Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

አቡ መስዑድ አልአንሷሪ ረዲየላሁ ዐንሁ ከሑዘይፋህ ረዲየላሁ ዐንሁ ዘንድ ገባና

January 23 

አቡ መስዑድ አልአንሷሪ ረዲየላሁ ዐንሁ ከሑዘይፋህ ረዲየላሁ ዐንሁ ዘንድ ገባና “የአብደላህ አባት ሆይ! እስኪ ምከረን” አለው፡፡“እውነቱ አልደረሰህም እንዴ” ሲል ጠየቀው“እንዴታ! በጌታዬ እምላለሁ ደርሶኛል!” አለው“እንገዲያውስ የጥመት ሁሉ ጥመት ማለት ቀድመህ (እውነቱ እንደደረሰህ) ትቃወመው የነበረን ነገር ዛሬ እንደመልካም መቁጠርህ ነው፡፡ ቀድመህ (እውነቱእንደደረሰህ) እንደ መልካም ትመለከተው የነበረን ነገር ዛሬ መቃወምህ ነው፡፡ አደራህን በዲን ላይ ከመለዋወጥ ተጠንቀቅ!! የአላህ ዲን አንድ ነውና!!!” አለው፡፡ (ሙሰነፉ ዐብዲር-ረዛቅ፡ 2045)
><><><><><><><><><><><><><><><><><><><><
1. ሱብሓነላህ!! እስኪ ትላንት ወደ ተውሒድ ሲጣሩ የነበሩ ዛሬ ተለዋውጠው 360 ዲግሪ ተሸከርክረው ፀረ-ተውሒድ የሆኑ ሰባኪዎችን በዓይነ-ህሊናችሁ ቃኙ፡፡ ትላንት ጠንካሮች በነበሩ ጊዜ ቦታም፣ ዝናም፣... አልነበራቸው፡፡ አሁን ግን መድረክ ተለቆላቸዋል፡፡ ካሴቶቻቸው እየታተሙላቸው ነው፡፡
2. እስኪ “አደራህን በዲን ላይ ከመለዋወጥ ተጠንቀቅ!! የአላህ ዲን አንድ ነውና!!!” የሚለውን አስምሩበትና በየሰፈሩ የሚገኙ ተለዋዋጭ እስስት ኢኽዋኖችን አስቡ፡፡ ጠንካራው ጋር ጠንካራ፣ ደካማው ጋር ደካማ ሆነው ይቀርባሉ፡፡ ሁሉን ለመያዝ፡፡ አንዳንዶቹ “አካባጆች” ጋር የሚቀላቀሉበት አጭር፣ “ቦርቃቆች” ጋር የሚቀላቀሉበት ረጅም ሱሪ አላቸው፡፡ አንዳንዶቹ ግን ረቀቅ ይላሉ፡፡ ሱሪያቸው ድንበር ላይ ነው-ቁርጭምጭሚት ላይ፡፡ “ሰፋፊዎች ጋ ሲደርሱ ቀበቷቸውን ያላላሉ፡፡ “ጠባቦቹ” ጋ ሲደርሱ ደግሞ፣...፡፡” እኔ ማሳጠር፣ ማስረዘም ብቻውን የሱኒ መታወቂያ ነው እያልኩ አይደለም፡፡ ግን መለዋወጥ ለምን?
><><><><><><><><><><><><><><><><><><><><