Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

አልከሶ አይጠቅሙም አይጎዱም


Abubeker Siraj

አሰላሙአለይኩም ወራህመቱላሂ ወበረካቱወገን...! ወገን..! ወገን...!
እራስህን ቤተሰብክን ቤተ-ዘመድክን ከእሳት አድንSHARE..! SHARE..! SHARE..!
የሽርክ የኹራፋት ድግስ በስልጤ ዞን አልከሶ (#ሶስት_ቀን_ቀረው!!)______________________ ረመዳን ደርሶ ይህን ታላቅ ወደ አላህ መቃረቢያ የተባረከ ወር ለመቀበል ሙስሊሙ ዑማ አሰፍስፎ በተጠንቀቅ በሚጠባበቅበት በያዝነው ወርሃ ሸዕባን ከወደ ስልጤ ግን ጉዳዩ ሌላ ነው። 
በስልጤ ዞን አልከሶ አካባቢ የሚገኝ አልከስዬ የተሰኘ አንድ መስጂድ አለ ። መስጂዱ የተገነባው በሺ ዘጠኝ መቶ ሰላሳ አራት አመተ ልደት ሲሆን ፤ በየዓመቱ የረመዳን ዋዜማ ኒስፈ ሻዕባን ማለትም ሻዕባን አስራአምስት ላይ በዚህ መስጂድ በተለምዶ የአልከስዬ ልደት (መውሊድ) በማለት የሚያከበር ክብረበዓል አለ ። ይህ መውሊድ ከተጀመረ አሁን አንድ መቶ አምስተኛውን ዐመት የያዘ ሲሆን ። ከአራቱም የአገሪቱ አቅጣጫ ብሎም ከባሕር ማዶ ወደዚህ አላህ የሚጠላው ቦታ ህዝቤ ይጎርፋል ።________ግጭት ቁጥር አንድ(1)#ቀብር_ዚያራ_ክልል_አቋርጦ_ጉዞየአላህ መልክተኛ (ኮርቻ) ወደ ሦስት ቦታዎች እንጂ አይጫንም ወደ አላህ ቤት ፣ ወደ መስጂድ አቅሷ እኔ ወደ መስጂዴ (መዲና) ። (ቡኻሪ)______.... ህፃኑ ፣ ወጣቱ ፣ አዛውንቱ ፣ ሽማግሌው ወደዚህ ስፍራ የሚመጣው በመውሊዱ ሰበብ የተዘጋጀውን ምግን ብቻ ተመግቦ ለመመለስ ብቻ መስሏቹ ከሆነ ተሳስታቿል ፤ የሚመጣው ሕዝብ ሁሉ ወደዚህ የአምልኮ ስፍራ ሲመጣ ባዶ እጅ አይመጣም በነፍስወከፍ የየራሱን ወጪ ያወጣበትን እሱ ሰደቃ ይሆናል ብሎ የሚያስበውን ፣ ስለቴ ተሳካልኝ ወይንም ልሳልበት ነው ብሎ የያዘውን ስጦታ ከርሱ ጋር ያመጣል ። ይህን ማድረግ ያልቻለ (ማለትም ወደዚህ ስፍራ ለመምጣት ያልቻለ) ካለ ይሄን ገንዘብ ወይንም የቁም ከብት ብቻ የተቻለውን ስጦታ በሰው ይልካል ።__________ግጭት ቁጥር ሁለት (2)#ስለት_የሚገባው_ለአላህ_ብቻ_ነውإِذْ قَالَتِ امْرَأَتُ عِمْرَانَ رَبِّ إِنِّي نَذَرْتُ لَكَ مَا فِي بَطْنِي مُحَرَّرًا فَتَقَبَّلْ مِنِّي ۖ إِنَّكَ أَنتَ السَّمِيعُ الْعَلِيمُ የዒምራን ባለቤት (ሐና) «ጌታዬ ሆይ፦ እኔ በሆዴ ውስጥ ያለውን (ፅንስ ከሥራ) ነጻ የተደረገ ሲኾን ለአንተ ተሳልኩ፡፡ ከእኔም ተቀበል አንተ ሰሚው ዐዋቂው ነህና» ባለች ጊዜ (አስታውስ)፡[ዒምራን -35]_________እዚህ መስጂድ አቅራቢያ አልከሶ የተባሉ ሸኽ ቀብር እንዳለ ይታመናል ፤ ዋናው የመውሊዱ አላማም ይህን ቀብር መዘየር ሲሆን ፤ ነገሩ ግን ከዚያራም አልፏል ፤ እኚህ ሸኽ ይመጀንባቸዋል ፣ ይለመናሉ ፣ ይታረድላቸዋል ፣ ወደ ቀብራቸው ይሰገድላቸዋል ፣ ድረሱልን እያሉ ይማኗፀቸዋል ። ከሞላ ጎደል አብዣኛው የአላህ መብት ይሰጣቸዋል ። (አላህ ይጠብቀን)__________ግጭት ቁጥር ሶስት #አምልኮ_የሚገባው_ለአላህ_ብቻ_ነውيأيها الناس ضرب مثل فاستمعوا له إن الذين تدعون من دون الله لن يخلقوا ذبابا ولو اجتمعوا له وإن يسلبهم الذباب شيئا لا يستنقذوه منه ضعف الطالب والمطلوبእናንተ ሰዎች ሆይ ምሳሌ ተደርጎላችዋልና አዳምጡ እነዚያ ከአላህ ውጭ የምትጠሯቸው ነገሮች ዝንብ እንኳ መፍጠር አይችሉም ቢሰባሰቡም እንኳ (ተጋግዞ ለመፍጠር) (ከምግባቸው ላይ) ዝንብ አንዳች ነገር አንስቶባቸው ቢሄድ ማስጣል አይችሉም ፈላጊውም ተፈላጊውም ደካማ ተደረገ። [አልሃጅ-73]___________በቁጥር ሁለት እንገናኝ ኢንሻአላህ ይቀጥላል