Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ጥያቄ፡- “ዱዓና ኢስቲግፋር ለማድረግ ከሌሎች የሰላት ማእዘናት በተለየ የመጨረሻዋን ሱጁድ ማስረዘም ምን ይሆን ብይኑ....


ጥያቄ፡- “ዱዓና ኢስቲግፋር ለማድረግ ከሌሎች የሰላት ማእዘናት በተለየ የመጨረሻዋን ሱጁድ ማስረዘም ምን ይሆን ብይኑ ይህን በማድረግ ሰላቱ ውስጥ ክፍተት ሊፈጠር ይችላልን

መልስ፡- “የመጨረሻዋን ሱጁድ ማስረዘም ሱና አይደለም፡፡ ምክኒያቱም ሱናው የሰላት ተግባራትን ተቀራራቢ ማድረግ ነው፡፡ ሩኩዕ፣ ከሩኩዕ ቀና ማለት፣ ሱጁድና በሁለት ሱጁዶች መሃል መቀመጥ፣... እንደምሳሌ መውሰድ ይቻላል፡፡ በራእ ኢብኑ ዓዚብ ረዲየላሁ ዐንሁ እንዳለው፡ “ከነብዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ጋር የሰገድኩትን ሰላት ሳስተውል መቆማቸውን፣ ሩኩዐቸውን፣ ሱጁዳቸውን፣ እንዲሁም በማሰላመታቸውና ጨርሰው በመነሳታቸው መካከል ያለው ጊዜ ተቀራራቢ ሆኖ አግኝቼዋለሁ፡፡ እናም በላጩ ይሄ ነው፡፡ ደግሞም ከሱጁድ ውጭም የዱዐ ቦታ አለ፡፡ እሱም ተሸሁድ ነው፡፡ ነብዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ዐብዱላህ ኢብኑ መስዑድን ተሸሁድ ሲያስተምሩት “ከዚያም የፈለገውን ዱዓ መምረጥ ይችላል” ብለውታል፡፡ ስለሆነም አጠረም ረዘመም የዱዐውን ቦታ ከመጨረሻው ተሸሁድ በኋላ ያድርግ ከማሰላመቱ በፊት፡፡”

ሸይ ሙሐመድ ሳሊሕ አልዑሠይሚን