Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ኢብኑ ዑሠይሚንና ባለታክሲው

 Ibnu Munewor

በአንድ ወቅት ሸይኽ ኢብኑ ዑሠይሚን ረሒመሁላህ መካ ሐረም ውስጥ ይሰግዱና ወደ ሚና ለመሄድ ኮንትራት ታክሲ ይይዛሉ፡፡ ጉዞ ላይ እንዳሉ ባለ ታክሲው ሊተዋወቃቸው ፈለገና.. “ማን ልበል” አላቸው፡፡
“ሙሐመድ ኢብኑ ዑሢሚን” አሉት፡፡
“እውን አንተ ሸይኽ ኢብኑ ዑሠይሚን ነህ?” አላቸው፡፡ እያሾፉ መስሎታል፡፡
“አዎ” አሉት፡፡
ሰውየው በአግራሞት እራሱን ነቀነቀ፡፡
“ምን አይነት ደፋር ሸይኽ ነው እራሱን በሸይኽ ኢብኑ ዑሠይሚን የሚያመሳስለው” እያለ ነው፡፡
“አንተስ ማነህ ወንድሜ?” አሉት፡፡
“እኔ ፈዲለቱሸይኽ ዐብዱልዐዚዝ ኢብኑ ባዝ ነኝ!” አላቸው፡፡ እያሾፉ ስለመሰለው እሱም
ማሾፉ ነው፡፡
“ኢብኑ ባዝ ግን አይነ-ስውር ነው መኪና መንዳት አይችልም” አሉት፡፡

የእውነት ሸይኽ ኢብኑ ዑሠይሚን
መሆናቸውን ሲያውቅ በጣም ተጨናነቀ፡፡
ይቅርታ ጠየቀ፡፡
(ኢብቲሳማቱል መሻይኽ)
_______________
2) “ነቢን”

በአንድ ወቅት የሸኽ ዑሰይሚንን ትምሕርት ለመከታተል ከተቀመጡት አንዱ ግብፃዊ “ነቢን” ብሎ ይምላል ። ሸኹም ጠንከር አድርገው የተናገረው ትክክል አለመሆኑን ገሰፁት ፤ ማስረጃ አጣቅሰውም መከሩት ። ሰውየው ምክሩን መቀበል ሊነግራቸው ፈልጎ ኖሮ “ነቢን! ድጋሚ አልምልም!” አላቸው ። በዙሪያው የነበረው ሰው ሳቀ ። ሸኽ ዑሰይሚንም “ በል ይቺ የመጨረሻክ ትሁን!” አሉት ።