Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

እራሳችንን እንፈትሽ!

እራሳችንን እንፈትሽ!

📌 ሰውባን እንዳስተላለፉት የአላህ መልዕክተኛ ﷺ እንዲህ ብለዋል፤
«ከኔ ህዝቦች፤ በእለተ ትንሳኤ ንፃታቸው ቲሀማ የተባለውን ተራራ የሚመስሉ መልካም ስራዎች የሚኖሯቸውን ሰዎች አውቃለሁ፤ አላህ ስራቸውን የተበተነ ትቢያ ያደርገዋል።» ሰውባንም፤ የአላህ መልእክተኛ ሆይ! ባለማወቅ ከነሱ እንዳንሆን ማንነታቸውን ግልፅ ያድርጉልን" አሏቸው።
እሳቸውም፤ «እነዚህ ሰዎች ከናንተው የሆኑ ወንድሞቻችሁ ናቸው፤ እናንተ የለሊት ስግደት እንደምትሰግዱ እነሱም ይሰግዳሉ። ነገር ግን እነዚህ ጭፍሮች ከሰዎች ሲገለሉና (ነገሮችሲመቻችላቸው) አላህ እርም ያደረጋቸውን ነገሮች ይዳፈራሉ»
ኢብኑ ማጀህ ዘግበውታል አልባኒም ሰሂህ ብለውታል

عَنْ ثَوْبَانَ رضي الله عنه ، عَنْ النَّبِيِّ صَلَّى اللَّهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ أَنَّهُ قَالَ : [لَأَعْلَمَنَّ أَقْوَامًا مِنْ أُمَّتِي يَأْتُونَ يَوْمَ الْقِيَامَةِ بِحَسَنَاتٍ أَمْثَالِ جِبَالِ تِهَامَةَ بِيضًا فَيَجْعَلُهَا اللَّهُ عَزَّ وَجَلَّ هَبَاءً مَنْثُورًا قَالَ ثَوْبَانُ يَا رَسُولَ اللَّهِ صِفْهُمْ لَنَا جَلِّهِمْ لَنَا أَنْ لَا نَكُونَ مِنْهُمْ وَنَحْنُ لَا نَعْلَمُ قَالَ أَمَا إِنَّهُمْ إِخْوَانُكُمْ وَمِنْ جِلْدَتِكُمْ وَيَأْخُذُونَ مِنْ اللَّيْلِ كَمَا تَأْخُذُونَ وَلَكِنَّهُمْ أَقْوَامٌ إِذَا خَلَوْا بِمَحَارِمِ اللَّهِ انْتَهَكُوهَا] رواه ابن ماجة (4245) وصححه الألباني .