Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ሰሞኑን በሚቀጠፉ ቅጥፈቶች ላይ የወንድም ሳዳት ድንቅ መልስ

ይህ ፖስት በአላህ እና በመጨረሻው ቀን ለሚያምኑ ሰዎች ብቻ ነው፡፡
====================================
ሰሞኑን አንዳንድ ወንድም እና እህቶች ልብ ባይሉትም እነርሱን ነገ አላህ ፊት ከባድ ጥያቄ ሊያስጠይቃቸው የሚችል፤ ማስረጃ እና መልስም ከሌላቸው አላህ ዘንድ ሊያስቀጣቸው የሚችል ተግባር እየሰሩ ነው፡፡ ነገ ከመፀፀት ዛሬ በማስረጃ ማውራት አይሻልም???
የነዚህ ወንድም እና እህቶች አባባሎች የሚከተሉትን ይመስላሉ
1) ‹‹የመንግስት ቅጥረኞች››
2) ‹‹ከበደ ካሳ የሚባል ካፊር፤ የመንግስት ካድሬ የእገሌን ፖስት ሼር አድርጎታል፤ ይሄም የመንግስት ተባባሪ እና የኢስላም ጠላት ለመሆኑ ማስረጃ ነው››
3) ‹‹ኢስላምን ለዱንያ ብለው የሚሸጡ››
4) ‹‹ሙስሊሞችን ለጠላት አሳልፈው የሚሰጡ››
5) ‹‹ኢስላም ሲጠቃ ዝም ብለው የሚያዩ››
6) ‹‹መንግስት ካሰለጠናቸው 400 ሰዎች ውስጥ ናቸው››
7) ‹‹የይሁዳ ተላላኪ›› እና የመሳሰሉትን
ለነዚህ ወንድሞች ጥቂት
ጥያቄዎች
1) እንዲህ እያላችሁ የምትወነጅሉዋቸው ወንድም እና እህቶች እናንተ ያላችሁትን ሆነው ባይገኙስ ????? ነገ አላህ ፊት መልሳችሁ ምን ይሆናል ?????
‹‹መንግስት ካሰለጠናቸው 400 ሰዎች ውስጥ ናቸው››
ፌስቡክ ውስጥ ስለዘገባው ሲነገር ‹‹ዝግ ስልጠና›› ተብሎ ነበር፡፡ ታድያ ዝግ ስልጠና ከሆነ እንዴት እነዚህ ወንድምና እህቶች ከ400 ሰልጣኞች መሆናቸውን አወቃችሁ? እንዲህ ብሎ በፌስቡክ መፃፍ አደጋው ምን ሊሆን እንደሚችል በሚቀጥለው ምሳሌ እንየው፡፡
ዝሙት፤ ‹‹እገሌ ዝሙት ሰርቷል፤ እገሌ ዝሙት ሰርታለች›› ብሎ መናገር በኢስላም ምን ያስፈርዳል ?????
1.1) ወንድ እና ሴት አንድ ክፍል ውስጥ ስለ ገቡ ዝሙት ሰርተዋል ብሎ መደምደም ይቻላልን እንደ ኢስላም አስተምሮት ?????
1.2) ወንድ እና ሴት ብርድ ልብስ ውስጥ ቢገኙ ዝሙት ሰርተዋል ብሎ መመስከር ይቻላልን እንደ ኢስላም አስተምሮት ????? ወንድ እና ሴት መርፌ እና ክር ሆነው እንዳዩ 4 ሰዎች ምስክሮች ካልተሟሉ፤ አንድ ሰው ቢጎድል እራሱ ሶስቱም 100፤ 100 ጅራፍ ይገረፋሉ፡፡ ታድያ የንፁሃንን ስም ያውም ወደ ተውሂድ እና ሱና የሚጣሩ፤ ሽርክ እና ቢድዐን ከነባለቤቶቹ የሚያወግዙ ሙስሊሞችን ‹‹ከኢስላም ጠላቶች ጋር ዝግ ስልጠና፤ ኢስላምን ለማጥቃት ላይ አብረው ሲዶልቱ ነበር›› ማለት ምን ያህል ይሆን አላህ ፊት የሚያስከፍለው ?????
ከዚህ ሁሉ አስገራሚ ደግሞ አላህ ወሬን አረጋግጡ እያለ ማስረጃ የሌለውን ውሸት እገሌ ዘግቦታል ብሎ፤ ከዛም ጨምሮ ጨማምሮ ሙስሊም ወንድም እና እህቶችን ‹‹የጠላት ቅጥረኞች›› ብሎ መጥራቱ ምን ይሉታል ?????
ዛሬ ይሄ ሁሉ ሙስሊም ወንድም እና እህቶች ላይ የተዋሸው ማስረጃ የሌለው ቅዠት እና ምናባዊ የፈጠራ ወሬ ነገ አላህ ፊት ምን ያመጣብን ይሆን ብለው አላሰቡትምን ????? አላህ ፍርዱ ያማረ ነው፡፡ ሁላችንም አላህን እንፍራ፡፡
‹‹ከበደ ካሳ የሚባል ካፊር፤ የመንግስት ካድሬ የእገሌን ፖስት ሼር አድርጎታል፤ ይሄም የመንግስት ተባባሪ እና የኢስላም ጠላት ለመሆኑ ማስረጃ ነው›› ማለት በጣም አሳዛኝ ነው፡፡ እነኚህ ስሜታቸውን የሚከተሉ ሰዎች የሚናገሩትን ቅጥፈት በራሳቸው አንደበት እስቲ ጥያቄዎችን ይመልሱልን፡፡
ጥያቄውም
አንድ ሙስሊም ‹‹አፈንድቶ ማፈንዳት›› በኢስላም እንደሌለ ቢፅፍ እና አንድ ክርስትያን ሼር ቢያደርገው፤ ያ ሙስሊም ‹‹ከካፊር ጋር እየሰራ ነው››፤ ‹‹የየሁዳ ቅጥረኛ ነው››፤ ‹‹ኢስላምን ከጠላቶች ጋር እየወጋ ነው›› ይባላልን ????? የስሜት ተከታዬች ሁሌ ሚዛናቸው ስሜት ነው፡፡
ካፊሮች ለስሜታቸው የሚመቻቸውን፤ ጥሩውንም ከኢስላም አስተምሮት ሼር ሊያደርጉ ይችላሉ፡፡ ይህ ማለት ግን ፅሁፉ በካፊር ሼር የተደረገለት ሰው ከካፊር ጋር እየሰራ ነው ማለት አይደለም፡፡ ይህን የሚሉ ሰዎች የሚፅፉትን ፅሁፍ ደግሞ ሌላ ካፊሮች፤ ፈላስፋዎች፤ ኢስላምን በግልፅ የሚተቹ ፖለቲከኞች ሰዎችም ሼር ያደርጉላቸዋል (ሼር አድራጊዎቹ እዚህም ጋር ካፊሮች ናቸው) ታድያ ወዴት ወዴት፤ እነሱስ ከማን ጋር እየሰሩ ነው ተብለው ቢጠየቁ ከማን ጋር ሊሉ ነው ?????
የስሜት ተከታዬች እነሱ ሰውን ከሚወቅሱበት ነገር ጠርተው አይገኙም፡፡ ሚዛን ሸሪዐ ነው እንጂ ስሜት አይደለም፡፡
2) ‹‹ሙስሊምን ለጠላት አሳልፈው የሚሰጡ›› የሚለው ቃል ክብደቱን ተረድተውታልን ?????
የነሱን ሃሳብ ያልተቀበለ ሰው ሁሉ ከኢስላም ጠላቶች ጋር አብሯል ማለት ይህስ ከባድ አባባል አይደለምን ?????
3) ‹‹ኢስላም ሲጠቃ ዝም ብለው የሚያዩ›› የሚለውም አባባል ሌላው ቅጥፈት ነው፡፡ አህባሽ ‹‹ኩፍርን፤ ሽርክን፤ ቢድዐን ይዞ ስለመጣ መጀመሪያ ህዝባችንን በእውቀት ማንቃት ነው ያለብን፡፡ ‹‹ተውሂድን፤ ሱናን፤ የሰለፎችን አረዳድ›› ማህበረሰቡ ዘንድ ማስረፅ ነው ያለብን ሲባሉ እና በተግባር የተውሂድ፤ የሱና ትምህርት ሲሰጥ፤ ሽርክ እና ቢድዐ አስከፊነቱ ሲሰጥ በግልፅ እንዲህ ሲሉ ተሰሙ ‹‹አትበታትኑን፤ አንድ ነን››፡፡
የፊስቡክ ተጠቃሚ እና ማህበረሰባችን ‹‹ቅድሚያ ለተውሂድ›› ማለት ሲጀምር ተውሂድን እናስተምር አሉ:: ግን አስገራሚ የማስተማር ስልት ብለው የሚከተለውን ፊስቡክ ላይ አስነበቡን ‹‹(ጎን ለጎንም ሶፊይ አስተሳሰብ ያላቸውን ወንድሞቻችንን እናዳይከፉ ጥንቃቄ በተሞላበት ሁኔታ ብናደርገው)›› የተውሂድ ዳእዋ ማለት እገሌ እንዳይከፋ የሚባል ነገር አለውን ?????
ሱፍዬች ‹‹የሽርክ እና ቢድዐ›› ችግር እንዳለባቸው ከታወቀ እነሱን ‹‹ስለ ተውሂድ እና ሱና›› ተጠንቅቀው እንዲያውቁ እና ‹‹ከእሳት ተጠብቀው፤ ጀነት እንዲገቡ›› መጣር እንጂ፤ ‹‹አንድ ነን›› ብሎ፤ እነሱን እንዳናስከፋቸው ብሎ ‹‹ወደ ተንቀልቃዩዋ›› ጀሃነም ሲሄዱ እያዩ ዝም ማለቱ ነው ሂክማው?????
‹‹ለኢስላም እና ሙስሊሞች›› ማሰብ ማለት ይህ ነው ?????
ሊዘነጋ የማይገባው ትላንት ‹‹አንድ ነን›› እየተባሉ ጥመታቸው ሲሸፈንላቸው የነበሩ ሱፍዩች ናቸው ዛሬ አህባሽ ሆነው ከባድ ጥፋት እያጠፉ ያሉት፡፡ ሸህ ጠሃን ይመስል፡፡
ትላንት ‹‹ሙሁሮቻችን፤ አዋቂዎቻችን ናቸው›› ሲባሉ የነበሩት ሰሃባ የሚዘረጥጡት፤ የሚተቹት፤ እና የቢድዐ ሰዎችን መፀሃፍ ለኢትዬጵያ ሙስሊም ሲተረጉሙ የነበሩት እነ ‹‹ሃሰን ታጁ፤ አብይ ጣሰው፤ ኡስታዞቹ›› እና ግሩፖቹ ናቸው አሁን ኡማውን እየፈተኑት ያሉት፡፡
ትላንት ‹‹ስለ ሺዐ›› እምነት እና የሺዐ ማስታወቂያ ሲለጥፍ የነበረው ‹‹አንድ ነን››፤ ‹‹ዝክረ ኢዘዲን›› ሲሉለት የነበረው ‹‹ቁድስ ጋዜጣ›› ነው ዛሬ ይሄው ኡማውን እያመሰ ያለው፡፡
ታድያ የአንድነት መስፈርቱ ምንድን ነው ????? እውነተኛ የሙስሊሞች አንድነትስ በምን ይመጣል?????
እንዲህ አይነት የቢድዐ አራማጆችን ማስተማሩ ነው የሚበጀው ወይንስ ‹‹አንድ ነን›› ብሎ እነሱን አቅፎ መንቀሳቀስ እና ወደ እሳት ሲሄዱ እያዩ ዝም ማለት ????? ባጢልን አቅፎ መንቀሳቀስ ትርፉ ኪሳራ ነው ልክ ከላይ እንደተጠቀሱት ምሳሌዎች፡፡ የቢድዐ ባለቤቶች መሃል ላይ ይከዱሃል፤ ልክ በተግባር እንደታየው፡፡ በቢድዐ ሰዎች ንግግር መሸወድ አያስፈልግም፡፡ ሚዛኑ ቁርዐን እና ሀዲስ ነው፡፡
የአቅማቸውን ተጠቅመው ተውሂድን፤ ሱናን፤ የሽርክ እና የቢድዐን አስከፊነት የሚያስተምሩ ወንድሞችን፤ የነሱን አካሄድ ስላልተከተሏቸው ብቻ ‹‹የሙስሊሙ ጉዳይ የማያሳስባቸው›› ብለው ይወቅሷቸዋል፡፡ ታድያ ለሙስሊሞች ማሰብ ማለት ሽርክ እና ቢድዐን አቅፎ መሄድ ነውን ?????
በማጠቃለያነት ተጨባጭ ማስረጃ ሳይዙ የተባለን ሁሉ ማራገብ ወንጀሉ የተነባበረ ነው፡፡ ይህ የቅጥፈት ወሬ የደረሰው ሁሉ ይህ ወንጀል ያደረሰው ሰው መዝገብ ላይ ወንጀል ሆኖ ይመዘገባል፡፡ አስገራሚው ደግሞ የተውሂድ እና ሱናን ዳእዋ ለማደናቀፍ የሚደረግ ጥረት መሆኑ፡፡ ወደ ተውሂድ እና ሱና የሚጣሩ ሰዎችን ስም እንዲህ አይነት በሆነ አፀያፊ እና ዘግናኝ ወንጀል በመወንጀል የሚያስተላልፉትን ትምህርት ሰው እንዳይቀበለው ለማድረግ ነው፡፡ እነዚህ ወንድም እና እህቶች አላህን ይፍሩ አላህ አያያዙ የበረታ ነው፡፡ አላህን ሁላችንም እንፍራ፡፡
የአላህ ሰላት እና ሰላም በነብያት መደምደሚያ፤ በቤተሰቦቻቸው፤ በሰሃባዎቻቸው እና ሃቅን በተከተለ ላይ ሁሉ ይሁን፡፡