Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ቅጥረኞቹ

<<ቅጥረኞቹ>>
የአላህ መላክተኛ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) እንዲህ ይላሉ ‹‹ዘመን ይመጣል እውነተኛው ውሸታም፤ ውሸታሙ እውነተኛ የሚባልበት….››፡፡

‹‹የማይመስል ነገር ለሚስትህ አትንገር›› ይላል ተራቹ

የትኛው መንግስት ይሆን የሚከተለውን የሚሉትን (የውስጥ አዋቂው አላህ ብቻ ነው) ሰዎች ቅጥረኛ አድርጎ የሚይዘው

1) አላህን ብቻ እናምልክ በእርሱም ላይ ማንንም ይሁን ምንንም አናጋራ፤
2) ያአላህ ብቻ እንበል ከአላህ ውጭ ያለን እንራቅ፤
3) እርድን ለአላህ ብቻ እንጂ ለአልከሶ አናድርግ፤
4) ሱጁድን ለአላህ ብቻ እንጂ ለቃጥባሪ ቀብር አይደረግ፤
5) ጠዋፍን ካዕባ ላይ ብቻ እና ለአላህ ብቻ ይደረግ ለኑርሁሴን ቀብር አይደረግ፤
6) ጌታችን አላህ ከፍጡራኑ ሁሉ በላይ ከአርሽ በላይ ነው፤
7) የነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ሱናን አጥብቀን እንያዝ፤ ከቢድዓ ሁሉ በአይነታው እንራቅ፤
8) የሽርክ መናሃሪያ የሆነውን ‹‹መውሊድ›› እንራቀው የእሳት መንገድ ነውና፤
9) ሰሃባዎች ክብራቸው ይከበር አይሰደቡ፤
10) ወለድን እንራቅ፤
11) ሴቶች አላህ እና መልክተኛው የረገሙትን ‹‹ቅንድብ መቀንደብ እና ማስቀንደብ፤ ዊግ መቀጠል እና ማስቀጠል፤ ንቅሳት መንቀስ እና ማስነቀስ›› ትተው ‹‹አላህ የሰውን ልጅ ባማረ ሁኔታ ፈጠርነው›› ብሏል የአላህን ያማረ አፈጣጠር አታበላሹ፤
12) ወንድ እና ሴት ለኢስላም ነው እየተባለ አይደባለቁ፤ ኢስላም አላህን በማመፅ አይረዳም፤
13) ወንዶች ጀመዐ ሰላት ግዴታ ተደርጎብናል፤ ኳስ እያልን የአላህን ቤት ጭር አናድርግ፤
14) በዲን እና ዲንን በተሸከሙ ሰዎች ላይ ማላገጥ ይቅር፤
15) መስጂዶችን የድራማ ሰሪ እየተባለ የአጅነቢ ወንድ እና ሴቶች ፎቶ አይለጠፍባቸው፤
16) ድራማ እና ፊልም የሚባል ነገር በኢስላም የለም፤
17) ጫት የሚባል ነገር የኢስላም አካል አይደለም፤ ሙስሊሞችን የሚያሽመደምድ፤ የሚያደነዝዝ እንጂ፤
እና የመሳሰሉትን የሚሉ መንግስት ቅጥረኛ አድርጎ ይይዛል ተብሎ ሲነገርህ እንዴት ታምናለህ???

ምክንያቱም የአላህ መላክተኛ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) በመልክተኝነት ከመላካቸው በፊት ‹‹ሙሃመዱል አሚን (ታማኙ ሙሃመድ)›› ነበር ስማቸው፡፡ አንድ አላህን ብቻ ተገዙ፤ ከእርሱ ውጭ ያሉትን ሁሉ (ስም ጠቅሰው ላትን፤ ኡዛን፤ ኢሳን፤ መላኢካን፤ ጂንን) ራቁ፤ እኔም የአላህ መላክተኛ ነኝ ሲሉ የሚከተሉትን ተባሉ ስማቸውን ለማጥፋት
‹‹እብድ፤ ገጣሚ፤ ድግምተኛ……. በታታኝ››

ታድያ ነብያት የተላኩበትን መንገድ እነሱ ባሳዩት መንገድ የሄደ፤ ማንኛውንም አይነት መንገድ ተጠቅመው ሰዎች ስሙን ቢያጠፉት እንዳይገርመው እና እንዳይሰማው ይሄ መንገዳቸው ነውና፡፡ ዋናው መገንዘብ ያለበት ነብያት በሄዱበት መንገድ መጓዙን ብቻ እና ብቻ ነው፡፡

እንደየዘመኑ ማስበርገጊያው ይለያያል፡፡
አላህ ብቻ ይመለክ ያለን ‹‹አማልክቶቻችንን የሚሳደብ፤ ነብያችንን የማይወድ፤ ወልዬችን የማይወድ››፤ ወደ እውነተኛው አንድነት የሚጣራውን ‹‹በታታኝ››፤ እና የመሳሰለውን ይሉታል ታድያ የአላህ መላክተኛ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) እንዲህ ይላሉ ‹‹ዘመን ይመጣል እውነተኛው ውሸታም፤ ውሸታሙ እውነተኛ የሚባልበት….››፡፡

ሰው መቼም ፍርድ የሚሰጠው ከላይ በሚያየው ነው፤ የውስጥ አዋቂው አላህ ብቻ ነው፡፡ ሰዎች ከሚያወሩት ድፍረት ውስጥ ወደ ተውሂድ እና ሱና የሚጣሩ ሰዎችን ‹‹ሙናፊቆች›› ብለው መጥራታቸው ነው፡፡ የአላህ መላክተኛ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) እንኳን ሙናፊቆችን አላህ ያሳወቃቸውን ብቻ ነበር የሚያውቁት፡፡ ዛሬ ውስጥ አዋቂ ይመስል ቢድዐውን ስታጋልጥበት ‹‹ሙናፊቅ›› ብሎ ታፔላውን ይለጥፍብሃል፡፡ ነገ አላሁ (ሱብሃነሁ ወተዓላ) ፍርድ በሚጠይቅበት ቀን ምን ይሆን የሁላችንም መልስ?

የአላህ ባርያዎች ሆይ! ሚዛን ይኑረን፡፡ እኛ ፍርድ የምንሰጠው ከላይ በምናየው ነው፤ አላህ ውስጥ አዋቂ ነው፡፡ ከላይ የተዘረዘሩትን ሁሉ በአቅማቸው ልክ የሚሰሩ ወንድም እና እህቶችን ‹‹ቅጥረኛ እና ሙናፊቅ›› ይላሉ፡፡ አላህ ከቅጥረኝነት እና ኒፋቅ ይጠብቀን ሁላችንንም፡፡ እውነት እንዲህ አይነት ቅጥረኛ አለ? የሙናፊቅነትን ጉዳይ አላህ ብቻ አይደለምን የሚያውቀው?

አላህ እንዲህ ይላል
فَمَن يَعْمَلْ مِثْقَالَ ذَرَّةٍ خَيْرًا يَرَهُۥ
የብናኝ ክብደት ያክልም መልካምን የሠራ ሰው ያገኘዋል፡፡
وَمَن يَعْمَلْ مِثْقَالَ ذَرَّةٍ شَرًّا يَرَهُۥ
የብናኝ ክብደት ያክልም ክፉን የሠራ ሰው ያገኘዋል፡፡
አላህ ሃቁን ይምራን፡፡ አላህ ሆይ! ሃቅን በሃቅነቱ አሳየን የምንቀበለውም አድርገን፤ ባጢልን በባጢልነቱ አሳየን የምንርቀውም አድርገን፡፡ የአላህ ሰላት እና ሰላም በነብያት ሁሉ መደምደሚያ፤ በቤተሰቦቻቸው፤ በባልደረቦቻቸው፤ ሃቅን በተከተለ ላይ ሁሉ ይሁን፡፡