Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ፈጣሪ ቀላቢ፤ ፍጡራን ተቀላቢ፡፡


ፍጥረተ አለሙን የፈጠረ፤ የሚያስተናብር፤ የሚቀልብ አላህ ብቻ ነው፡፡ ይህንን ከአላህ ውጭ ያለ ያደርገዋል ብሎ መናገርም ይሁን ማመን ክህደት ነው፡፡ ሁሉን የፈጠረ ቀላቢ፤ ሁሉም ፍጡራ የብቸኛው ፈጣሪ ተቀላቢ ሆነው ሲያበቁ፤ ጥራቻ ለአላህ የተገባው ይሁን አገራችን ላይ የሚከተሉትን ክህደት እና ባዕድ አምልኮዎች እናገኛለን፡፡

1) አላሁመሰሊ አላ ሙሀመዲ
መገን ነቢ (በጣም ይገርማሉ ነቢ)
የሁሉ ቀላቢ

2) ለካም አንቱ ነሁ ያነቢ
ለመላው ኸልቅ ቀላቢ
ብትን ያለውን ሰብሳቢ
በሶፋ ቡራቅ ጋላቢ

3) አባድር ፆም አያሳድር፡፡

እነዚህ ከላይ ያነበባችኋቸው የክህደት፤ የኩፍር ቃላት ናቸው፡፡ አላህ ስለ እራሱ እንዲህ ሲል ይናገራል፡፡
وَمَا مِن دَآبَّةٍ فِى ٱلْأَرْضِ إِلَّا عَلَى ٱللَّهِ رِزْقُهَا وَيَعْلَمُ مُسْتَقَرَّهَا وَمُسْتَوْدَعَهَا ٰ
በምድርም ላይ ምንም ተንቀሳቃሽ የለችም ምግቧ በአላህ ላይ ያለ ቢኾን እንጂ፡፡ ማረፊያዋንም መርጊያዋንም ያውቃል፡፡
إِنَّ ٱلَّذِينَ تَعْبُدُونَ مِن دُونِ ٱللَّهِ لَا يَمْلِكُونَ لَكُمْ رِزْقًا فَٱبْتَغُوا۟ عِندَ ٱللَّهِ ٱلرِّزْقَ وَٱعْبُدُوهُ وَٱشْكُرُوا۟ لَهُۥٓ ۖ إِلَيْهِ تُرْجَعُونَ
ውሸትንም ትቀጣጥፋላችሁ፡፡ እነዚያ ከአላህ ሌላ የምትግገዙዋቸው (መላኢካዎችም፤ ነብያትም (ኢሳን፤ ኡዘይርን፤ ነብዩ ሙሃመድን ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም)፤ ደጋጎችም አልይም፤ ሁሴንም፤ ፋጢማም፤ ጠንቋይም፤ ጂንም እናም ሌሎችም) ለእናንተ ሲሳይን ሊሰጧችሁ አይችሉም፡፡ ስለዚህ ሲሳይን ከአላህ ዘንድ ብቻ (ፍጡራኑን የሚያብቃቃ ፍጡራኑን የሚያብቃቃ ብቸኛው አምላክ፤ ብቸኛው ፈጣሪ አላህ ከእርሱ ብቻ) ፈልጉ፡፡ ተገዙትም (ለእርሱ ብቻ የሚገቡትን መብቶች ለፍጡን አሳልፋችሁ አትስጡ)፡፡ ለእርሱም አመሰግኑ፡፡ ወደእርሱ ትመለሳላችሁ፡፡

ተውሂድ ማለት አላህ ብቻ የሚነጠልበትን መነጠል ሲሆን፡፡ ሽርክ ደግሞ ለአላህ ብቻ የሚገቡትን ወይንም አላህ ብቻ የሚነጠልባቸውን ከእርሱ ውጭ ላለ ማንም አካል (ፍጡር ማለት ነው፡፡ ብቸኛው ፈጣሪ እሱ ብቻ ሆኖ ሳለ) ይሁን አሳልፎ ለፍጡራን መስጠት ነው፡፡

በአላህ ላይ ማጋራት ከባድ ወንጀል እና በደል ነው፡፡ እያጋራ የሞተ ሰው መኖርያው እሳት ነው፤ ጀነት በእርሱ ላይ እርም ናት፡፡ የአላህ ባርያዎች ሆይ! የሽርክን አስከፊነት ተገንዝበን እራሳችንን፤ ቤተሰባችንን፤ ዘመዶቻችንን፤ መላውን ማህበረሰብ ከእሳት በአላህ ፈቃድ ልናድን ይገባናል፡፡

የአላህ ሰላት እና ሰላም በነብያት ሁሉ መደምደሚያ፤ በቤተሰቦቻቸው፤ በባልደረቦቻቸው፤ ሃቅን በተከተለ ላይ ሁሉ ይሁን፡፡