Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

አልከስኛና እና ኢኽዋንኛ


Abubeker Siraj

አልከስኛና  እና ኢኽዋንኛ 
ነገሩ እንዲህ ነው...ባለፉት ዐመታት ኢቢኤስ (EBS) የተባለ አንድ የኩፋሮች የቲቪ ቻናል ዕሁድ ጠዋት ላይ ';'የኢስላም ፕሮግራም'' በሚል የሚቀርብ የኢኽዋኖች 'ቢላል-ሾው' የሚባል የአየር ሰዐት አለ ። ይህ ፕሮግራም ላይ ይህን ዑማ እንደሰለጠኑት ሃገራት ትሪፕ (ጉዞ) ማስለመድ አለብን በሚል የተለያዩ አላህ ወደሚጠላቸው የሽርኪያት ቦታዎች እንደ አልከሶ ፣ ቃጥባሬና የመሳሰሉት ቦታ ኢኽ ዋኖችና አጫፋሪዎቻቸው ይሄዳሉ።

እናም ተራው ደርሶ በጄይሉ ሚዲያና በቢላል ኮሙኒኬሽን አማካኝነት ወደ አልከሶ ጉዞ ይኬዳል ። ጉዞው ሰውን ከሽርክ ለማስጠንቀቅ መስሏቹ ከሆነ ተሳስታቿል። በጣም የሚያሳዝነው እራሳቸውን ወደ ዳዕዋ ያስጠጉ ሁለት በኢኽ ዋን አስተሳሰብ የተበከሉ ዱዓቶች ወደዚህ ቦታ ይህን ግሩፕ እየመሩ ተጉዘው ነበር ። 

'ዳዒያህ' ሳዲቅ መሃመድ እና ለጊዜው ስሙን የማልጠራው አንድ ግለሰብ ስንትና ስንት ሽርኪያት የሚሰራበት ወደዚህ አልከሶ ወደተባለው ስፍራ መሄዳቸው ሳያንሳቸው 

«#በጣም_ደስ_ብሎናል_ምን_እንድንተባበራቹ_ትፈልጋላቹ?..» 
ብለው ሞራል ሰጥተው ተመልሰዋል (አላህ ሂዳያ ይስጣቸው ) ይሄን ቪድዮ ለመመልከት ይህን ሊንክ ይጫኑ .. http://youtu.be/z6DqFT--k5Q
__________ 
ወንድሜ ይሄን የምነግርክ ወድጄ አይደለም ፤ አይባቸውን ለማውጣትም አስቤ እንዳልሆነ ዕወቅልኝ ፤ ነገር ግን ይሄን ቪድዮ የተመለከቱና (አሁንም በዩቱብ በብዛት እየተሰራጨ ያለ ቪድዮ ነው) እነዚህ ዱዓት ተብዬዎች ቦታው ድረስ ሄደው በርቱ አልፎተርፎ ምን እንተባበራቹ ማለታቸውን በጠባብ አስተሳሰባቸው የተረዱ የኛው ወገኖች ወደዚህ ቦታ መሄድ ይቻላል ወይንም አለባቹ ወደሚል ሸሪዓዊ ማስረጃዊ ግንዛቤ ስለቀየሩትና እየየቀየሩት ስለሚገኝ ማስጠንቀቅ ግድ ሆኖብናል ።

እንደውም አንዳንዱ ምን ይላል ..
« አንተ ዛሬ ብድግ ብለክ ወደ ጌቶች (አልከሶ) አት ሂዱ ትላለክን ? እከሌ የተባሉት ቴሌቪዥን ላይ የሚቀርቡት ዑለማዎች ቦታው ድረስ ሄደው አልከሶን ዘይረው አድንቀው ምን እናግዛቹ ብለው እንኳን መጥተዋል ፤ አንተ ዛሬ መጥተክ ታወራልክ እንዴ ዝም በል..» ያለም አልጠፋም። 

እናም ወንድሜ አሁንም በድጋሚ ልምከርክ ፤ እራስክንም ቤተሰቦችክንም ቤተ-ዘመዶችክንም ወደዚህ ስፍራ እንዳይሄዱ ተማር አስተምር!!

አላህ ከሽርክና ከኢኽዋን ሴራ ይጠብቀን

Post a Comment

1 Comments

  1. Anti_Islam and Muslim Article. Have you ever talked with them why they did it?

    ReplyDelete