Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ሰካራሙ ስለስካር ሲመክር

January 23 

አባትና ልጅ ጠላ ይጠጣሉ፡፡ አባት ልጁን ስካር ጥሩ እንዳልሆነ ሊመክረው ፈለገ፡፡ (ድንቄም ምክር፣ ደግሞ የሰካራም ምክር!) አባት፡- “ልጄ ሆይ! ሁሉም ነገር ልክ አለው፡፡ መጠጥም እንዲሁ፡፡ ከልክ ካለፈ ጥሩ አይደለም፡፡”ልጅ፡- “እሱ ገባኝ አባዬ፡፡ ግን እንዴት ነው ልካችንን የምናውቀው?”አባት፡- ከማዶ እያመላከተ፣ “እነዚያ ሁለት ሰዎች ይታዩሃል?”ልጅ፡- “እሺ” አለ፡፡ ቀጥሎ የሚመጣውን በጉጉት በመጠበቅአባት፡- “አራት ሆነው ከታዩህ ሰክረሃል ማለት ነው፡፡”ልጅ፡- “እንዴ አባዬ እዚያ ማዶ እኮ ያለው አንድ ሰው ብቻ ነው?!!!” (ምንጩን አላስታውስም)1. ለካስ አባትየው እራሱ ሰክሮ ኖሯል!! አሁን ይሄ ሰውዬ 3 ፌደራሎችን መንገድ ላይ ቢመለከት ምን የሚል ይመስላችኋል?2. ሰዎቹ “አትስከር እንጂ ጠጣ” ነው አይደል የሚሉት ይሁን? ግን እሱን መቼ ነው የሚያውቁት? ሲሰክሩ?3. ልክ እንደዚህ ሰካራም የተንሻፈፈ “ሒክማ”፣ የተንሻፈፈ “ወሰጥያ” አብጅተው፣ ሒክማ ይኑራችሁ”፣ “መካከለኛ” ሁኑ” የሚሉን አሉ፡፡ ግና ባወራ አይደለም፡፡ መካሪ ሁሉ መካሪ አይደለም፡፡ ቢሆንማ ይሄም ሰካራ “እየመከረ” ነበር፡፡