Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ከሙኻሊፎች ጋር መተባበር?


Salah Ahmed

📌ከሙኻሊፎች ጋር መተባበር?📌
 ከሌሎች ጋር የሚኖረን የጋራ መተባበር የሚወሰነው በሸሪአዊ ሚዛን ነው። አላህ ሱብሀነሁ ወተዓላ ምዕመናን በመልካም ተግባር እና አላህን በመፍራት ላይ እንዲተባበሩ አዟል።
አላህ እንዲህ ይላል፤
{وَتَعَاوَنُوا عَلَى الْبِرِّ وَالتَّقْوَى وَلَا تَعَاوَنُوا عَلَى الْإِثْمِ وَالْعُدْوَانِ} سورة المائدة ٢
«በበጎ ስራና ወንጀልን በመጠንቀቅ ላይ ተረዳዱ፤ በኃጢአትና ወሰንን በመጣስ ላይ አትተባበሩ!» 
[አል-ማኢዳህ ፡ 2]
√ ቢድዓ ላይ ካሉ ሰዎች ጋር ኢስላምን በሚጠቅም ተግባር ላይ መተባበር እንደሚያስፈልግም አያጠያይቅም። ምናልባት በዚህ ምክኒያት የሚከሰቱ መጥፎ ዉጤቶች (መፋሲዶች) ካሉ፤ እነርሱን ማስቀረት የሚቻልበትን መንገድ ማጤን እና ትክክለኛውን አቅጣጫ መያዝ ያስፈልጋል።
√ ግልፅ ከሆኑ ዲናዊ መረጃዎች እንደምንረዳው ፍትህንና ልማትን በሚያፋጥኑ ጉዳዮች ላይ ሙስሊም ካልሆኑ ሰዎች ጋር ጭምር መተባበሩ አስፈላጊ ነው። 
አል-ኢማም ኢብኑ’ል-ቀይ-ዪም “ሑደይቢያህ” ስምምነት ላይ ካለፉ ክስተቶች የሚቀሰሙ ቁም-ነገሮችን ሲዘረዝሩ የተናገሩት በወንድም ኢልያስ አህመድ እንዲህ ተተርጉሟል፦ «አጋሪያን፣ የቢድዓህ ባለቤቶች፣ ጋጠ-ወጦች፣ ወሰን አላፊ አማፂያንና በደለኞች ከተከበሩት የአላህ ድንጋጌዎች አንዱን ለሚያልቁበት ጉዳይ እርዳታን በጠየቁ ጊዜ (አዎንታዊ) ምላሽ ይለገሳሉ፤ የጠየቁትም ይሰጣቸዋል፤ በዚያም ላይ እገዛ ይደረግላቸዋል፤ ምንም እንኳ ሌላን ነገር ቢከለከሉም! እናም ክህደታቸው ወይም ድንበር ማለፋቸው ላይ ሳይሆን የአላህ ድንጋጌዎችን የሚያልቁባቸው ጉዳዮች ላይ ይታገዛሉ፤ ከዚያ ወዲያ ያለውን ደግሞ ይነፈጋሉ! አላህ ዘንድ ተወዳጅ የሆነና እርሱን የሚያስደስት ነገር ላይ እገዛን የፈለገ ማንኛውም ሰው ማንም ይሁን ማን በዚህ ተወዳጅ ተግባር ላይ በሚደረግለት ትብብር የተነሳ ከዚያ የበለጠ የተጠላ ውጤት እስካልተከተለ ድረስ አዎንታዊ ምላሽ ይሰጠዋልና! ይህም እጅግ ረቂቅና ለነፍስም ከሁሉ በላይ ከባድና (ለመቀበል) አስቸጋሪ ከሚሆኑት ሁኔታዎች ይመደባል..!»
[“ዛዱ’ል-መዓድ” (3/303)]
ይህንን ቁርአናዊ አካሄድ "መንሀጅ" በሀሳብ ደረጃ ብዙዎች ቢቀበሉትም በተግባር የሚሰሩበት ግን ጥቂቶች ናቸው። 
አላህ ሆይ! ውዴታን ካንተ ብቻ ከሚከጅሉ ባሮችህ አድርገን! ከመሳሳት እና ከማሳሳትም ባንተ እጠበቃለሁ! 
قال الإمام ابن القيم
وَمِنْهَا: أَنَّ الْمُشْرِكِينَ وَأَهْلَ الْبِدَعِ وَالْفُجُورِ وَالْبُغَاةَ وَالظَّلَمَةَ إِذَا طَلَبُوا أَمْرًا يُعَظِّمُونَ فِيهِ حُرْمَةً مِنْ حُرُمَاتِ اللَّهِ تَعَالَى، أُجِيبُوا إِلَيْهِ وَأُعْطُوهُ وَأُعِينُوا عَلَيْهِ، وَإِنْ مُنِعُوا غَيْرَهُ؛ فَيُعَاوَنُونَ عَلَى مَا فِيهِ تَعْظِيمُ حُرُمَاتِ اللَّهِ تَعَالَى، لَا عَلَى كُفْرِهِمْ وَبَغْيِهِمْ، وَيُمْنَعُونَ مِمَّا سِوَى ذَلِكَ؛ فَكُلُّ مَنِ الْتَمَسَ الْمُعَاوَنَةَ, مَحْبُوبٍ لِلَّهِ تَعَالَى مُرْضٍ لَهُ، أُجِيبَ إِلَى ذَلِكَ كَائِنًا مَنْ كَانَ، مَا لَمْ يَتَرَتَّبْ عَلَى إِعَانَتِهِ عَلَى ذَلِكَ الْمَحْبُوبِ مَبْغُوضٌ لِلَّهِ أَعْظَمُ مِنْهُ، وَهَذَا مِنْ أَدَقِّ الْمَوَاضِعِ وَأَصْعَبِهَا وَأَشَقِّهَا عَلَى النُّفُوسِ [(زاد المعاد" (3/303"]