Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

የተውሂድ ጠቀሜታዎች

የተውሂድ ጠቀሜታዎች
ተውሂድ ከዲን መሰረታዊ ከሆኑ ነገሮች በሙሉ ቅድሚያ ሊቸረው የቻለው አያሌ ጠቀሜታዎች ስላሉት ነው::ከነዚህም መካከል የሚከተሉት የጎላ ጠቀሜታዎች ይገኛሉ::
1_ ተውሂድ በዱንያም ሆነ በ አዀራ ለሚከሰቱ ጭንቀቶችና ቅጣቶች መከላከያና መጠበቂያ ነው
2_ በልቦናው ውስጥ ቅንጣት ታክል እንኳ ተውሂድ ኖሮት ወንጀሎችን ፈፅሞ
የአላህ እዝነት ሳያገኘው ቀርቶ እሳት ቢገባ ግለሰቡ እሳት ውስጥ ዘውታሪ አይሆንም::ነገር ግን ሙሉ በሙሉ ልቦናው በተውሂድ የተሞላ
ከሆነ በዱንያ ከጥመት የራቀ ይሆናል በ አዀራ ደግሞ ሙሉ ደህንነትን ያገኛል(እሳት ከነጭራሹ አይገባም)::
3_ ተውሂድ የአላህን ውዴታንና ምንዳውን ለማግኘት ብቸኛው ሰበብ ነው::
4_ ተውሂድን የያዘ
ግለሰብ ብዙ አስከፊ ነገሮች ቢገጥሙትም እንኳ ከአላህ ውሳኔ መሆኑን በማመን በህይወቱ በጣም ደስተኛና የተረጋጋ ይሆናል::
5_ ተውሂድን የያዘ ግለሰብ ለፍጠር ተገዥ ባሪያ አይሆንም::የሚፈራው:የሚከጅለው:ደጅ የሚጠናው ገታውን አንድ አላህን ብቻ ይሆናል::ይህ ነው የክብርና የልቅና መገለጫ!
6_ ተውሂድን የያዘ ግለሰብ አላህ መጥፎ ከሚባል ነገር በሙሉ ሊጠብቀውና ጀነትን ሊያስገባው እንዲሁም በዚህች አለም እርሱን በማውሳት የመንፈስ እርካታን ሊያጎናፅፋቸው ቃል ገብቷል::

Post a Comment

0 Comments