Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ኢንጂነሩ እና ፎቁ



አንድ ኢንጂነር 10 ፎቅ ያለው ከሰራሁ በኋላ መሰረቱን እሰራዋለሁ ቢል አምኖ ገንዘቡን የሚሰጠው የለም፡፡ ምክንያቱም ያለ መሰረቱ ፎቁ ሊቆም አይችልምና፡፡ ልክ እንደዚሁ ሁሉ ወደ አላህ መንገድ የሚጣራው ተጣሪ መሰረቱን (ተውሂድን እና አቂዳን) ቀድሞ ሳይጣራ እና ሰዎች ላይ ሳያስተካክል ወደ ሌላ አርስቶች የለፋውን ቢለፋ ከንቱ ልፋት ሆኖ ብቻ ነው የሚቀረው፡፡ ያለ መሰረት የሚሰራው ፎቅ ፈራሽ እንደሚሆነው ሁሉ ያለ ተውሂድ እና ሱና መሰረት የተሰራው ስራ ሁሉ ወዳቂ፤ ትቢያ ብቻ ነው ውጤቱ፡፡ ወደ አላህ መንገድ የሚጣሩ ሰዎች ሁሉ ይህን ልብ ሊሉ ይገባቸዋል፡፡
አላህ መሰረታቸው ተስተካክሎ፤ ለሰዎች መሰረት መስተካከል የሂዳያ ሰበብ ከሚሆኑት ያድርገን፡፡