Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ተውሂዱል አስማኢ ወሲፋት

ተውሂዱል አስማኢ ወሲፋት
http://www.facebook.com/emnetihintebiq
ተውሂዱል አስማኢ ወሲፋት ማለት አላህ በቁርዓንና ሐዲስ የተወሱ ያማሩ ስሞችና የላቁ ባህሪዎች እንዳሉት በነዚህም ስምና ባህሪዎች አምሳያ የሌለው ብቸኛ መሆኑን ማመን ነው፡፡

ይህ የተውሂድ ክፍል ቀላልና ግልፅ ሆኖ ሳለ ነገር ግን ለቁርዓንና ሀዲስ መረጃዎች እጅ ባለመስጠትና አጉል ፍልስፍና ውስጥ በመግባታቸው ምክንያት ብዙ የሙስሊም ቡድኖች ሲሣሣቱበትና ከትክክለኛው መንገድ ሲያፈነግጡበት ይስተዋላል::

ስለዚህ ከስህተት ለመጠበቅና ትክክለኛውን እምነት ለመጨበጥ በዚህ ርዕስ ላይ ያሉትን የቁርዓንና የሐዲስ ጥቅሶችን ያለምንም የትርጉም ማዛባት ቀጥተኛውን የቃል ትርጓሜያቸውን መያዝና ማመን ግድ ነው፡፡

በዚህ ርዕስ ላይ የተጠቀሱ ቁርዓናዊና ሀዲሳዊ ጥቅሶችን ያለምንም የትርጉም ማዛባት ቀጥተኛውን ትርጉም እንድንከተል ከሚያስገድዱን ነጥቦች ውስጥ፦

1ኛ አላህ የተናገራቸው በመሆናቸውና እሱ ደግሞ ከማንም ይበልጥ ለራሱ የሚገባውንና የማይገባውን የሚገለፅባቸውንና የማይገለፅባቸውን ስሞችና ባህሪዎችን አዋቂ መሆኑ፡፡

2ኛ አላህ ከማንም ይበልጥ እውነት ተናጋሪና በፍፁም የማይዋሽ መሆኑ::

3ኛ አላህ ከማንም ይበልጥ ባማረና ግልፅ በሆነ ንግግር ፍላጎቱን የሚገልፅ መሆኑ::

4ኛ አላህ ለባሮቹ ከማንም ይበልጥ አዛኝ በመሆኑ ለስህተት የማይዳርጋቸውንና የሚመሩበትን ግልፅ ንግግር ስለሚናገር፡፡

5ኛ ነብዩ የተናገሯቸው በመሆናቸውና እሳቸው ደግሞ ከአላህ ቀጥሎ ከላይ በተጠቀሱ ባህሪዎች የመጀመሪያው ተገላጭ በመሆናቸው::

6ኛ የአላህን ስሞችና ባህሪዎችን የሚጠቅሱ ቁርዓናዊና ሀዲሳዊ ጥቅሶችን በቀጥታ ትርጉማቸው ማፅደቅ የቀደምት ብርቅዬ ትውልዶችና የታላላቅ የዲን መሪዎች መንገድ በመሆኑ፡፡
ለምሳሌ ያህል የአራቱ መዝሀቦች መሪዎችን አቋም በአጭሩ እነሆ፡-

ከኢማም አቡ ሀኒፋ ንግግሮች፡-
“ማንኛውም ሰው አላህ እራሱን በገለፀበት ባህሪያት መግለፅ እንጂ ስለ አላህ በግል አስተያየቱ አንዳችም ነገር መናገር የለበትም”

“አላህ በቁርአኑ የተናገራቸው፦ ፊት፣እጅና ነፍስ የርሱ መገለጫ ባህሪዎች ናቸው፡፡ እጁ ሀይሉ ወይም ፀጋው ነው ማለት የርሱን ባህሪ ማጥፋት በመሆኑ እንዲህ መባል የለበትም”

“አላህ ይቆጣል ይወዳል:: ቁጣውን ቅጣት ውዴታውን ምንዳ ማለት አይቻልም”
ከኢማም ማሊክ ንግግሮች፡-

አንድ ሰው መጥቶ “የዐብድራህማን አባት ሆይ! አራህማን አርሽ ላይ ወጣ እንዴት ነው የወጣው? በማለት ሲጠይቃቸው “መውጣት የታወቀ ነው እንዴት እንደሆነ ግን ማወቅ አይቻልም በዚህ ማመን ግዴታ ሲሆን ስለሱ መጠየቅ ቢድዓ ነው በማለት መለሱለት”

ከኢማሙ ሻፍዕይ ንግግሮች፡-
“አላህ እራሱን እንደገለፀውና ሰዎች ከሚገልፁት በላይ ሆኖ ነው ያለው”
“ቁርዓንና ሀዲስ የገለፁትን ባህሪዎች እያመንን እንዲህ በማለት ከራሱ አምሳያን እንዳስወገደው እናስወግዳለን”

لَيْسَ كَمِثْلِهِ شَيْءٌ وَهُوَ السَّمِيعُ الْبَصِيرُ

“የሚመስለው ምንም ነገር የለም እርሱም ሰሚው ተመልካቹ ነው” (አሽ ሹራ 11)
ከኢማሙ አህመድ ንግግሮች፡-

“አላህ እራሱን በገለፀበት ወይም መልዕክተኛው በገለፁት ባህሪ እንጂ መግለፅ አይቻልም፡፡ ቁርዓንና ሐዲስን መተላለፍ አይፈቀድም”

Post a Comment

0 Comments