Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

‹‹ሰሃባ የሚሳደብ ኡለማ›› አለን?


በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩህሩህ እጅግ በጣም አዛኝ፡፡

እውነተኛ ሙስሊም ጥሩን ይወዳል መጥፎን ይጠላል፡፡ ስለዚህ ሙስሊምን ማታለል እና መሸወድ የፈለጉ ሰዎች ጥሩውን መጥፎ መጥፎውን ጥሩ አድርገው ያቀርቡለታል፡፡

አርስቱ በግልፅ እንደሚያሳየው ‹‹ሰሃባ የሚሳደብ ኡለማ›› አለን?

ማስረጃዎቹን ማየት ነው፡፡

ኡማውን የሚያከፍር፤ የአላህ ሰም እና ባህሪያትን ውድቅ የሚያደርግ፤ ሰሃባዎችን የሚሳደብ ኡለማ አይታችሁ ታውቃላችሁን?

እስቲ የአላህ ባርያዎች ሆይ! ጥቂት እንበል በአላህ ፈቃድ፡፡ ከጥንት ጀምሮ እንደሚታወቀው የጥመት አራማጆች የያዙትን ጥመት ስሙን ቀይረው ጥሩ አስመስለው ያቀርቡታል፡፡ ሃቅን ደግሞ በመጥፎ ስም ይጠሩታል፡፡

ጥቂት ምሳሌዎች
1) የመካ ሙሽሪኮች ሽርካቸውን ‹‹ወደ አላህ መቃረቢያ፤ አማላጆቻችችን›› ብለው ጠሩት
2) ረሱል (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለምን) ‹‹ድግምተኛ፤ አባት እና ልጅን የሚለያይ›› እና የመሳሰሉትን፡፡ ልብ በል ወደ ተውሂድ እና ሱና ሲጠሩ የዚህ ዘመኖቹም ‹‹አንድነት አትበታትኑ ይላሉ›› ጥያቂ ከተውሂድ እና ሱና ውጭ አንድነት አለን?

ወደ ጥያቂው እንምጣ እና ‹‹ኡለማ ይሳደባሉ›› ለተባለው መልስ መስጠት እፈልጋለሁ፡፡
አሊም ማለት ምን ማለት ነው?

አላህን የሚፈራ፤ ቁርዓን እና ሀዲስን አጥብቆ የሚይዝ፤ የሰሃባዎችን መንገድ የሚከተል፤ ሰሃባዎችን የሚያከብር እንጂ የአላህን ስም እና ባህሪያት ውድቅ የሚያደርግ፤ ኡማውን በጅምላ የሚያከፍር እና ሰሃባዎችን የሚተች አይደለም፡፡

በዋናነት እነዚህ ወንድሞች ኡለማ ብለው የሚጠሯቸው፤ ጥብቅና የሚቆሙላቸው የሚከተለሉት ይገኙበታል፡፡
- ሀሰን አል በና
- ሰይድ ቁጡብ
- ዩሱፍ አል ቀርዳዊ
- አልመውዱዲ እና የመሳሰሉት

በጥቂቱ ስህተታቸውን እና ኡማውን ለማጥመም መሞከራቸውን በማስረጃ እንይ፡፡

1) ሀሰን አል በና የኢኽዋነል ሙስሊሚን ጀመዓ መስራች፡፡
================================================

ጥያቄው ለምን የጥንት የጠዋቱ የሰሃባዎች መንገድ ለሁሉ ነገር የሚበጅ ሆኖ ሳለ፤ ለምን አዲስ ጀመዐ መመስረት አስፈለገው?
ታድያ ማን ነው በታታኙ?
አዲስ ቡድን ይዞ መጥቶ ጥንት የነበረውን ይወቅሳል፡፡ ‹‹ከኋላ የመጣ አይን አወጣ›› እንደሚሉት ማለት ነው፡፡

ሀሰን አል በና የሚከተሉትን ብሏል
• የኩፍር ንግግር፡- መውሊድ ላይ ሆነን እንዲህ እንል ነበር‹‹ይህ ሀቢብ (ነብያችንን) ከተወዳጆቹ ጋር መጣ፤ የሁላችንንም ከዚህ በፊት የሰራነውን ወንጀል ምሯል››፡፡ አላህ ግን ‹‹ከአላህ ውጭ ማን ነው ወንጀልን የሚምር?›› ይላል፡፡ ይህ እንግዲህ ሀሰን አል በና ነው፡፡ ታድያ አንድ ሰው አብደላህ ሀረሪ አቂዳችንን ሊያበላሽ ነው የመጣው ካለ፤ ሌላ ሰው እንዲህ አይነት የአቂዳ ብክለት ያለበት ንግግር ሲናገር፤ ወይንም ወደ እንደዚህ አይነት ንግግር ሲጣራ ምን ነው አይቃወመውም??? ለምንስ ጥብቅና ይቆምለታል???
እውነት ይህ ነው ለአላህ ብሎ መውደድ ለአላህ ብሎ መጥላት????? አላህን እንፍራ
አሁንም ሀሰን አል በና እንዲህ ይላል

• ‹‹እወቅ አህሉ ሱና እና ሺዐዎች ሙስሊሞች ናቸው፡፡ ‹ላኢላሃ ኢለላህ ሙሃመዱ ረሱለላህ› የሚለው ቃል አንድ ታደርጋቸዋለች፡፡ ይህም የአቂዳ መሰረት ነው፡፡ ይህንን በተመለከተ ሱናና ሺዐ አንድ ናቸው..››::

ከሺዓዎች እምነት በጥቂቱ እንካችሁ
• ‹‹ቁርዐን ተቀንሷል፤ ሱረቱል ዊላያ የሚባል ሱራ አለ ያላሉ›› ይህ የክህደት እምነት ነው ምክንያቱም አላህ ‹‹ቁርዐንን እኛ ነን ያወረድነው እኛው እንጠብቀዋለን›› ስለሚል ነው፤
• ሀዲስንም አይቀበሉም ቡኻሪ፤ ሙስሊም፤ አህመድ የመሳሰሉትን፡፡
• እንዲህ ብለው ነሺዳ ሲያነሽዱም ተሰምተዋል ‹‹አንተ ሁሴን ከአላህ በላይ ትልቅ ነህ››
• የሺዐ መሪ ከነበሩት አንዱ ሃያቶላ ኹመይኒ እንዲህ ይላል ‹‹አነዚህ ሙሽሪኮች መዲናን መውረርና እነዛን ሁለት ጣዖቶች (አቡበክር እና ኡመርን) ማስወገድ ፈለጉ››
• ከሺዐዎች መሪ አንዱም ስለ ምዕመናን እናት አኢሻ እንዲህ አለ ‹‹አኢሻ በእርግጥ ካሃዲ(ካፊር) ናት›› የአላህ እና የረጋሚዎች እርግማን ሁሉ በርሱ ላይ ይሁን፡፡
• ከሺዐዎች አንዱም ተጠየቀ ‹‹ሱንዩ አለም ሙስሊም ይባላል ወይ?›› እሱም ‹‹አይባሉም፤ ምክንያቱም ሙስሊም የሆነ ሰው አቡበክርን እና ኡመርን አይወድም›› በማለት መለሰ፡፡
• የኡመር ኢብነል ኸጣብን ገዳይ አቡ አላ አልመጁሲን የዲን ጀግና ነው ብለው አላህን ከዚህ የተረገመ ሰው ጋር እንዲቀሰቅሳቸው ዱዐ ያደርጋሉ፤
• ኡመር የተገደለበትን ቀን የኢድ ቀን አድርገው ይዘዋል፤
• አቡበክርና ኡመር ከሸይጧን በታች ጀሀነም ውስጥ እየተቀጡ ነው ይላሉ፤
• እንደዚሁም ከነሱ ሸሆች አንዱ በVCD እየታየ ነብያችን አስሩን ጀነት ያበሰሩዋቸውን ሰሃባዎች አላህ ይርገማቸው ብሎ ዱዐ ያደርጋል፤
• ሌላው ሀሰን ነስረላህ በመባል የሚታወቀው የሂዝቦላህ መሪ ታላቁን ሰሃባ አቡሱፍያንን ሲያከፍር በቴሌቭዥን ታይቷል፤
• ኢብነል ቀይም እንደገለፃቸው ‹‹አንድም የውጭ ጠላት እስላምን ለማጥቃት አይመጣም ሺዐዎች እየመሩ ቢያመጡት እንጂ››፤ የሺዐዎች ጉድ ተነግሮ አያልቅም፡፡

ታድያ እውነት ከሺዓዎች ጋር አንድ መሆን ይቻላል???

- ሰይድ ቁጡብ
============
ኡማውን በጅምላ ማክፈሩ፤ የ21 ክፍለ ዘመን የተክፊር መሪ መሆኑ፡፡ ይህንንም ስንል እንደተለመደው በማስረጃ ነው፡፡ ሰይድ ቁጡብ እንዲህ ይላል

• ‹‹በእርግጥ በምድር ላይ ሸሪዐና ፊቅህ መመሪያው የሆነ አገርም ሆነ ማህበረሰብ የለም›› (ዚላል አል-ቁርዐን 4/2122)
• ‹‹በእርግጥ ይህ እየኖርንበት ያለው የጃሂልያ ማህበረሰብ የሙስሊም ማህበረሰብ አይደለም›› (ዚላል አል-ቁርዐን 4/2009)
• ‹‹ዛሬ ጃሂልያ ላይ ነን፡፡ የአላህ መልክተኛ ከመላካቸው በፊት ወደ ነበረው ፤ እንዲያውም ከዚህ በባሰ ዙሪያችን በጠቅላላ ጃሂልያ ነው›› (መዓሊም ፊጠሪቅ ገፅ 21. 17 እትም፣ 1991)
• ከላይ ያነበባችኋቸውን 3 የሰይድ ቁጡብ አባባሎች ኡመተል ኢስላምን ማክፈር አይደሉምን?

የሚከተሉት የነብያችን (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) አባባል፤ የሰይድ ቁጡብን አባባል ውድቅ ያደርገዋል፡፡ ‹‹በኔ መላክ ትልቁ ጃሂልያ ተወግዶላችኋል›› ‹‹ከኔ ኡመት ሀቅ ላይ እና የበላይ የሆነች ቡድን አትጠፋም፤ እነሱን የሚቃወማቸውም አይጎዳቸውም……›› የሚሉት ሀዲሶች ኡመተል ኢስላም ሙሉ በሙሉ ጨርሶ ከሳቸው መላክ በኋላ ሊጠም እና ጃሂልያ ውስጥ ሊገባ እንደማይችል ይጠቁማል፤ ከጀማዓተ አተክፊር የመጣ አመለካከት እንጂ እስልምና ውስጥ ተቀባይነት የሌለው ፍልስፍና ነው፡፡
አስገራሚ ነው፡፡ ተክፊር ሰውን ተክፊር ብሎ ሲጠራ፡፡

ድንገት ይህ ከላይ ያያችሁትን ተክፊር አይደለም ይሉ ይሆናል፡፡ እስቲ የገዛ የራሳቸው ፖለቲካ ፓርቲ ተከታይ የሆነው ዩሱፍ አልቀርዳዊ፤ ሰይድ ቁጥብ ወደ ተክፊር እንደሚጣራ እና በጅምላ እንደሚያከፍር እንዲህ ሲል ይመሰክርበታል፡፡

ዩሱፍ አልቀርዳዊ እንደ ዩሮፒያን አቆጣጠር 4 May 2004 ላይ ‹‹ሀል ዩከፊር “ሰይድ ቁጡብ” ሙስሊመል የውም? (ሰይድ ቁጡብ የዛሬ ሙስሊሞችን ያከፍራቸዋል ወይ?)›› በማለት ከታተመ አርቲክል የተወሰደ፡፡ ሰይድ ቁጡብ ስላለበት የተክፊር አስተሳሰብ እንዲህ ሲል ይገልፃል
ዩሱፍ አልቀርዳዊ ከሰይድ ቁጡብ ዚላል (7/269) የሆኑ ያህል መስመሮችን ጠቅሶ የሚከተለውን ተናገረ፡፡

‹‹ፅሁፉ ግልፅ ነው፡፡ ፀሃፊው (ቁጡብ) ማንንም ሙስሊም አይልም የሱን ሀሳብ ከሚከተሉት ውጪ፤ ይህንንም ቡድን የሙስሊም ግንባር በሎ ይጠራዋል፡፡ ይህም ቡድን እራሱን ብቻ የሙስሉሙ ኡማ ነው ብሎ ማሰብ አለበት፤ ይህንን ቡድን ያካበበው ምንም ይሁን ማን እዚህ ጀመዐ ውስጥ ያልገቡ ሁሉ ጃሂልያ ናቸው፤ ሰዎቹም የጃሂልያ ሰዎች ናቸው፡፡ ማለትም ሙሽሪክና ካፊር ናቸው ከእስልምና ምንም ድርሻ የላቸውም ቢሰግዱም፤ ቢፆሙም፤ ዛካ ቢሰጡም ሃጅ ቢያደርጉም፡፡ ይህም ማለት ሁሉም ሙስሊሞች ከመካ ሙሽሪኮች ጋር አንድ ናቸው ነብያችን የተላኩበት ወቅት የነበሩት እንደማለት ነው፤ የሱም ዳዕዋ ከነብያችን (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ዳዕዋ ጋር እኩል ነው እንደማለት ነው፤ በዛ ዳዕዋ ያመነ (ቁጡብ በሚያምንበት) ወደ እስልምና ይገባል፤ ያላመነም ጃሂልያ፤ ካፊር ነው፤ ደሙንም ማፍሰስ ይበቃል››፡፡ ያነበባችሁት የዩሱፍ አልቀርዳዊ ከኢኽዋን አባሎች ዋናዎቹ ውስጥ አንዱን ነው፡፡ ሰይድ ቁጡብ የሚናገራቸው ሁሉ ‹‹የኸዋሪጅ መንገዶች ናቸው (የሙስሊምን ደም ሀላል ማድረግ፤ ልክ ኸዋሪጆች የሰሃባዎችን ደም ሃላል እንዳደረጉት)››

አሁንም ዩሱፍ አልቀርዳዊ ‹‹አውለዊያት አል-ሀረካቲል ኢስላሚያ (የእስልምና እንቅስቃሴዎች ተቀዳሚያቸው)›› በሚባለው መፀሃፉ ገፅ 110 ላይ እንዲህ ይላል

‹‹በዚህም ወቅት ነበር የሸሂድ ሰይድ ቁጡብ መፀሀፎች ብቅ ያሉት የመጨረሻ ሃሳቦቹን የያዙት፡፡ የኡማውን በጠቅላላ መክፈር የሚያረጋግጡ የሆኑት …. የሰው ልጅን በጠቅላላ የተወገዘውን ጂሃድ እነሱ ላይ ማወጅ …፡፡ ይህንን በግልፅ መዐሊም ፊጠሪቅ፤ ፊዚላሊል ቁርዐን እና አል-ኢስላም ወሙሻኪላት አል-ሃዳራሀ በሚባሉ መፀሃፎቹ ላይ አስቀምጧቸዋል››፡፡ ከምስክርነቱ አልፎ የተሰመረበትን ቃል ልብ ብለዋል ሸሂድ፤ የአላህ መልክተኛ በግልፅ ኢማሙ ቡኻሪ በዘገቡት ሀዲስ ላይ ‹‹እገሌ ሸሂድ ነው አትበል›› ብለዋል፡፡

ይህ ነው የሰይድ ቁጡብ ተክፊር፡፡ ኡማውን በጅምላ ሲያከፍር፡፡ የሱን ኪታቦች ኢትዬጵያ ላይ በተለይ በዩኒቨርሲቲ አካባቢ ላሉ ተማሪዎች ሲያሰራጩት ነበር፡፡ ለዛም ሲባል፤ ይህ ሃቅ ሲጋለጥ ያላቸው አማራጭ፤ አሁንም መጥፎውን ጥሩ አድርገው ማቅረብ ነው፡፡ ሰይድ ቁጡብ ‹‹ሸሂድ ኡለማ ነው›› ብለው ይናገራሉ፡፡ ሸሂድ የሆነውን አላህ ብቻ ነው የሚያውቀው፡፡ ኢማሙ ቡኻሪም ‹‹ይህ ምዕራፍ ነው፤ እገሌ ሸሂድ ነው አይባልም›› ብለው ምዕራፍ አዘጋጅተው አንድን ሰው ስም ጠርቶ አላህ እና መልክተኛው (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ከመሰከሩለት ውጭ፤ እገሌ ሸሂድ ነው ማለት እንደማይቻል ያስቀመጡበት፡፡

2) ሰሃባዎችን ማጣጣሉ እናም ብሎ ኡስማን ኢብን አፋን (ረድየላሁ አንሁ) ላይ የተደረገውን መፈንቅለ መንግስት እያደነቀ መፃፉ፤ እነዚህን ሁሉ አዳለቱል ኢጅቲማእያ የሚባለው ኪታቡ ላይ ይገኛሉ፡፡
ጋዜጠኛው (ጋዜጠኛ ያሉት ሸይህ አልባኒ ናቸው) ሰይድ ቁጡብ አረብኛን ስለቻለ እና ጋዜጠኛ ስነ ነበረ ብቻ፤ ዲንን ሳይማር ዝም ብሎ ከስሜቱ እና ከቢድዐ ‹‹ሺዐ፤ ረዋፊዳ›› እምነት ተነስቶ ታላቁ ሰሃባ ኡስማን ኢብን አፋን (ረድየላሁ አንሁም) ላይ የሚከተሉትን አዳለቱል ኢጅቲማኢያ የተባለ መፀሃፉ ላይ አስፍሩዋል፡፡

1)‹‹አልይ ሶስተኛው ኸሊፋ አለመሆኑ ፊትና ነበር›› (ገፅ 191 5ኛው እትም፤ 162 12ኛው እትም)
ይህ እንደሚታወቀው ከሺዐ ክፍል ውስጥ ከሆኑት ውስጥ የአንዳቸው እምነት ነው፡፡ ታላቁ ሰሃባ አብደላህ ኢብን መስኡድ (ረድየላሁ አንሁም) ኢማሙ ቡኻሪ በዘገቡት ሰሂህ ሀዲስ እንዲህ ይላል ‹‹በነብያችን (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ዘመን ከነብያችን ቀጥሎ ምርጥ ሰው አቡበክር ነው፤ ከዛም ኡመር ነው፤ ከዛም ኡስማን ነው እንል ነበር››፡፡ ነብያችን (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ልክ ባይሆን ኖሮ ይህ አባባል በዝምታ አያረጋግጡትም ነበር፡፡ ሰይድ ቁጡብ ‹‹አልይ ሶስተኛው ኸሊፋ አለመሆኑ ፈተና ነበር›› ሲል፤ ፈተናው ለማን ነው፡፡ ለሙስሊሞች፤ ለሱኒዬች ወይንስ ለራፊዳዎች???

ሰይድ ቁጡብ ማለት ከኢራኖች በስሙ የፖስታ ቴምብር ተሰርቶለታል፡፡

2)ኡስማን የመራው ዘመን በሁለቱ ሸሆች (አቡበክር እና ኡመር) እና በአልይ መሃል የነበረ ክፍት ዘመን ነው (ገፅ 206 5ኛው እትም)

ሰይድ ቁጡብ ምን ለማለት ፈልጎ ነው??? ይህ ጋዜጠኛ ማን ሆኖ ነው ኡስማን የመራው ዘመን ክፍት ዘመን ነው የሚለው??? እውነታው ግን ሰይድ ቁጡብ እንደሚለው ሳይሆን፤ ታላቁ ሰሃባ አብደላህ ኢብን መስዑድ ኡስማን ስልጣን ላይ ሲወጣ እንዲህ አለ ‹‹ከቀሩት ውስጥ ምርጣችንን ነው የመረጥነው፤ ምርጣችንንም በመምረጥ ላይም አልተሳሳትንም›› (አጠበቃት አል ኩብራ 3/63)

ሌላው ኡስማን የሰራውን አደለም ኸሊፋ ሆኖ፤ ከኸሊፋነት በፊት በሰራው ስራ የአላህ መልክተኛ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) እንዲህ ይላሉ

በነብያችን አንደበት ኡስማን ኢብን አፋን የተቡክ ዘመቻን ሲወጡ 100 ግመል በመስጠቱ የአላህ መልክተኛ እንዲህ ብለዋል ‹‹ኡስማን የሰራውን ቢሰራ ከዚህ በኋላ አይጎዳውም››
ታድያ ወገኖቼ የማንን ንግግር ነው የምትቀበሉት??? የነብያችንን (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ወይንስ የራፊዳ፤ ሺዓዎች፤ የቢድዓ አራማጆችን የንፍቅና ንግግር??????????????????????????????????????????????????????????

3)የሚያሳዝነው ኡስማን ለኸሊፋነቱ የደረሰው ሽማግሌ እና ወኔው በደከመበት ሰዐት ነው፤ ለእስልምናም የሚፈለገውን ግብ መድረስ አልቻለም (ገፅ 186 5ኛው እትም)
እንደ ሰይድ ቁጡብ እና እንደ ሙናፊቆች አመለካከት የእስልምና ግብ ምን ማለት ይሆን?????????? ነብያችን (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) አይደሉ እንዴ ‹‹የኔን እና የቅን ምትኮቼን (ኹለፋኡ ራሺዲን) ፈለግ ተከተሉ ያሉት››??????

ነብያችን (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) አይደሉ እንዴ ለኡስማን ኢብን አፋን ልጃቸውን ኡሙ ኩልሱምን ዳሩለት ሞተችበት፤ ሩቅያን ዳሩት ሞተችበት፤ ካዛ ም እንዲህ አሉ ‹‹ሶስተኛ ቢኖረኝ እድርህ ነበር››፡፡ ነብያችን ለዚህ ታላቅ ሰው ልጃቸውን እንዲህ የዳሩለት፤ ፍትሃዊነቱን፤ ቅንነቱን እና ታላቅ ሰውነቱን አይተው አይደለምን??????????????????????????????

4)ኡስማን ላይ የተደረገውን መፈንቅለ መንግስትና የግፍ ግድያ በማድነቅ እንዲህ ይላል ‹‹በእስልምና እይታ ላየው፤ መፈንቅለ መንግስቱ በአጠቃላይ የእስልምና መንፈስ ነበረው›› (ገፅ 160-161)
እንግዲህ ልብ በሉ፤ ኡስማንን የገደሉት ኸዋሪጆች እነዛ የጀሃነም ውሻዎች ናቸው፤ ግድያውን ያቀናበረው ደግሞ አብደላህ ኢብን ሰባዓ አል የሁዲ (ላዕነቱላኢ አለይሂ) ነው፡፡ ሌላ ማብራሪያ አያስፈልግም ነብያችን (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ስለ ኡስማን ፈተና አስመልክተው የተናገሩትን እና የኡስማን ገዳዬች እነማን እንደሆነ ሲተነብዩ እንዲህ ይላሉ

• የአላህ መልክተኛ ከአቡበክርን፤ከኡመርን እና ከኡስማን ጋር እሁድ ተራራ ላይ በወጡበት እሁድ ተንቀጠቀጠች የአላህ መልክተኛው በእግራቸው በታ አደረጓትና እንዲህ አሉ ‹‹የያዝሽው እኮ ነብይ፤ ሲዲቅ እና ሸሂዶች ነው››፡፡ ሲዲቁ አቡበክር ሲሆን ሸሄዶች ኡመርና ኡስማን ናቸው

• ኡስማን ያለ አግባብ እንደሚገደል የአላህ መልክተኛ ተናግረዋል፡፡ አብደላህ ኢብን ኡመር እንዲህ ይላል የአላህ መልክተኛ ‹‹ፊትና እንደሚመጣና እንደሚያልፍ ተናገሩ፡፡ ከዚያም ፊቱን የተሸፈነው ሰው በግፍ ይገደላል አሉ›› ሙስነድ ኢማሙ አህመድ 2/115

• ከዐብ ኢብን ኡጅራ እንዲህ ይሉናል፤ የአላህ መልክተኛ ፊትና እንደሚመጣና ወዲያውም እንደሚያልፍ ተናገሩ፡፡ አንድ ጭንቅላቱን የተሸፈነ ሰው አለፈ የአላህ መልክተኛም ‹‹ያን ቀን ይህ ሰው ሀቅ ላይ ነው›› እየሮጥኩ ሄጄ የኡስማንን እጅ ይዤ ወደ አላህ መልክተኛ አዞርኩና ‹‹ይህ ሰው›› ብዮ ጠየኳቸው አሳቸውም ‹‹አዎን እሱ›› አሉኝ፡፡ (ሰሂህ ሱነን ኢብን ማጃህ 1/24 (111))

• የምእመናን እናት አኢሻ (አላህ ስራዋን ይውደድላትና) እንዲህ ትላለች የአላህ መልክተኛ ኡስማንን አስጠርተው አዋሩት …… የመጨረሻ ንግግራቸው ጀርባውን ይዘው እንዲህ አሉት ‹‹ኡስማን ሆይ አላህ ኩታን ያለብስሃል (ስልጣንን) ሙናፊቆቹ አውልቀው ካሉህ እኔን እስክትገናኘኝ እንዳታወልቀው፡፡ኡስማን ሆይ አላህ ኩታን ያለብስሃል ሙናፊቆቹ አውልቀው ካሉህ እኔን እስክትገናኘኝ እንዳታወልቀው፡፡ኡስማን ሆይ አላህ ኩታን ያለብስሃል ሙናፊቆቹ አውልቀው ካሉህ እኔን እስክትገናኘኝ እንዳታወልቀው፡፡›› ሙስነድ ኢማሙ አህመድ፡፡

ጥያቄ ሰይድ ቁጡብ የት ነው ያለው የአላህ መልክተኛን ቃል በመቃወም ላይ ‹‹በእስልምና እይታ ላየው፤ መፈንቅለ መንግስቱ በአጠቃላይ የእስልምና መንፈስ ነበረው›› የሙናፊቆች ግድያ እንዴት እስላማዊ መንፈስ ይኖረዋል?

የአላህ ባሪያዎች ሆይ! ይህ ነው የሰይድ ቁጡብ እውነታ፡፡ ሰይድ ቁጡብ ብዙ መፀሃፍ ፅፏል ብቻ ሳይሆን መባል ያለበት፤ የፃፈው ምንድን ነው መባል አለበት፡፡
ነብያችን እና ሰለፎች ስለ ኡስማን ኢብን አፋን (ረድየላሁ አንሁም) ምን ይላሉ
• ኡስማን የጀነት ነው
• አንድ ቀን ቤት ውስጥ በተቀመጡበት ታፋቸው ተገልፆ ነበር፤ አቡበክር ገባ አልሸፈኑትም፤ ኡመር ገባ አልሸፈኑትም፤ ኡስማን ገባ ሸፈኑት ተጠየቁ ለምን እንዳደረጉ፤ እሳቸውም እንዲህ አሉ ‹‹ኢስማንን አደለም በምድር ያለ በሰማይ ላይ ያለ መላኢካ ያፍረዋል››
• ነብያችን ለኡስማን 2 ሴት ልጃቸውን መዳራቸው ቅፅል ስሙም ‹‹ዙኑረይን›› የሁለቱ ኑሮች ባለቤት፤ አንዷን ድረውት ስትሞት ሌላኛዋን ሰጡት፡፡ አንድ ነብይ ሁለት ሴት ልጁን ሲሰጥ በሰው ልጆች ታሪክ ታይቶ አይታወቅም፡፡ እንዲያውም ሶስተኛ ቢኖረን እንደግምህ ነበር ብለውታል ይባላል
• በነብያችን አንደበት ኡስማን ኢብን አፋን የተቡክ ዘመቻን ሲወጡ 100 ግመል በመስጠቱ የአላህ መልክተኛ እንዲህ ብለዋል ‹‹ኡስማን የሰራውን ቢሰራ ከዚህ በኋላ አይጎዳውም››
• የአላህ መልክተኛ እንዲህ አሉ ‹‹ትናንት ማታ መልካም ሰው ታየ (በህልም) እናም አቡበክር ከአላህ መልክተኛ ጋር፤ኡመር ከአቡበክር ጋር እና ኡስማን ከኡመር ጋር የተያያዙ ናቸው›› ጀሪር ኢብን አብዲላህ (አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸው) እንዲህ ይላሉ ‹‹የአላህ መልክተኛን ተለይተን ስንሄድ እንዲህ አልንመልካሙ ሰው የአላህ መልክተኛ ናቸው፤ አንዱ ባንዱ መተሳሰራቸው አላህ መልክተኛውን በላከበት ጉዳይ ላይ ሀላፊ ይሆናሉ›› (ሱነን አቢ ዳውድ 2/513)
• ኡስማን ስልጣን ላይ ሲወጣ አብደላህ ኢብን መስዑድ እንዲህ አለ ‹‹ከቀሩት ውስጥ ምርጣችንን ነው የመረጥነው፤ ምርጣችንንም በመምረጥ ላይም አልተሳሳትንም›› (አጠበቃት አል ኩብራ 3/63)
• የአላህ መልክተኛ ከአቡበክርን፤ከኡመርን እና ከኡስማን ጋር እሁድ ተራራ ላይ በወጡበት እሁድ ተንቀጠቀጠች የአላህ መልክተኛው በእግራቸው በታ አደረጓትና እንዲህ አሉ ‹‹የያዝሽው እኮ ነብይ፤ ሲዲቅ እና ሸሂዶች ነው››፡፡ ሲዲቁ አቡበክር ሲሆን ሸሄዶች ኡመርና ኡስማን ናቸው
• ኡስማን ያለ አግባብ እንደሚገደል የአላህ መልክተኛ ተናግረዋል፡፡ አብደላህ ኢብን ኡመር እንዲህ ይላል የአላህ መልክተኛ ‹‹ፊትና እንደሚመጣና እንደሚያልፍ ተናገሩ፡፡ ከዚያም ፊቱን የተሸፈነው ሰው በግፍ ይገደላል አሉ›› ሙስነድ ኢማሙ አህመድ 2/115
• ከዐብ ኢብን ኡጅራ እንዲህ ይሉናል፤ የአላህ መልክተኛ ፊትና እንደሚመጣና ወዲያውም እንደሚያልፍ ተናገሩ፡፡ አንድ ጭንቅላቱን የተሸፈነ ሰው አለፈ የአላህ መልክተኛም ‹‹ያን ቀን ይህ ሰው ሀቅ ላይ ነው›› እየሮጥኩ ሄጄ የኡስማንን እጅ ይዤ ወደ አላህ መልክተኛ አዞርኩና ‹‹ይህ ሰው›› ብዮ ጠየኳቸው አሳቸውም ‹‹አዎን እሱ›› አሉኝ፡፡ (ሰሂህ ሱነን ኢብን ማጃህ 1/24 (111))
• የምእመናን እናት አኢሻ (አላህ ስራዋን ይውደድላትና) እንዲህ ትላለች የአላህ መልክተኛ ኡስማንን አስጠርተው አዋሩት …… የመጨረሻ ንግግራቸው ጀርባውን ይዘው እንዲህ አሉት ‹‹ኡስማን ሆይ አላህ ኩታን ያለብስሃል (ስልጣንን) ሙናፊቆቹ አውልቀው ካሉህ እኔን እስክትገናኘኝ እንዳታወልቀው፡፡ኡስማን ሆይ አላህ ኩታን ያለብስሃል ሙናፊቆቹ አውልቀው ካሉህ እኔን እስክትገናኘኝ እንዳታወልቀው፡፡ኡስማን ሆይ አላህ ኩታን ያለብስሃል ሙናፊቆቹ አውልቀው ካሉህ እኔን እስክትገናኘኝ እንዳታወልቀው፡፡›› ሙስነድ ኢማሙ አህመድ፡፡

ጥያቄ ሰይድ ቁጡብ የት ነው ያለው የአላህ መልክተኛን ቃል በመቃወም ላይ ‹‹በእስልምና እይታ ላየው፤ መፈንቅለ መንግስቱ በአጠቃላይ የእስልምና መንፈስ ነበረው›› የሙናፊቆች ግድያ እንዴት እስላማዊ መንፈስ ይኖረዋል?

• ኢብን ኡመር (አላህ ስራቸውን ይውደድላቸውና) እንዲህ ይላሉ ‹‹የአላህ መልክተኛ (ሰላትና ሰላም በሳቸው ላይ ይሁን) በነበሩበት ወቅት በሰዎች መሃል እናበላልጥ ነበር፤ አቡበክርን ከዛ ኡመርን ከዛ ኡስማንን እንመርጥ ነበር›› ኡማሙ ቡኸሪ
ኢብን አባስ ይህንን አንቀፅ ይቀራና هَلْ يَسْتَوِى هُوَ وَمَن يَأْمُرُ بِٱلْعَدْلِ ۙ وَهُوَ عَلَىٰ صِرَٰطٍ مُّسْتَقِيمالنحل: ٧٦‹‹ይህ ነበር ኡስማን›› ይል ነበር (ተፍሲር ኢብን ከሲር 2/579)
እንግዲህ የአላህ ባርያዎች! እኛ ሰሃባን የሚሳደብ ሰው እሱ ሰሃባን እንደተሳደብው ባንሰድበውም፤ በግልፅ ግን ለሰሃባዎች ጥብቅና ቆመን ሃቁን እናወጣለን፡፡ እነዚህ ናቸው እንግዲህ ያለ ማስረጃ የሚያወሩት፡፡ አገር ውስጥ ያሉ ኡለማዎች ስም ላሉት፤ አገር ውስጥ ያሉ የሚከበሩ ኡለማዎች የእውነት አሉ፡፡ እንደዚህ ደግሞ የሰይድ ቁጡብ እና መሰሎቹ ጠበቆች አሉ፡፡ ማንም ይሁን ማን ለሰሃባዎች ተሳዳቢ፤ ሰይድ ቁጡብ ጥብቅና ቆሞ ቢመጣ አንሰማውም፡፡ እንቃወመዋለን፡፡

ተክፊር እና ሰሃባ ተሳዳቢ ለኡማው አሳቢ መስሎ በውሸት ተሞልቶ፤ ሃቅን በባጢል ስም፤ ባጢልን በሃቅ ስም እየጠራ ማንንም ሊያታል አይችልም፡፡ መልስ ይሰጠዋል፡፡ ስለዚህ ሰሃባን የሚሳደብ ሰው እናንተ እንደምትሉት ‹‹ኡለማን ይሳደባሉ›› ብትሉንም፤ እኛ አንሳደብም፤ የናንተን የስድብ መዝገበ ቃላት አየነው፤ ስማችሁን ቀይራችሁ ብትሳደቡ፤ መላኢካዎች በስማችሁ ነው የሚመዘግቡት፡፡
ሰሃባን ለሚሳደብ ሰው ጥብቅና ተቁሞ ድል የለም ውርደት እንጂ፡፡

- ዩሱፍ አል ቀርዳዊ፡-
========================

ይህ ሰው በዘመናችን የስሜት ተከታዬች ከነሱ ስሜት ጋር የሚሄድ ፈትዋ ስለሚሰጣቸው ሙፍቲ ይሉታል፡፡ ወጣቶችን በማጥመም የታወቀ ሰው ነው፡፡ እስቲ ከራሱ ንግግሮች እናንብብ
• የኩፍር ንግግሩ፡- የጁምዐ ሁለተኛ ኹጥባ ላይ የሚከተለውን ተናግሯል ‹‹ኹጥባዬን ጨርሼ ከመውረዴ በፊት ትንሽ ስለ እስራኤል ምርጫ መናገር እፈልጋለሁ፡፡ አረቡቹ በጠቅላላ ነዳህ ጲሪዝ ያሸንፋል ብለው ተስፋቸውን ጥለው ነበር፤ ነገር ግን ተሸነፈ፡፡ ከእስራኤል የምንወድላትም ይህንን ነው፡፡ የእኛም ሀገር እነደዚህች አገር እንድትሆን እንመኛለን እንፈልጋለን፡፡ በጥቂት ሰዎች አማካኝነት ሲመራ የነበረው ስልጣኑን አጥቷል፡፡ አገራችን ላይ እንደለመድነው 94% ወይንም 95% (ድምፅ) አይደለም ነገር ግን 99% (አዎን 99%፤ ምንድን ነው ይሄ?) አላህ ለሰው ልጆች እራሱን ተመራጭ አድርጎ ቢያቀርብ ይህንን ያህል ድምፅ አያገኝም ፡፡ይሄ (አረብ አገር ላይ የምናየው ምርጫ) ውሸት ማጭበርበር እና የመሳሰሉት እንጂ ሌላ አይደለም፡፡ እስራኤልን እሰየው እንላታለን››፡፡ ምድር በዚህ የኩፍር ንግግር አትሰነጠቅምን? ለሸይኽ ኢሰይሚን (አላህ ይዘንላቸውና) ይህ ቃል በድምፅ ተከፍቶላቸው ከሰሙ በኋላ የሚከተለውን ተናገሩ ‹‹በአላህ እጠበቃለሁ፡፡ ይህ ሰው መቶበት ግድ ይለዋል፤ እምቢ ካለ እንደ ሙርተድ (ሀይማኖቱን እንደከዳ ሰው) ይገደል፡፡ ፍጡራንን ከፋጣሪ ስላስበለጠ፡፡ ተውበት ካደረገ አላህ የባሪያውን ወንጀል መሀሪ ነው፤ ካልሆነ ውላቱል አምር (የሙስሊም መንግስት) አንገቱን (በሰይፍ) ይቀንጥሰው፡፡››
• ዘፈንና ሙዚቃን መፍቀዱ፤ እንዲያውም ጥሩ ነገር ነው ማለቱን ‹‹አል ሀራም ወል ሀላል›› ‹‹ፈትዋ ሙዐሲራ›› እና በመሳሰሉ መፀሃፎቹ መግለፁ፡፡ እራሱ እንደተናገረው ‹‹የፋይዛ አህመድ፤ ሻዲያ፤ ኡሙ ኩልሱም፤ ፊሩዝ እና የመሳሰሉትን ሴቶች ዘፈን መከታተል ይወድ እንደነበር ጠቅሷለል›› (አራያህ የሚባል የኳታር መፅሄት ቁጥር 5969 ቀን 19/ ጁማዱል ኡላ 1419 ሂጅሪ)፡፡ ዘፈን ሃራም ለመሆኑ የነብያችን አንድ ሀዲስ ሀቅን ለሚፈልግ ትበቃዋከች ‹‹የአላህ መልክተኛ (ሰላትና ሰላም በርሳቸው ላይ ይሁንና) ከኔ ኡመት ሰዎች ይመጣሉ ለወንድ ልጅ ሀር ልብስን የሚፈቅዱ፤ መጠጥን እና የሙዚቃ መሳሪያን የሚፈቅዱ›› ኢማሙ ቡኻሪ ዘግበውታል፡፡ የአላህ ባሪያዎች እንደው እናንተው ፍረዱት፡፡
ስለ ሙዚቃው ማብራሪያ አያስፈልገውም፡፡
እንዚህን እና ጠበቆቻቸው ሲጋለጡ ነው እንግዲህ ‹‹ኡለማ ተሰደብ›› የሚሉት

- አልመውዱዲ
========================

ይህም ግለሰብ የነብያችንን (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ሀዲስ እንዲህ ሲል ያጣጥላል፡፡
• ረሳኢል ወምሳኢል በሚባል መፀሃፉ ገፅ 57፣ 1351 ሂጅራ እትም እንዲህ ይላል ‹‹የአላህ መልክተኛ ደጃል በሳቸው ጊዜ ወይንም በሳቸው ቅርብ ጊዜ ይወጣል ብለው ያስቡ ነበር፡፡ ነገር ግን 1350 አመት በዚህ ጥርጣሪ አልፋል፤ ብዙ ክፍለ ዘመናት እስካሁን ግን ደጃል አልመጣም፡፡ ይህ የሚያሳየው የሳቸው (ሰላትና ሰላም በርሳቸው ላይ ይሁን) ግምት ልክ አለመሆኑን ነው›› በ1362 ሂጅራ እትሙ የሚከተለውን አረፍተ ነገር ጨምሮበታል ‹‹1350 አመት አልፏል……….ደጃል እስካሁን አልመጣም፡፡ ይህ ነው እውነታው››፡፡ ገፅ 55 ላይ እንዲህ ይላል ‹‹ስለደጃል የመጡት ሀዲሶች ጠቅላላ የመልክተኛው አስተያየቶችና ግምቶች ናቸው፡፡ መልክተኛውም (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) እዚህ ጉዳይ ላይ ጥርጣሪ ነበራቸው››፡፡ የአላህ ባሪያዎች ይህ አባበሉ ግልፅ የነብያችንን ንግግር አለመቀበልና፤ የደጃልን መምጣት ማስተባበል አይደለምን፡፡ አላህ ስለ መልክተኛው ‹‹መልክተኛው ከስሜቱ አይናገርም፤ እኛ መለኮታዊ ራእይ (ወህይ) ያወረድንለት ቢሆን እንጂ›› ይህ የአላህን ቃል ማስተባበል አይሆንምን?

ስለ ነብየላህ ዩሱፍ (አለይሂ ሰላም) እንዲህ ይላል ‹‹ይሂ (የዩሱፍ የግብፅ አስተዳዳሪ ለመሆን መጠየቁ) የገንዘብ ሚኒስቲር መሆን ብቻ ፈልጎ አይደለም አንዳንድ ሰዎች እንደሚገምቱት፡፡ ነገር ግን የአምባገነንነት ፍላጎት ነው፡፡ በመጨረሻም ሰይድና ዩሱፍ (አልይሂ ሰላም) እና ሞሶሎኒ ጣሊያን ውስጥ በዚህ ጊዜ እየተዝናናበት ያለው ስልጣን አንድ ነው››፡፡(ተፍሂማት ክፍል 2 ገፅ 122፣ 5ተኛ እትም) ውድ አንባቢያን ይህ ኩፍር አይደለምን? ዩሱፍ (አልይሂ ሰላም) ወንድሞቻቸውን እንኳን ይቅር ብለዋል አይደለም የግብፅ ህዝብ ላይ አንባገነን ሊሆኑበት ቀርቶ፡፡ ሌላው የአላህን ነብይ ከማን ጋር እያመሳሰለ እንደሆነ ተርድተዋልን? ከሞሶሎኒ፤ ከካፊር ጋር፡፡ አላህ ይጠብቀን

‹‹ኡለማ የሚሳደቡ>> እያሉ የውሸት ማምታቻ የሚነዙ ሰዎች ስለ መሬዎቻቸው ‹‹ኡማውን ማክፈር፤ ነብያት ላይ ማላገጥ፤ ሰሃባ መተችት…..›› የት ጥለውት ነው፡፡ አመልሽን በጉያ ስንቅሽን ባህያ፡፡
ውድ ሙስሊም ወንድም እና እህቶች ሆይ! የተናገረ ሁሉ አይታመንም፡፡ ማስረጃ ግድ ነው፡፡

አስገራሚው ሼኽ አብዱልአዚዝ ኢብኑ ባዝ፤ሼኽ ሙሃመድ ናስሩዲን አልባኒ፤ ሸኽ ሙሃመድ ቢን ሷሊህ አል ኢሰይሚን እና ሌሎች ኡለማዎችን እንደሽፋን ሊጠቀሙባቸው ይሞክራሉ፡፡ አሳዛኙ አነዚህ ኡለማዎች እነ ሰይድ ቁጡብ ላይ ያላቸውን ከባድ አቋም አለማወቃቸው ወይንም አውቀው እንዳላወቁ ‹‹እያወቁ አለቁ›› እንደተባለው መሆናቸው ነው፡፡

አላህ ሆይ! ሃቅን በሃቅነቱ አሳየን የምንቀበለው አድርገን፤ ባጢልን በባጢልነቱ አሳየን የምንርቀውም አድርገን፡፡

የአላህ ሰላት እና ሰላም በነብያት መደምደሚያ፤ በቤተሰቦቻቸው፤ በባልደረቦቻቸው፤ ሃቅን በተከተለ ላይ ሁሉ ይሁን፡፡