Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ጎበዝ አላህን እንፍራ እንጂ ያለ ምንም መረጃ ሠውን ካድሬ ፣ የወያኔ ቅጥረኛ ፣ሌባ ፣ ሆዳም ፣ ለሆዱ ያደረ ምናምን እያልን እንሠድባለን እንዴ??


ጎበዝ አላህን እንፍራ እንጂ ያለ ምንም መረጃ ሠውን ካድሬ ፣ የወያኔ ቅጥረኛ ፣ሌባ ፣ ሆዳም ፣ ለሆዱ ያደረ ምናምን እያልን እንሠድባለን እንዴ??

ተው እንጂ ወንድሞች ከመጥፎ ንግግር እኮ ዝምታ በጣም ትልቅ ዋጋ አለው
ነቦዩ ሠለላሁ አለይሒ ወሠለም ያሉትን እናስታውስ እንጂ «በአላህ እና በመጨረሻው ቀን የሚያምን ሠው መልካምን ይናገር ወይም ዝም.ይበል» አይደለም ያሉት

እርግጠኛ ነኝ የስድብ ጥሩ አለ እንደማትሉ.

ይህንን የፃፍኩት ለተሣዳቢው አስቤ አይደለም

ወንድሞቼ እህቶቼ ነገ አላህ ፊት መቆም አለ ዛሬ አፍህ እንዳመጣልህ ተናግረህ ነገ የተናገርካት ሁላ የሠፈረባት መፀሀፍ ስትመጣ ምን ይውጥሀል??

ወንድሜ አንተ ካድሬ ነህ ፣ ለሆድህ ያደርክ… ሌላም ሌላም በል እኔ ግን እኔ ግን አፀፋውን አልመልስልህም ምክንያቱም ሙስሊም ወንድሜ ስለሆንክ የወንድምነት ምክር መለገስ ስላለብኝ ነው

☞ ከአንድ ሠው በቀር እስካሁን ድረስ በዚህ መልኩ ለሠደባችሁኝ አውፍ ብያቹሀለው

☞ ከአሁን ቡሀላ ግን ወላሒ ማንንም አውፍ አልልም አላህ ፊት እጠይቅሀለው!!!