Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ለረመዳን ፆም ቅድመ መስፈርቶች

ለረመዳን ፆም ቅድመ መስፈርቶች
የሚከተሉትን መስፈርቶች ያሟላ ግለሰብ የረመዳን ፆም ግዴት ይሆንበታል፦
1. ኢስላም መሆን፡- ከሃዲ እስካልሰለመ ድረስ ፆሙ ተቀባይነት አያገኝም፡፡ ምክንያቱም ፆም ከአምልኮ ተግባሮች አንዱ በመሆኑ እስልምናን ከመቀበል በፊት መፆም ትርጉም አይኖረውም፡፡ አንድ ግለሰብ እስልምናን ሲቀበል ግን የቀድሞ ፆምን ቀዷ (እዳ መክፈል) አይጠበቅበትም፡፡
2. አቅመ አዳም (ሄዋን) መድረስ፡- ተጠያቂነት የሚጀምርበትን እድሜ ያልደረሰ ሰው ፆም ግዳጅ አይሆንበትም፡፡ ይህን በተመለከተ ነብዩ ه “ከሶስት ሰዎች ብዕር ተነስቷል (አይጠየቁም) ህፃን እስኪደረስ፣ የተኛ እስኪነቅ፣ የአእምሮው ህመምተኛ እስኪድን፡፡”
ትንሽ ልጅ የመለያ እድሜ (ሰባት አመት) ከደረሰ አቅመ አደም ባይደርስም ፆሙ ትክክለኛ ነው፡፡ ወላጆቹም ፆምን ለማስለመድ ያህል እንዲፆም ሊያደጉት ይገባል::
3. የአእምሮ ጤናማ መሆን፡- በእብደትና መሰል ችግር አእምሮውን ያጣ መፆም ግዳጅ አይሆንበትም፡፡ ይህን በተመለከተ ከላይ በተጠቀሰው ሀዲስ ነቢዩ ه ጤናማ እስኪሆን ብዕር እንደተነሳለት ተናግረዋል፡፡
4. ጤነኛ መሆን፡- ህመምተኛ በህመሙ ሳቢያ መፆም የማይችል ከሆነ ከህመሙ እስኪያገግም ፆም ግዳጅ አይሆንበትም፡፡
አላህ እንዲህ ብሏል፦
"فَمَنْ كَانَ مِنْكُمْ مَرِيضًا أَوْ عَلَى سَفَرٍ فَعِدَّةٌ مِنْ أَيَّامٍ أُخَرَ"
“በሽተኛ ወይም በጉዞ ላይ የኾነም ሰው ከሌሎች ቀኖች ቁጥሮችን (በልኩ) መጾም አለበት”፡፡
ህመምተኛ ከህመሙ ሲያገግም ያሳለፋቸውን የፆም ቀናት ቀዷ ማውጣት (እዳን መክፈል) አለበት፡፡
5. በመንደሩ ኗሪ መሆን፡- መንገደኛ ፆም ግዴታ አይሆንበትም::
አላህ እንዲህ ብሏል፦
فَمَنْ كَانَ مِنْكُمْ مَرِيضًا أَوْ عَلَى سَفَرٍ فَعِدَّةٌ مِنْ أَيَّامٍ أُخَرَ" البقرة: ١٨٥"
“በሽተኛ ወይም በጉዞ ላይ የኾነም ሰው ከሌሎች ቀኖች ቁጥሮችን (በልኩ) መጾም አለበት”፡፡
መንገደኛ ጉዞ ላይ ችሎ ከፆመ ፆሙ ትክክለኛ ነው፡፡ ከጉዞ ሲመለስ ያሳለፋቸውን የፆም ቀናት ቆጥሮ መፆም አለበት፡፡
6. ከወር አበባና ከወሊድ ደም መፅዳት፡- የወር አበባ ጊዜዋ ላይ ወይም የወሊድ ደም ላይ ያለች ሴት ፆም ግዳጅ አይሆንባትም:: እንዲያውም መፆምም አይፈቀድላትም ነቢዩ ه እንዲህ ብለዋል “ሴት የወር አበባ ላይ ስትሆን አትሰግድም አትፆምም፡፡”
ከወር አበባ በምትፀዳበት ወቅት ቀዷእ ማውጣት ይኖርባታል፡፡ አዒሻ “በነቢያችንه በወር አበባ ምክንያት ያሳለፍነውን ቀዷእ እንድንፆም ስንታዘዝ ያልሰገድውን ሰላት ግን ቀዷእ እንድንሰግድ ግን አልታዘዝንም፡፡”

Post a Comment

0 Comments