Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

አልከሶ_ለመሄድ_ህዝቤ_እየተሰናዳ_ይገኛል


#አልከሶ_ለመሄድ_ህዝቤ_እየተሰናዳ_ይገኛል
ልጅ ሙሉ ድፍን ዐመቱን ጥሮ ግሮ ለፍቶ የሰራውን ገንዘብ ለአባትና እናት ወደ አልከሶ መሸኛ ይቆጥረዋል ፤ የባሰበትም መኪናውን ሰርቪስ አስደርጎ ካልሆነም ተከራይቶ ለቤተሰቦቹ ጥሩ ነገር የዋለ እየመሰለው ይዟቸው ወደእሳት ይነጉዳል (ወደ አልከሶ) ::
እናት ማክሰኞ ማክሰኞ " ጌቶች ደዋም " ብላ ቡናዋን አፍልታ የቡና ቁርስና 'አተካኖና ሼሽት አዚዝ' (የስልጤ ባሕላዊ ምግቦች) አዘጋጅታ አልከስዬ ለርሶ ይድረሶት እያለች አመቱን ሙሉ ስታመልካቸው እንዳልቆየች ፤ አሁን ቀኑ ደርሶ መውሊዳቸው ሊወጣ ነው ፤ እንደሷና እንደ አብዛኛው የመውሊዱ አክባሪ አስተሳሰብ አልከስዬ አልሞቱም መውሊዳቸው ላይ ይመጣሉና እሳቸውን ልታይ ወደዚው ለመሄድ መቀነቷን አስራ ወደዚህ አላህ የሚጠላው ቦታ ለመሄድ አኮብኩባለች ።
አባትም ተነስቷል ፤ በሬ ገዝቶ ለጌቶች የሚያስገባውን ሰደቃ ሙሉ ዐመቱን ሲያጠራቅም ቆይቶ አሁን ጊዜው ነው ፤ አንድ ሶስት ጁባ ጫት መግዣም ኪሱ ስር መኖሩን ያረጋግጣል ፤ አልከሶ መውሊድ ሳምንቱን ሙሉ ድቤ እየተደለቀ አልከስዬ ይለመናሉ ፤ (ድርቂ ሺቅ አሹን) ድርቁን አሽሹልን ፣ (ደቺ አርጥቡለን) መሬቱን አርጥቡልን ፣ (ጩላልቻይ ቂሩን) ልጆቻችንን ጠንቁልን ፣ (ከአላህ አትጋቡን) ከአላህ አማልዱን ፣ (የቀብሪኔት ጂጁን) ቀብር ላይ ድረሱልን ብቻ ማይባል ጉድ የለም ።
_______________
አንተ ወጣት እስኪ ልጠይቅክ ፤ ወላጆችክን በዱኒያም በአኺራም ውርደትን እንዲከናነቡ ወደዚህ አላህ የሚጠላው ቦታ ይዘሃቸው ትሄዳለክን?
የለፋክበትን ገንዘብ እንኩ ወደ እሳት ሂዱ ብለክ ትሰጣለክን ?
ቤተሰብክን ማስተማር ሲገባክ አንተም ተጨምረክ ወደ እሳት ትጓዛለክን ?
ወንድሜ ሆይ አላህን ፍራ ፤ መቼ ሞት ወዳንተም ሆነ ወደ ቤተሰቦችክ እንደሚመጣ አታውቀውም ፤ አላህን እየተገዙ ሞታቸውን ይጠባበቁ እንጂ ሽርክ ላይ ሆነ አላህን እንዳይገናኙ ፍራ ፤ ሽርክ ላይ ሆኖ የሞተ ከሳሪ ነው ፤ መውጫም የለውም ።

(( አላህ በርሱ ማጋራትን በፍፁም አይምርም )) ኒሳዕ-48
__
አላህ ከሽርክ ይጠብቀን

Post a Comment

0 Comments