒሽ/ የሚባለው የኸዋሪጅ አንጃ ለመግለፅ የሚሰቀጥጡ ጭፍጨፋዎችን እየፈፀመ እንደሆነ አለም እየተመለከተው ነው፡፡ ነገሩን በቅጡ ሳያጣሩ፣ የዑለማዎችንም አቋም ሳያረጋግጡ እንዲሁ “ኢስላማዊ” የሚል ቃል ለተለጠፈለት ሁሉ በጭፍን የሚያራግቡ ሙስሊሞች ቢሸወዱም አንጃው በርካታ ከኢስላም ጋር የማይሄዱ ያፈጠጡ፣ ያገጠጡ ጥመቶችን እያንፀባረቀ ነው፡፡ ከጥመት ባህር ውስጥ የምትዋልለው አሕባሽ ታዲያ ገባያዋ አልደራ ቢላት፣ የሚከተላት ብታጣ ጊዜ፣ አጋጣሚውን ልትጠቀም እየተውተረተረች ነው፡፡ በዳዒሽ እየተፈፀሙ ያሉ ዘግናኝ ጥፋቶችን በምስል እያስደገፈች “ይሄውና ወሃብዮች ይህን ፈፀሙ” እያለች ታራግብ ይዛለች፡፡
ነገር ግን
1. ይህንን የኸዋሪጅ አንጃ ከማንም በፊት ከማንም በላይ እያጋለጡት ያሉት የጠማማው አሕባሽ አንጃ ተከታዮች ሳይሆኑ የአህሉሱና ዑለማዎች ናቸው፡፡ ማረጋገጥ የሚፈልግ እነዚህን ሊንኮች ይከታተል፡፡
a. የኸዋሪጁን ቁንጮ አቡበክር አልበግዳዲን በተመለከተhttp://www.safeshare.tv/w/DvLotvfpCt
b. ዳዕሽ፣ አንሳሩሽሸሪዐንና መሰሎቻቸውን በተመለከተhttp://www.safeshare.tv/w/YQuHxSjTKn ,http://www.safeshare.tv/w/mzfCCWunMA
c. ዳዕሽ አልቃኢዳና ኢኽዋንን በተመለከተhttp://www.sahab.net/forums/index.php?showtopic=146336
d. ሙስሊም ዳዕሽን ሊወድም ለነሱ ቃል ሊገባም አይገባውም- ሸይኽ አርሩሐይሊ http://www.ajurry.com/vb/attachment.php?attachmentid=45809&d=1408716828
e. ወዮላችሁ የዳዕሽ ተከታዮችhttp://ar.alnah.net/audio/download/1612/waylakum_ayuha_adawa3ish.mp3
f. ዳዕሽና አመለካከታቸው፣ ሸይኽ ኣይድ አሽሹመሪ http://goo.gl/wPgHr6
g. የኸዋሪጅና የዳዕሽ እውነታ፣ ሸይኽ ኻሊድ ዐብዱረሕማንhttp://ar.alnah.net/audio/download/1340/28-1435
h. የኢስላምና የሸይኽ ሙሐመድ ኢብኑ ዐብዲልወሃብ የሰለፍያ ደዕዋ ከዳዕሽ የጠሩ ናቸው! ሸይኽ ዐብዱላህ አዝዙፈይሪ http://goo.gl/26xhZc
i. ዳዕሽን ከሰለፍያ ጋር የሚያይዝ በርግጥም ዋሽቷልhttp://ar.alnah.net/audio/download/1695/obaid-daesh-nabta.mp3
2. ከዚያ በተረፈ አሕባሽ እራሷ ከሊባኖሱ የርስበርስ ብጥብጥ ውስጥ እጇን አስገብታ ስታቦካ እንደነበር ማስረጃዎች ያመላክታሉ፡፡
3. ለሰው በላው የሶሪያው መንግስት የሚያጨበጭቡት አሕባሾች በየትኛው ሞራላቸው ነው ደግሞ ተቆርቋሪ ሆነው የሚቀርቡት?
a. አሕባሽ ለሶሪያ መንግስት ድጋፍ ሲሰጡ http://www.youtube.com/watch?v=PKBb2_fQGg8
b. አሕባሽ ከሰው በላው አልአሰድ ጋር ያላቸው ቁርኝትhttp://www.youtube.com/watch?v=KF-fxls6YB4
c. አሕባሽ አይሁዳዊው ፕሮፌሰር ሀጋይ ኢርሊች በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ባደረገው “ፓናል ዲስከሺን” “ለኢትዮጵያ የሚበጀው እስልምና” ብሎ አጭቷቸዋል፡፡ በአይሁድ የሚመረጡበት ምክኒያት እውነት ለኢስላም ቢበጁ ነው?
ባይሆን አንድ ወሳኝ ጥያቄ አለ፡፡ “እነኚህ ዘመናዊ ኸዋሪጆች እየተከተሉ ያለው የማንን መስመር ነው?” የሚል፡፡ አንዳንዶች እነዚህ በየቦታው የሚያፈነዱትና ሴትና ህፃናት ሳይለዩ ሰላማዊ ሰዎችን የሚገድሉት “በኢኮኖሚ ችግር ምክኒያት ተስፋ የቆረጡ ናቸው” የሚል አጉል ግምት ያስቀምጣሉ፡፡ እውነታው ግን ሰዎቹ የኸዋሪጅን አመለካከት በሰፊው መቀበላቸው እንጂ ከኢኮኖሚ ችግር ጋር ወይም ከኑሮ ውድነትና ከስራ ማጣት ጋር የሚያያዝ አይደለም፡፡ ብዙዎችን ቢመርራቸውም እውነታው ግልፅ ነው፡፡ አዎ ዘመናዊ የተክፊር አንጃ መሰረቱ ኢኽዋን ነው፡፡ በተለይ ደግሞ ሰይድ ቁጥብ፡፡ እነኚህ ጠርዘኞች እየተከተሉ ያለውም የኢኽዋኒውን ሰይድ ቁጥብ አመለካከት ነው፡፡ ሚዛናዊ ሁናችሁ የሚከተሉትን ነጥቦች አስተውሉ፡፡
1. እነኚህ ዘመናዊ ኸዋሪጆች ሙስሊሞችን እየገደሉ ያሉት እንደካፊር ስለሚቆጥሯቸው ነው፡፡ ከተራው ህዝብ አልፈው ታላላቅ ዑለማዎችን እያከፈሩ ነው፡፡ በጅምላ ማክፈር ደግሞ የሰይድ ቁጥብ መንገድ ነው፡፡ እራሱ ይመስክር፡- “እሄ የምንኖርበት ማህበረሰብ እራሱ ሙስሊም ማህበረሰብ አይደልም፡፡ ለዚያም ነው ኢስላማዊ ስርኣት ያልዘረጋው…” “በመጨረሻም ከነዚህ የጃሂሊያ ስብስብ ውሰጥ የሚካተቱት እነዚህ ሙስሊም እንደሆኑ የሚሞግቱት ህዝቦች ናቸው፡፡” [ፊ ዚላሊልቁርኣን፡ 3/1816፣ 4/2009-2010] “ጉዳዩ የማመንና የመክፈር ጉዳይ ነው፡፡ ሰዎች እንደሚሞግቱት ሙስሊሞች አይደሉም፣ የሚኖሩት የጃሂሊያ ህይወት ነው፣ ደዐዋችን የተነሳው እነኚህን ጃሂሊዮች ወደ ኢስላም ለመመለስ ነው-እንደ አዲስ ሙስሊም ለማድረግ” [መዓሊሙን ፊጦሪቅ፡ 173] “የሙስሊሙ ኡማ ህልውና ከብዙ ከፍለ-ዘመናት በፊት ተቋርጧል፣ እንደ አዲስ መመለስ ይኖርብናል” [መዓሊሙን ፊጦሪቅ፡ 6]፣ “ዛሬ ያለነው ኢስላም ሲነሳ ያጋጠመው ዓይነት ጃሂሊያ ውስጥ ነው ወይም ከዚያ የከፋ!” [መዓሊሙን ፊጦሪቅ፡ 21]፡፡ “በአሁኑ ጊዜ ያሉ ሙስሊሞችን እርድ መብላት ይቻላል ወይ” ተብሎ ሲጠየቅ“እንደ አህሉልኪታብ (አይሁድና ክርስቲያን) እርድ ቆጥራችሁ ብሉ” ብሎ ነው የመለሰው፡፡ [አታሪኹሲሪይ ሊጀማዐቲል ኢኽዋነል ሙስሊሚን፡ 80]
2. የአልቃኢዳ ሁለተኛ ሰው የሆነው አይመን አዝዘዋሂሪ አመለካከታቸውን ከሰይድ ቁጥብ እንደወሰዱት እንዲህ ይናገራል፡- “(መዓሊሙን ፊጠሪቅ) በሚለው ዳይናሚት በሆነው ኪታቡ የሙጃሂዶችን ህገ-መንግስት ያሰፈረው ሰይድ ቁጥብ ነው፡፡ሰይድ መሰረታዊነትን ህያው በማድረግ በኩል ምንጭ ነው፡፡ “አልዐዳለቱልኢጅቲማዕያህ ፊልኢስላም” የሚለው ኪታቡ ለመሰራተውያን ሀይሎች (fundametalists) ከሁሉም በላይ ወሳኝ የሆነ አእምሯዊና እሳቤያዊ ውጤት ነው፡፡ የሱ (የሰይድ ቁጥብ) እሳቤ ከውስጥም ከውጭም ባሉ የኢስላም ጠላቶች አንፃር አብዮት ለማቀጣጠል መነሻ የእሳት ፍንጣቂ ነው፡፡ [ሸርቁልአውሰጥ ጋዜጣ፡ ቁ. 8407፣ 19/9/1422] ኡሳማ ቢን ላደን እራሱ በመንሀጅ ተለያይተው ሳይሆን የተሰጠውን ትእዛዝ በሚገባ ባለመፈፀሙ ምክኒያት ኋላ ላይ ቢያባሩትም የኢኽዋን ቡድን ውስጥ የታቀፈ ነበር፡፡ በዚህ ሊንክ ይግቡና አይመን አዝዘዋሂሪን ያድምጡት፡፡http://www.youtube.com/watch?v=2ghcL4sr2h4
3. የዘመናዊ የኸዋሪጅ ታሪክ መነሻው በ 19 ስልሳዎቹ ከግብፅ እስር ቤቶች ውስጥ ታስረው ከነበሩ ኢኽዋኖች ነው፡፡ በጀማል አብዱናሲር አገዛዝ ከሚደርስባቸው ሰቆቃ ላይ በጅምላ የሚያከፍረውን የሰይድ ቁጥብን አቋም ሲጨምሩበት ከመሪ እስከተመሪ በጅምላ ወደማክፈር ተሸጋገሩ፡፡ ይህንን እውነታ በርካታ የኢኽዋን ቁንጮዎች መስክረውታል፡፡ ለምሳሌ ዩሱፍ አልቀርዷዊ “አውለውያቱል ሀረከቱል ኢስላሚያህ፡ 110” በሚለው ኪታቡ ላይ፣ ፈሪድ አብዱልኻሊቅ “አልኢኽዋኑል ሙስሊሙን ፊሚዛኒልሀቅ፡ 115” ኪታቡ ላይ ይህን እውነታ አስፍረዋል፡፡ በተጨማሪ ዐልይ ዐሽማዊ (የሰይድ ቁጥብ ቅርብ ሰው ነው) በአንድ ወቅት ከሰይድ ቁጥብ ጋር ያጋጠመውን እንዲህ ይገልፃል፡- “የጁሙዐ ወቅት ሲደርስ “ተወንማ እንነሳና እንስገድ” አልኩት፡፡ አስደንጋጭ ነበር! ለመጀመሪያ ጊዜ ሰይድ ቁጥብ ጁሙዐ እንደማይሰግድ አወቅኩኝ፡፡ “ኢስላማዊ ኺላፋ ከሌለ ጁሙዐ የለም፡፡ ያለ ኺላፋ ጁሙዐ የለም!” አለ፡፡ [አትተንዚሙ አስሲሪ፡ 112]
በጥቅሉ ጠርዘኝነትና ተክፊር ከኢኽዋን አልጋ ላይ ነው የተወለደው፡፡ ለተጨማሪ ማብራሪያ ይህን ሊንክ ይከተሉ፡-http://www.andaluspress.com/ar/articles/3828.html
* * * ሊቀጥል ይችላል * * *