Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ፆም ከሰው ልጆች አንፃር

ፆም ከሰው ልጆች አንፃር
1. ፆም በእያንዳንዱ ሙስሊም፣ ለአካለ መጠን የደረሰ፣ ጤናማ አዕምሮ ያለው፣ መፆም የሚያስችለው ጤና ያለው እና መንገደኛ ባልሆነ ሰው ላይ ሁሉ ግዴታ ነው፡፡
2. ሙስሊም ያልሆነ ሰው ፆም ግዴታ አይሆንበትም፡፡ እንዲሁም ወደ ኢስላም ቢመጣ ከመስለሙ በፊት ያለፈውን ፆም የመክፈል (ቀዳእ የማውጣት) ግዴታ አይኖርበትም፡፡
3. ለአካለ መጠን ያልደረሰ ህፃን ፆም ግዴታ ባይሆንበትም ነገር ግን እንዲለምደው በማሰብ እንዲፆም ይታዘዛል፡፡
4. የአዕምሮ በሽተኛ ፆምም ይሁን ለፆም ማካካሻ የሚሆን ፆም ግዴታ አይሆንበትም፡፡ በተመሳሳይ ሁኔታ ነገሮችን መለየት የተሳነው ዘገምተኛ ሰው እንዲሁም የጃጀ ሽማግሌ ፆም ግዴታ አይሆንባቸውም፡፡
5. እንደ እርጅናና ለመዳን ተስፋ እንደሌለው በሽታ ባሉ ዘውታሪ ምክንያቶች የተነሳ መፆም የተሳነው ሰው ለእያንዳንዱ ቀን አንድ አንድ ምስኪን ያበላል፡፡
6. መዳኑን ተስፋ በሚያደርግ ጊዜያዊ በሽታ የተያዘ ሰው መፆም ከከበደው ከበሽታው ሲያገግም በመፆም ያካክሳል፡፡
7. በእርግዝናና በማጥባት ላይ ያሉ ሴቶች በዚህ በእርግዝናው ወይም በማጥባቱ ምክንያት ፆም ከከበዳቸው አሊያም በልጆቻቸው ላይ ጉዳት እንዳይከሰት ከሰጉ ፆምን በመፍታት ስጋቱ በተወገደና በገራላቸው ወቅት ይፆማሉ፡፡
8. በወር አበባና በወሊድ ደም ላይ ያሉ ሴቶች የማይፆሙ ሲሆን ያለፋቸውን የፆም ቀናት በሌላ ጊዜ በመፆም ያካክሳሉ፡፡
9. በእሳት ቃጠሎ ወይም በውሃ የመስጠም አደጋ ላይ የወደቁ ሰዎችን ለመታደግ የነፍስ አድን ስራ ላይ በመሰማራቱ ፆም ለመፍታት የተገደደ ሰው ፆሙን በሌላ ጊዜ በመፆም ያካክሳል፡፡
10. መንገደኛ (ሙሳፊር) ሰው ከፈለገ ይፆማል ከፈለገም ፆሙን በመፍታት በሌላ ጊዜ ያካክሳል፡፡ ይህም ማለት በዘውታሪነት ሳይሆን በድንገት እንደዑምራ ላሉ ተግባራት የሚጓዘውንም ይሁን በዘውታሪነት ጉዞ ላይ የሚሆኑትን (የአገር አቋራጭ) የሕዝብ ማመላሻ ሠራተኞችን ይመለከታል፡፡ እነዚህ ሰዎች በመኖሪያ አገራቸው እስካልሆኑ ድረስ ከፈለጉ ፆምን ይፈታሉ ማለት ነው፡፡

Post a Comment

0 Comments