Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

አልከሶን በአዲስ አበባ

#አልከሶን_በአዲስ_አበባይሄ ደሞ ጉድ ሌላ ነው
አልከሶም አዲስ አበባ ላይ ይመለካሉ ፤ በከተማችን አዲስ አበባ ኮልፌ መሳለሚያ በተለምዶ ዜሮ አንድ (01) ቀበሌ ተብሎ የሚጠራው ሰፈር ውስጥ 'በይዲ' የሚባል መስጂድ ይገኛል ፤ ስያሜውን ያገኘው ከሸኽ በይዲ ሲሆን ሸኽ በይዲ የአልከሶ ልጅ ናቸው ፤ ይህ መስጂድ በየአመቱ ሻዕባን አስራአምስት ላይ ወደ ስልጤ ዞን አልከሶ መሄድ ያልቻሉ የዚህ አምልኮ አባላት ከሙሉ አዲስ አበባ ተሰባስበው ወደዚህ መስጂድ ገና ከጠዋቱ ይጎርፋሉ ፤ ድቤ ይደለቃል ፣ ጫቱ በገፍ ይቃማል ፣ ስለቱ ይቀርባል ፣ ለአልከስዬ ይታረዳል ፣ አልከስዬ ይለመናሉ ብዙ ብዙ ይሄን መስጂድ ካነሳን አይቀር የአልከሶ መቸባይ ወይንም የልጅ ልጅ የሆነው አብዲናስር በደዊ አልከሶ ማንሳት ይገባናል ።

አብድናስር በይዲ አልከሶ ወይንም በአጭሩ 'አብዲ በይዲ' ማነው ?
- አብዲ በይዲ ''ወሊይ ነው ሳሊህ ነው ጌቶች ነው'' የሚባል አደገኛ ጠንቋይ ነው ።

ስለ አብዲ በይዲ በአጭሩ ለማወቅ የወንድም ሳዳት እሱን አስመልክቶ የፃፈውን ፅሁፍ ለማንበብ ይሄን ሊንክ ይጫኑ .. http://goo.gl/LG1ZEx

ዋናው ይሄን ሰው ያነሳንበት አላማ ፤ ይህ ሰው የ አልከሶ የልጅ ልጅ ነው ተብሎ ስለሚታሰብ እዚው በደዊ መስጂድ አቅራቢያ የሚገኘው ቤቱ ላይ ሰዎች ጘይብን ይነግረናል ፣ ጉዳያችንን ያስፈፅምልናል ፣ በረካ ይሰጠናል ፣ ሃብት ያሸክመናል ብለው ዐመቱን ሙሉ ወደዚህ ሰው ይመላለሳሉ ።
አንድ ሰሞን አልከሶ አካባቢ ወባ ገባ ተብሎ ሲወራ ይህን ገጥመዋል
ኪሉ ኮልፌ በይዲ ያጎን መርፌ
አደብ አሱ ወበ ኤለ ባልከሶ
(ሂዱ ኮልፌ በይዲ መርፌ ይወጋሉ
ስርዓት ያዙ ወባ የለም አልከሶ)

የሚገርመው እዚህ መስጂድ ጀምዐተ ተብሊጎች በብዛት የሚገኙ ሲሆን አልፎ ተርፎ ከሩቅ እናስተምራለን ብለው ለአርባ ቀንና አስር ቀን ወደዚህ መስጂድ ይጎርፋሉ ነገር ግን እንኳን ይሄን በሽርክና ኹራፋት የተጨማለቀ ማህበረሰብ ሊያስተምሩ ይቅርና ከነርሱ ጋር አብረው አንዳንድ የተውሂድ ዱዐቶች ቦታው ላይ እንዳያስተምሩ አዳጋች ሆነውባቸው ለብዙ ዐመት ቆይተዋል ። አላህ ሂዳያ ይስጣቸው

በሳምንት አንድ ቀን ማክሰኞ ፣ በዐመት አንድ ሳምንት ከሻዕባን አጋማሽ ጀምሮ እዚህ ቦታ ብዙ ሽርኪያትና ኹራፋት በመንዙማ መልክ የሚዜም ዕርድና መስዋዕት የሚቀርብ ሲሆን ፤ በዚህ መልኩ ለብዙ ዐመታት ቆይቷል።

እዛው አካባቢ ያላቹ ወጣቶች ቤተሰቦቻቹን በማስተማርና በመገሰፅ ከዚህ አላህ ወደሚተላው ቦታ እንዳይሄዱ ማስተማር ይገባናል ።