Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

‹ሂጃብ ሲቃጠል የት ነበራችሁ?፤ ሴት እህቶቻችን መከራ ሲደርስባቸው የት ነበራችሁ›› እና ሌሎችም የድምፃችን ይሰማ ደጋፊዎቹ የሚያነሱት ክሶች


‹‹ሂጃብ ሲቃጠል የት ነበራችሁ?፤ ሴት እህቶቻችን መከራ ሲደርስባቸው የት ነበራችሁ›› እና ሌሎችም
የድምፃችን ይሰማ ደጋፊዎቹ የሚያነሱት ክሶች፡፡

‹‹መቶኝ አለቀሰ፤
ቀድሞኝም ከሰሰ›› ይላል ገጣሚው

የነዚህ ሰዎች ሁኔታ ይህ ነው፡፡ አብዛኛው ሰልፍ ብለው የጠሩት ላይ የሚደርሰውን ድብደባ እና መከራ ቀድሞ እንደሚደርስ አደለም እነሱ ተራው ማህበረሰብ እንኳን ኢንፎርሜሽን እየደረሰው ውጣ ይሉታል፡፡ ከዛም የፌስቡክ አክቲቪስቶች ሙስሊሙን ‹‹መቅረፅ እንዳንረሳ›› ይሉታል፡፡ ከድብደባው በኋላ ያለውን መከራ በሰላም ከተቀመጡባት ዜና ማጣፈጫ አድርገው ያቀርቧታል፡፡ ሙስሊሙ ከግዜ ወደ ግዜ ሞራሉ ላይ ማንም እንዲረማመድበት እያደረጉ ያሉት ሰዎች ወይ ዲን ወይ ፖለቲካ ያልገባቸው መሆናቸውን ስራቸው እየመሰከረ ነው፡፡

አስገራሚው ለጠሩት ያውም ችግር እንዳለበት የሚያውቁትን ሰልፍ፤ ሙስሊሙ መከራ ደርሶበት ሲያበቃ የመጣውን መከራ ግን የሚያላክኩት የፈረደበት ‹‹ቅድሚያ ለተውሂድ›› እያሉ የሚያሾፉበት እና ቃሉን ሚድያ ላይ እንደጦር የሚፈሩት የነብያት ጥሪ እና እሱን ተከተታዬች ላይ ነው፡፡ እንዲህም ብለው ሲፅፉ ታይተዋል ‹‹ቅድሚያ ለተውሂድ ይላሉ፤ ሂጃብ ሲቃጠል የት ነበሩ?››፡፡ ሱብሃነላህ ታድያ የዚህ ተጠያቂ ውጪ ሆኖ የሚያቀጣጥለው ነው ወይንስ ....????

እነሱ የሚጠሩት ሰልፍ ችግር እንዳለው በተለይ ለሴቶች ተብሎ መልክት ሲሰጣቸው ‹‹የመንግስት ቅጥረኛ፤ ሙናፊቅ፤ የአላህ ጠላቶች፤ የኢስላም ጠላቶች›› እና የመሳሰለውን ስም ይለጥፋሉ፡፡ እነሱ በተገላቢጦሹ አንዱ ሰልፍ ላይ ከባድ ኪሳራ አስከትለው እንዳይወቀሱ ‹‹የእፎይታ ግዜ››፤ ሲፈልጉ ‹‹ሙስሊሙን የጥቁር ሽብር ሰለባ ላለማድረግ እና የመሳሰለውን ይላሉ፡፡ እስቲ በአላህ ስም የምጠይቀው የትኛው የኢትዬጵያ ሙስሊም ላይ የደረሰ ችግር ነው ችግሩ እንደሚደርስ ሳይታወቅ የደረሰው፡፡ ‹‹እያወቁ አለቁ›› እንደሚባለው፤ ሙስሊሙን መጠቀሚያ ማድረግ ነው የተያዘው፡፡

ኢንሻ አላህ ነገ አላህ ፊት ሁላችንም እጃችን ላለበት ሁሉ እንጠየቅበታለን፡፡

እሱ ኦንላይን ሆኖ የት ነበርክ ይልሃል፡፡ ሌላው አሜሪካ እና ዩሮጵ ሆኖ ይዘግብልሃል፡፡ ታድያ እውነት ለዲን ከሆነ ምን አስቀመጠህ ውጭ አገር እሞትለታለሁ እያልክ ፌስቡክ ላይ የምትደሰኩርለትን ብቅ ብሎ ማየት ነዋ፡፡ ውጪ ተቀምጦ በሰላም እንዲህ ሲል ይሰብካል

‹‹በሆነ ባልሆነው ሁሉ ነገር ይበላናል የሚመስላቸው የሚፈሩ አሉ፤ የሚቦኩ አሉ ምንም እንትን የሚለው የለም ሞት እንደሆነ አላህ ባዘዘበት ቀን ነው የሚመጣው›› ይሉናል፡፡

ተናጋሪው ግን በሰላም ውጭ ተቀምጧል፡፡ እዚህ ያለውን አትፍራ እያለ ይሰብካል፡፡ የጀነት ጉዞ ከሆነ ለምን ብቅ አይልም ወይንስ እሱ ጀነቷን አይፈልጋትም?

አላህ ‹‹እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ለምንድን ነው የማትሰሩትን የምትናገሩት›› ይላል፡፡ አላህ ከእንዲህ አይነት የማይሰሩትን የሚናገሩ ጠብቀን፡፡

ወንጀል የዚህ ሁሉ ሰበብ ሊሆን እንደሚችል እና ወደ አላህ በተውበት መመለስ ግድ እንደሚለን በሚከተሉት የአላህ ቃሎች ተናግሬ እጨርሳለሁ፡፡

إِنَّ ٱللَّهَ لَا يُغَيِّرُ مَا بِقَوْمٍ حَتَّىٰ يُغَيِّرُوا۟ مَا بِأَنفُسِهِمْ ۗ

አላህ በሕዝቦች ዘንድ ያለውን ፀጋ አይለውጥም፤ (እነርሱ) በነፍሶቻቸው ያለውን ጥሩ ነገር (መጥፎ በመስራት) እስካለወጡት ድረስ፡፡

ظَهَرَ ٱلْفَسَادُ فِى ٱلْبَرِّ وَٱلْبَحْرِ بِمَا كَسَبَتْ أَيْدِى ٱلنَّاسِ لِيُذِيقَهُم بَعْضَ ٱلَّذِى عَمِلُوا۟ لَعَلَّهُمْ يَرْجِعُونَ የሰዎች እጆች በሠሩት ኃጢኣት ምክንያት የዚያን የሠሩትን ከፊሉን ያቀምሳቸው ዘንድ መከራው በየብስና በባሕር ተገለጠ፤ (ተሰራጨ)፡፡ እነርሱ ሊመለሱ ይከጀላልና፡፡

አላህ ሆይ! ሃቅን በሃቅነቱ አሳየን የምንቀበለውም አድርገን፤ ባጢልን በባጢልነቱ አሳየን የምንርቀውም አድርገን፡፡
የአላህ ሰላት እና ሰላም በነብያት ሁሉ መደምደሚያ፤ በቤተሰቦቻቸው፤ በባልደረቦቻቸው፤ ሃቅን በተከተለ ላይ ሁሉ ይሁን፡፡