Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ተውሂድን ያረጋገጠ ያለ ምንም ምርመራ ጀነት ገባ

ተውሂድን ያረጋገጠ ያለ ምንም ምርመራ ጀነት ገባDawud Yassinقال الله تعالى"إن إبراهيم كان أمة قانتا لله حنيفا ولم يك من المشركين"النحل 120"ኢብራሂም ለአላህ ታዛዥ ወደ ቀጥተኛ ሃይማኖት ተዘንባይ ህዝብ ነበር።ከአጋሪዎቹም አልነበረም።"አል ነህል 120
ይህ ቁርዓናዊ አንቀፅ የኢብራሂም አለይሂ ሰላም ባህሪ ተውሂድን እጅግ በጣም ያረጋጋጠ መሆኑን ያሳየ ነው። አላህ ሱብሃነ ወተዓላ በአራት ትልልቅ ባህሪዎች አውስቷቸዋል።

1.በተውሂድ አርዓያ፣መሪና ጥሩ ነገር አስተማሪ
2.አላህን በመታዘዝና በመገዛት ላይ ዘውታሪ
3.ወደ አላህ የዞረና ከሱ ውጪ ካለ ነገር የራቀ
4.ከሽርክና ከሽርክ ባለቤቶች የራቀ

፨ ሰዎች ተውሂድን በማረጋገጥ ላይ ሁለት ደረጃዎች አሏቸው

➀ .የተሟላ ተውሂድ ፦ ይኸውም በአላህ ማመን ፣ በእርሱ መመካት፣ ልብን በእርሱ ላይ ማንጠልጠል፣ የሰውነት አካልን በኢስላማዊ ህግጋት ላይ የፀና ማድረግ እንዲሁም ይህን እምነቱ በወንጀልና በቢድዓ ያላጓደለ ነው።

➁.የተውሂድ መሰረትን ያስገኘና የተውሂድ ሙሉነትን ያላረጋገጠ ፦ ይኸውም ከሽርክ ራሱን ያፀዳና ነገር ግን ተውሂድን ሊያጓድሉ የሚችሉ ወንጀሎች ላይ የወደቀ ነው ፤ ነገር ግን እነዚህም ወንጀሎች የተውሂድን መሰረት የማያስወግዱ የሆኑ ናቸው። አላህ ንፁህ ተውሂድን ይወፍቀን