Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ለዐብዱልዐዚዝ ዐልይ ውዥንብር የተሰጠ ምላሽ


ለዐብዱልዐዚዝ ዐልይ ውዥንብር የተሰጠ ምላሽ
1. ((መሳደብ አና መዝለፍ የሃቅ ጎዳና ለሚመስላችሁ ወንድም እና እህቶቼ))
መልስ፡- እውነታውን ለማየት ፖሰቶችህን ማየት ብቻ በቂ ነው፡፡ ማጥላላት፣ ማንቋሸሽ፣ መናቅ ፖሰቶችህ ውስጥ በሰፊው የሚታዩ ነገሮች ናቸው፡፡
2. ((በሃገራችን በተለያዩ ጊዜያቶች የተለያዩ አስተሳሰብ ያላቸው ጎጠኛ ቡድኖች ሙስሊሙን ኡማ ግራ ሲያጋቡት እና ሲረብሹት ይስተዋላል፡፡ ይህ ችግር የሚመነጨው ከእውቀት ማነስ እና በጭፍን ወገንተኝነት በሚመነጭ አካሄድ ነው፡))
መልስ፡- እውነት ብለሃል፡፡ ግን ከነዚህ በሀገራችን ከሚገኙ ጎጠኛ ቡድኖች ውስጥ አንዱ ኢኽዋን ነው፡፡ ያለ እውቀት ከሚያወሩት ደግሞ አንዱ አንተ ነህ፡፡ እስኪ ዐብደላህ አልጉማይማን ማነው? እስኪ መቼ ነው ስለ ኢኽዋን አደጋ ያስተማራችሁት?
3. ((ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ደግሞ በተለያዩ ማህበራዊ ሚዲያዎች የኡለሞችን እና ዱአቶችን ስም የማጥፋት፣የመሳደብ፣የመዝለፍ፣…))
መልስ፡ አዎ፡፡ ልክ አሁን አንተ እንደምታደርገው፡፡ እኔ ልንገርህ ከታሰሩት ውስጥ ፈውዛንን ሲሳደብ የነበረ አውቃለሁ፡፡ የምትሟገትላቸው ሰባኪዎች ብዙዎቹ ሰሐባ ለሚሳደበው ሰይድ ቁጥብ የሚከላከሉ ናቸው፡፡ የሰሐባ ክብር አያሳስባችሁም፣ የሙብተዲዖቹ ግን ያስጨንቃችኋል፡፡ ይሄ ነው ለኢስላም መቆርቆር?
4. ((ከኛው አስተሳሰብ ውጪ ያለው የዚህ ቡድን ተከታይ ነው፣ እከሌ እንዲህ ነው፣እነ እከሌ አላማቸው ስልጣን ነው ወዘተ የሚሉ የመንደር ወሬዎች በዳዕዋ ሽፋን ለሰዎች ሲደርሱ ማደመጥ የተለመደ ሆኗል፡፡ ይህን የሚያደርጉት ወጣቶችም አሊሞች ስር ቁጭ ብለው የቀሩ፣በርካታ እውቀቶችን ያካበቱ ሳይሆኑ ግልብ እውቀት እና እንዲሁ ከኢንተርኔት እና በእንግሊዝኛ የተተረጎሙ መፅሃፎች በማንበብ ብቻ ትንሽ እውቀትን የያዙ ናቸው፡፡
መልስ፡- በመጀመሪያ የሐሰን አልበናን እና የተከታዮቹንን ግግሮች ብታስተውልና ሚዛናዊ ብትሆን እኛ ብቻ ሐቅ ላይ ሲልህ ታገኘው ነበር፡፡ እሱ ያልታየህ ስለማታውቅ ይሁን ከነሱው ሆነህ ይሁን አላውቅም፡፡ ባለ ግልብ እውቀቶቹ እነማን እንደሆኑ ለዚህ ጥሩ ማሳያ ከሚሆኑት ውስጥ አንዱ አንተ ነህ፡፡ የዑለማዎችን ንግግር ያለ መልእክቱ ከኢኽዋን መከላከያ አድርገህ ልታቀርብ ትሞክራለህ፡፡ እነ አልባኒ፣ ኢብኑ ባዝ፣ … ኢኽዋን ላይ ያላቸው ጠንካራ አቋም የሚታወቅ ነው፡፡ ኢብኑ ባዝ ረሒመሁላህ ኢኽዋንን ከ 72ቱ ጠማማ አንጃዎች ውስጥ መድበውታል፡፡ አልባኒም ረሒመሁላህ እንዲሁ ኢኽዋን የሱና ጠላት እንደሆነና አደጋውም ከአይሁዶች አደጋ ሊከፋ እንደሚችል ነው የተናገሩት፡፡የሚገርመው ግን ለባጢልህ የምታጣቅሳቸውን ዓሊሞች ስም እንኳን በትክክል አለማወቅህ ነው፡፡ እስኪ ጉማይማን የሚበለው ማነው? የአፃፃፍ ግድፈት እንዳይባል በተለያየ ቦታ ደጋግመህ ተጠቅመኸዋል፡፡ ደግሞም አታፍርም ታፔላ መለጠፍ ትላለህ፡፡ መድኸሊ፣ ተክፊር፣ የሁዳ የምትሏቸውስ ታፔላ እየለጠፋችሁላቸው አይደለም? እስኪ የጠቀስካቸው ሸይኽ ኢብኑ ባዝ፣ ኢብኑ ዑሠይሚን፣ አልባኒ ስለመድኸሊ ምን እንደሚሉ ተናገር፡፡ መድኸሊን በሚገርም ሁኔታ እያደነቁ እንጂ እንዳንተ የቡድን መጠሪያ አድርገው አይደለም የሳሉት፡፡ አንተ ግን ፕሮፋይል ፒክቸርህ ይናገራል፡፡ ደግሞ በአቋምህ ኮንፊደንስ እንደሌለህ ፐሮፋይል ፒክቸርህ ይመሰክራል፡፡ በሰፊው የተሰራጨውን የሳዳትን ፒክቸር ወስደህ ተጠቀምክ፡፡ ከዚያም ብትጠነቀቅም በሚያስፎግር መልኩ ሌላ ቃል አስገባህበት፡፡ ሰለፊ መስለህ ሰለፍያን ከምትዋጋ ድፍረቱ ካለህ ለምን እራስህን አትሆንም?
5. ((ደግሞ ከሁሉም ከሚያሳዝነው በዚህ ጥመት ላይ የወደቁ ወንድሞቻችን ከአላህ ጠላቶች ጋር ያላቸው ቀረቤታ …)
መልስ፡- ቀረቤታ ያላቸው እነማን እንደሆኑ በተጨባጭ እናውቃለን፡፡ ትላንት ለኢህአዴግ ንብ ያለበት ቲሸርት ለብሰው ሲቀሰቅሱ የነበሩት፣ በየአዳራሹ ለመንግስት ሲሰብኩ የነበሩት፣ እነማን እንደነበሩ ይታወቃል፡፡ መሻኢኾች ሳይቀሩ የኢህአዴግ የድርጅት አባል የሆኑ አውቃለሁ፡፡ እነሱ የመንግስት ተባባሪ ያልሆኑትን ማን ሊሆን ነው? ለዲን ሊሰሩ ነው በለን፡፡
6. ((በእምነት አንድ የሆነው እና በአስተሳሰብ ከሱ ጋር የተለየውን ግን በጠላትነት ፈርጆ 24 ሰአት በሙብተዲነት፣ በሙሽሪክነት እና በፋሲቅነት ሲፈርጅ መመልከታችን ነው፡፡))
መልስ፡- ሙብተዲዕ ከሆነ ምን እንዲባል ትፈልጋለህ?! ሰሐባ ለሚሳደብ፣ ኡማውን በጅምላ ለሚያከፍር፣ በጥቅሉ ለኢኽዋን አንጃ የሚሟገቱትን ምን እንበላቸው? ያንተ ኡስታዞች ከሙዐውያ ይልቅ ለሰይድ ቁጥብ የሚሟገቱ ከሆነ ሙብተዲዖች እንደሆኑ ከመናገር ወደ ኋላ አንልም፡፡ በአስተሳሰብ ስለተለያየን ብቻ ለደህንነት አሳልፈው ሲሰጡ የነበሩት የናንተ ኡስታዞች ናቸው፡፡ ፊትና ላለመፍጠር እንጂ ከነስማቸው የትና መቼ እንዳደረጉት እቆጥርልህ ነበር፡፡
7. ((የሃቀ ጎዳና ተከታዬች እኛ ብቻ ነን የሚሉት ወንድሞቻችን ግን ከዚህ ቁርአን አንቀፅ በተፃራሪው በመቆም በአማኞች ላይ ብርቱ ሲሆን በካሃዲዎች ላይ ደግሞ ሲለሳለሱ እየተመለከትናቸው ነው፡፡ ያውም ከሃዲ ሆኖ ሙስሊሞችን ሳይነካ በሰላም የተቀመጠውን ሳይሆን አቂዳህን ካልቀየርኩብህ በግድ ያለውን አካል ከምላሳቸው ሰላም አግኝቶ እየተንከባከባቸው ይገኛል፡፡))
መልስ፡- ምን ያህል ውሸታም እንደሆንክ የመጨረሻው አረፍተነገርህ ይናገራል፡፡ የሚገርመኝ እንዲህ አይነት በውሸት የታጨቀ መርዛማ ንግግርህ እያየ ፖሰቶችህን ላይክ የሚያደርግልህ ሰለፊ ነው!!
8. ((ውድ እህት እና ወንድሞቼም ሃቅ ነው ብላችሁ በዱአቶች እና በአሊሞች ላይ ከድንቁርና በአላህ ፈቃድ ያወጡዋቹን አሊሞች እንድትሳደቡ፣እንድትጠሉዋቸው እና ታፔላ እየለጠፋቹ እህዋን ነው፣.ሙብተዲእ ነው እንድትሉ ያደረጉዋቹን ወጣቶች በጥሜት ላይ እንደከተቷችሁ ከዚህ በታች የቀረበውን የኡለሞች ምክር አንብባችሁ እራሳችሁን ፈትሹ፡፡ ቀብር ስትገቡ የፌስቡክ ወዳጅ፣ዋትስአፕ እና እስካይፒው ሰባኪያችሁ አያስጥላችሁም፡፡))
መልስ፡- አንዱ የማህበራዊ ድረ-ገፅ ሰባኪ እኮ አንተ ነህ!! “መድኸሊ፣ ተክፊር፣ ካድሬ፣ የሁዳ፣ ..” እያሉ ዱዐቶችን የሚወነጅሉትንስ እንዳንተ አይነቱ የፌስቡክ ሰባኪ ከቀብር ቅጣት ሊያተርፋቸው ነው? ለምን ይህንንም አታካትትም፡፡ እራስህን ፈትሽ፡፡ ከኢኽዋን መከላከል ከቀብር ቅጣት አያተርፍም፡፡ የዘረዘርካቸው ዐሊሞችን ኢኽዋንን በጥብቅ ያወግዛሉ፡፡ እውነት ምክራቸውን የምትቀበል ከሆንክ ከቻልክ ስለኢኽዋን የፃፉትንም ልክ አሁን እንዳረግከው ተርጉም፡፡ ካልሆነልህ ትርጉም እየገለበጥክ ሳታውቅ አዋቂ ለመመስል አትሞክር፡፡